የጉበት ስብ በሽታ ምንድን ነው ?መከላከያውስ?
ሀኪምሰለሞን አዳሙ
iframe width="791" height="445" src="https://www.youtube.com/embed/Afzp4sB63vU" frameborder="0" allow="accelerometer; autoplay; clipboard-write; encrypted-media; gyroscope; picture-in-picture" allowfullscreen>
ጉበት መርዛማ ንጥረ ነገሮች በደም አማካኝነት ወደ ተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች ውስጥ ዘልቀው ገብተው ጤናችን አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ብርቱ ተጋድሎ የሚያደርግ የሰውነታችን ክፍል ነው፡፡ በምንመገባቸው ምግቦችና መጠጦች እንዲሁም ለተለያዩ በሽታዎች ማከሚያነት በምንወስዳቸው መድሃኒቶች ውስጥ የሚገኙና ለሰውነታችን አላስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ሁሉ በጉበት አማካኝነት እየተመረጡ እንዲወገዱ ይደረጋል፡፡ ቀይ የደም ሴሎቻችን የአገልግሎት ዘመናቸውን ሲያጠናቅቁ የሚወገዱትም በዚሁ በጉበታችን አማካኝነት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጉበታችን ፋቲ አሲድ፣ ፕሮቲን፣ ጉሉኮስንና በሽታን ለመከላከል የሚያስችሉ ንጥረ ነገሮችን እያመረተ ለሰውነታችን ክፍሎች እንዲዳረሱ ያደርጋል፡፡ የዚህ የሰውነታችን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ሰጪ የሆነው የሰውነታችን ክፍል በህመም መጠቃት በሰውነታችን ሥርዓተ ዑደት ላይከፍተኛተፅእኖንያሳድራል፡፡
ጉበትን በእጅጉ በመጉዳት ከሚታወቁ ነገሮች መካከል አልኮል ዋንኛው ነው፡፡ በአልኮል ሳቢያ የሚከሰተው የጉበት ስብ በሽታ በርካቶችን ለሞት እየዳረገ እንደሚገኝ የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ አልኮል አመጣሽ በሆነው የጉበት ስብ በሽታ የተጠቁ ሰዎች አምስት አመት በህይወት የመቆየታቸው እድል 50በመቶ % ብቻ ነው፡፡ በሽታው የጉበትን የመሥራት አቅም በፍጥነት የሚያዳክምና ከአገልግሎት ውጪ የሚያደርግ በመሆኑ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ለህልፈት የመዳረጋቸው እድል ከፍተኛ ነው፡፡ በሽታው ምንም አይነት ምልክቶችን ሳያሳይ ሊቆይ እንደሚችል ከ75% በላይ የሚሆኑት የጉበት ስብ ህሙማን በበሽታው የመያዛቸውን ምልክት የሚያሳዩት ጉበታቸው የመጨረሻ ደጃ ላይ ሲደርስና ውሃ መያዝ ሲያቅተው ነው የበሽታው ስርጭት በአገራችን በተለይ እድሜያቸው ከአርባ ዓመት በላይ የሆኑና አልኮል አዘውታሪ ሰዎች በበሽታው የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው ህፃናትም ለበሽታው ተጋላጭናቸው፡፡
የጉበት ጤና በማቃወስ ከሚታወቁት ነገሮች መካከል አንዱና ዋንኛው በሆነው ስብ የተጠቃ ጉበት ለጉበት ስብ በሽታ የሚጋለጥ ሲሆን ይህም በሁለት ምክንያቶች የሚከሰትና ጉበትን ወደ ቃጫነት በመለወጥ ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ በሽታ ነው፡፡ የጉበት ስብ በሽታ ከሚከሰትባቸው ሁለት ምክንያቶች መካከል አንደኛው የአልኮል መጠጥ ሲሆን ሌላው ከአልኮል ውጪ በሆኑ ሌሎች ምክንያቶች ማለትም ለተለያዩ በሽታዎች ማከሚያነት የምንወስዳቸው መድሃኒቶች እንዲሁም የስኳር በሽታ፣ ውፍረት፣ ጉሉኮስ የማከማቸት ችግርና ኮፐርና ዚንክ የተባሉ ማእድናትን በሰውነት ውስጥ ማከማቸት… ለጉበት ስብ በሽታ መነሻ ምክንያት ሆነው ይጠቀሳሉ፡፡ የአልኮል መጠጦች በጉበት ስብ በሽታ ለመጠቃት 40በመቶ ድርሻይኖራቸዋል፡፡
