ዝንጅብል ለምግብ አለመፈጨት
Author: solomon
Date: 2026-02-04
ዝንጅብል ለምግብ አለመፈጨት
አንድ ራስ ዝንጅብል ወስደው ይፍጩ ይህንን ከሎሚ ውሀ ጋር አኝከው ይዋጡ።ፈጣን እፎይታን ያገኛሉ።እንዲሁም 1 ማንኪያ የእርድ ዱቄት ከአንድ ብርጭቆ ትኩስ ሻይ ጋር አዋህደው ይውሰዱ ።ይህ በተለይ ለረጅም ጊዜ ለቆየ ተቅማጥ በሽታ በቀን ሶስት ጊዜ ይታዘዛል።የዕርድ ዱቄት ሻይ በተከታታይ በመጠቀም የአንጀት ኢንፌክሽን ማከም ይቻላል። በዝንጅብል ውሀ አንድ ማንኪያ የዕርድ ዱቄት 1 ብርጭቆ በእየለቱ መውሰድ አንጀትን ከተለያዩ በሽታዎች በተለይ ጥገኛ ተዋስያን ያፀዳል።ድገተኛ ተቅማጥንም ሆነ የቆየ ተቅማጥን ለማከም ይረዳል።
አንድ የሻይ ማንኪያ ትኩስ የዝንጅብል ልንቀጥ ሎሚና ማርን በኩል መጠን ይደባልቁ።ከድብልቁ ጠዋት በባዶ ሆድ የሻይ ማንኪያ መመገብ ምግቡን ለማሽከርከር የምግብ አምሮትን ከፍ ለማድረግና የደም ዝውውር ለማቀላጠፍ ይረዳል።ስድስት ግራም ትኩስ የዝንጅብል ፍሬ ከጥቂት የገደል ጨው ጋር ለተከታታይ 10 ቀናት ከምግብ በፊት አኝከው መዋጡ በሆድ ዕቃ ውስጥ የሚከማች አየርን ለማስወገድ ይጠቅማል። የምግብ አለመፈጨት ችግር ካለበዎ ምግብ ላይ ጥቂት የገደል በመነስነስ ይመገቡ። ወይም አንድ ራስ በደቃቁ የተከፈለ ዝንጅብል በቅቤ ጠብሰው መጠነኛ ጨው ከጨመሩበት በሀላ በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ ቁንጣንን መከላከል ይቻላል። ከዝንጅብል ጋር የረጋ ወተትን በመጠጣት በሆድ ዕቃ ውስጥ የተጣበቀ አየርን የአንጀት ችግሮችን ማከም ይቻላል። አንድ የሻይ ማንኪያ የተነቀጠ ዝንጅብል በአንድ ብርጭቆ ውሀ ውስጥ በጥዋት መጠጣት አይነ ምድርን ለማቅጠን አሊያም ቁርጠትን ለማስወገድ ይረዳል።
▪️እንዲሁም የጣዝማ ማር እኛ ጋር ታገኛላችሁ።በብዛትም እናስረክባለን።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት ያለው ህንፃ ንግድ ባንክ ያለበት አንደኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna
Tiktok: https://www.tiktok.com/@st.mikael.tradi.medicine?_t=ZM-8xh6Ap1Zfx0&_r=1
YouTube: https://youtube.com/@kidusmikaeltradionalmedicine?si=HqtJJp8jxVlRs8rq