የሳይነስ በሽታ
Author: Hakim Solomon
Date: 2021-03-03
ቅዱስሚካኤልየባህልህክምና
ሀኪምሰለሞንአዳሙ
የሳይነስ በሽታ የምንለው በአፍንጫ ቀዳዳ መተለፊያ አካባቢ መቆጣት ወይም ማበጥ ሲሆን ንፍጥን እንዲቀጥን ያደርጋል እንዲሁም በአፍንጫ አካባቢ ግፊት በመጨመር እራስ ምታትን ይፈጥራል ።
የሳይነስ በሽታ መንስኤዎች የሚከተሉት ናቸዉ እነርሱም ፦ አለርጂ ፣ ቅዝቃዜ ፣የጥርስ ኢንፊክሽን እና መጥፎ ጠረን ናቸዉ ።
የሳይነስ በሽታ ምልክቶች ደግሞ የሚከተሉት ናቸዉ እነርሱም ፦ከአፍንጫ የሚወጣ ቀጠን ያለ ፈሳሽ መፍሰስ /መጥፎ ጠረን ያለው ሊሆን ይችላል / ፣ የፊት ሕመም ፣ እራስ ምታት ፣ ትኩሳት፣ አይን አካባቢ ሕመም መሰማት ፣ መጥፎ የአፍ ጠረን፣ የጆሮ ወይም የጥርስ አካባቢዎች ላይ ግፊት መፈጠር የመሳሰሉት ናቸዉ ።
የሳይነስ በሽታን ለመከላከል ማድረግ የሚገባን ነገሮች ፦
1 ብዙ ፈሳሽ መውሰድ ትኩስ መጠጥ እንደ ሻይ የመሰሉትን መውሰድ
2 አፍንጫን ሊከፈቱ የሚችሉ ነገሮች መጠቀም
3 ለብ ያለ ውሃ እና 1/2 ጨው ማንኪያበማድረግ ገሮሮ አካባቢ ማፅዳት
4 በሙቅ ውሃ ገላን መታጠብ
5 መጥፎ ሽታን ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮች ማፅዳት
6 ወደ ሕክምና ተቋማት በመሄድ በሐኪም ትዕዛዝ የሚሰጡ መድኃኒት መውሰድ ናቸዉ ።
• ለበጠ መረጃ ፡- ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ጎራ በማለት ሀኪም ሰለሞንን ያማክሩ
• ሀኪም ፡- ሰለሞን አዳሙ
• አድራሻ ፡- ቦሌ ሚካኤል በዋናው በር መግቢያ ደሴ ህንፃ ፊትለፊት
ስልክ፡- 0989020202 ወይም ፡- 0911810736