የአልኮል መጠጦች ለጉበት ስብ በሽታ መነሻ የሚሆኑባቸውን መንገዶች “የአልኮል መጠጦችን በምንጠጣበት ጊዜ በአልኮሉ ውስጥ የሚገኙና ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች ጥቅም ላይ ከዋሉ በኋላ ቅሪቱ ንጥረ ነገር በጉበታችን ውስጥ ያልፋል፡፡ በዚህ ጊዜም የጉበታችን ሴሎች ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ ጉበታችን በአግባቡ ሥራውን እንዳያከናውን ያደርገዋል፡፡ ጉበታችን ስራውን በአግባቡ ማከናወን ሲሳነው ወደ ሰውነታችን የገቡትና በጉበታችን አማካኝነት መጣራት የሚገባቸው ንጥረ ነገሮች በሰውነታችን ውስጥ ዝም ብለው ይከማቻሉ፡፡ በዚህ ጊዜም ጉበታችን ከመጠን በላይ በሆኑ ስቦች እንዲጨናነቅ ያደርጋል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ የጉበታችንን ሴሎች ወደ ቃጫነት በመቀየር ጉበታችን ፋትን ማመንጨትና መጠቀም እንዳይችል እንዲሁም ውሃ መያዝም እንዲያቅተው ያደርገዋል፡፡ ጉበት ሲታመም ፈሳሽ የመቋጠር አቅሙን ያጣል፡፡ ይህም ፈሳሽ በሆዳችን ውስጥ እንዲጠራቀም በማድረግ ሆዳችንን ያሳብጠዋል፡፡ መጣራት ሲኖርባቸው ሳይጣሩ ቀርተው በሰውነታችን ውስጥ የተጠራቀሙት መርዛማ ንጥረ ነገሮችም በደም አማካኝነት ወደ ጭንቅላታችን ውስጥ ገብተው ራሳችንን ያስቱናል፡፡ በተጨማሪም ፕሮቲን ጉሉኮስ፣ ፋትና በሽታን የሚከላከሉ ንጥረ ነገሮች በሰውነታችን ውስጥ መመረታቸው፣ መከማቸታቸውና በጥቅም ላይ መዋላቸው ያቆማል፡፡
ከአልኮል ውጭ የጉበት ስብ በሽታን ከሚያስከትሉ ነገሮች መካከል የሚጠቀሰው ለተለያዩ ህመሞች የምንወስዳቸው የተለያዩ ይዘቶች ያሏቸው መድሃኒቶች ናቸው፡፡ በተለይ ቴትራሳይክሊን፣ የደም ብዛት መድሃኒቶች፣ ለካንሰር ህሙማን የሚታዘዙ መድሃኒቶችና ሆርሞኖች በአብዛኛውን ጊዜ ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር መድሃኒቶች ተደራርበው እንዳይወሰዱ ለማድረግ የሚመከረው በመድሃኒቶች ሳቢያ የሚከሰቱ የጐንዮሽ ጉዳቶችን ለመቀነስ በማሰብ ነው፡፡ የጉበት ስብ በሽታ ምንም አይነት ምልክቶችን ሳያሳይ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ሊደርስ በአብዛኛው የችግሩ መኖር የሚታወቀው ጉበቱ ከጥቅም ውጪ ከሆነና ለመዳን እጅግ አስቸጋሪ ከሚሆንበት ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ነው፡፡ አንዳንድ የጉበት ስብ በሽታ ህሙማን የእግር ማበጥ፣ የአይን ቢጫ መሆን፣ በቀኝ ጐን በኩል የህመም ስሜቶች መኖር ሊያጋጥማቸው እንደሚችልም ገልፀዋል፡፡ በሽታው ስር ያልሰደደ ከሆነና ጉበቱ ሙሉ በመሉ ከጥቅም ውጪ ከመሆኑ በፊት ከተደረሰበት በተለያዩ ቫይታሚኖችና መድሃኒቶች በሽታውን አክሞ ማዳን እንደሚቻል ጠቁመው ከጥቅም ውጪ ለሆነ ጉበት የሚሰጥ ህክምና በአገራችን ደረጃ አይሰጥም ፡፡ አልኮልን አዘውትሮ አለመጠጣት፣ መድሃኒቶችን አብዝቶ አለመጠቀም፣ በአመጋገብ ላይ ጥንቃቄ ማድረግና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የጉበት ስብ በሽታን ለመከላከል ይረዳሉ፡፡
የጉበት ስብ በሽታ ምንድን ነው ?መከላከያውስ?
የጉበት ስብ በሽታ ማለት አላስፈላጊ የሆነ ስብ በጉበት ላይ መከማቸት ማለት ነው።
የጉበት ስብ በሽታ መንስዔዎች
-የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መጠቀም
-በደም ውስጥ ያለ የስብ መጠን ከፍተኛ መሆን
-የስኳር ህመም
-በዘር ውስጥ የጉበት በሽታ ተጠቂ መኖር
-ለሌላ በሽታ የሚወሰዱ መድሀኒቶች
ለጉበት ስብ በሽታ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
-የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መጠቀም
-ከሀኪም ትዕዛዝ ውጪ እና ከተገቢው በላይ መጠኑ ከፍ ያለ መድሀኒት መውሰድ ለምሳሌ:- ፓራሲታሞል
-እርግዝና
-ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል መጠን
-የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መኖር
-ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች አብዝቶ መመገብ
የጉበት ስብ በሽታ ምልክቶች
1.የምግብ ፍላጎት መቀነስ
2.የክብደት መቀነስ
3.የሆድ አካባቢ ህመም
4.የድካም ስሜት መኖር
5.ማዞር እና ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት
6.ማቅለሽለሽ እና ወደ ላይ ማለት
7.በሆድ የላይኛው የቀኝ ክፍል ላይ ከፍተኛ ህመም መኖር
ጉበት በከፍተኛ ደረጃ ስትጎዳና ቁስለት ሲፈጠር …
1.በሆድ አካባቢ በፈሳሽ መሞላት እና እብጠት መኖር
2.የቆዳ እና የዓይን አካባቢ ወደ ቢጫነት መቀየር
3.በቀላሉ መድማት
4.ራስን መሳት
የጉበት ስብ በሽታን እንዴት መከላከል ይቻላል?
-የአልኮል መጠጥ አብዝቶ አለመጠቀም
-ከሀኪም ትዕዛዝ ውጪ መድሀኒት አለመውሰድ
-የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
-ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች አለመመገብ
የጉበት ስብ በሽታ ከተከሰተ በኋላ በቤት ውስጥ እንዴት ማከም ይቻላል?
1.የፖም አቼቶን መጠቀም(Apple cider vinegar)
2.የሎሚ ጭማቂን በቀን ከ2-3 ጊዜ መጠጣት
3.በቀን ከ3-4 ሲኒ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት
4.ግማሽ የሻይ ሲኒ እርድ ከግማሽ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሃ ጋር በማዋሃድ በቀን 2 ጊዜ መጠጣት
5.መጨናነቅን ማቆም
6.ፓፓያን መመገብ
7.በቀን ከ8-10 ብርጭቆ ንፁህ ውሃ መጠጣት
8.በቂ እረፍት ማድረግ
9.አትክልትና ፍራፍሬን አዘውትሮ መመገብ
10.የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር
11.በየጊዜው ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ክትትል ማድረግ

• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736
የወይባ ጢስ የተቀመመም ያልተቀመመም በጅምላም ይሁን በችርቻሮ መረከብ የምትፈልጉ 0941454593 /0989020202 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።