ዝንጅብል ለሆድ ዕቃ
Author: solomon
Date: 2026-01-28
ዝንጅብል ለሆድ ዕቃ
ዝንጅብል ለሆድ ዕቃ ችግሮች
ትኩስ የዝንጅብል ቁራጭ ሎሚ እና ማር በኩል መጠን ደባልቀው ጠዋት በባዶ ሆድ 1 የሾርባ ማንኪያ መመገብ ምግቡን ለማንሸራሸር ፣የምግብ አምሮቶን ከፍ ለማድረግ ፣የደም ዝውውርን ለማቀላጠፍ ይረዳል ።አንድ የሻይ ማንኪያ ትኩስ የዝንጅብል ልቁጥ ለምለም የድንብላል ቅጠሎች ወይም ጥቂት የቆንዶ በርበሬ ዱቄትን ከምግብ በፊት (30 ደቂቃ )ቀደም ብሎ በአንድ ብርጭቆ ውሀ በጥብጦ መጠጣቱን የምግብ አለመፈጨትን ችግር ያስወግዳል ። 6 ግራም ትኩስ የዝንጅብል ፍሬ የገደል ጨው ጋር ለተከታታይ 10 ቀናት ከምግብ በፊት አኝከው ይዋጡ።በሆድ ዕቃ ውስጥ የሚከማች አየርን ለማሶገድ ይጠቅማል።
የምግብ አለመፈጨት ችግር ካለቦዋ ምግብ ላይ ጥቂት የዝንጅብል ዱቄት በመነስነስ የመገቡ ወይም አንድ ራስ በደቃቁ የተከተፈ ዝንጅብል በቂቤ ጠብሰው መጠነኛ ጨው ከጨመሩበት በሀላ በቀን ሁለት ጊዜ በመመገብ ቁንጣንን ማራቅ ይቻላል። ከዝንጅብል የተፈላ ወተትን ለመጠጣት በሆድ ዕቃ ውስጥ አየርንና የአንጀት ችግሮችን ለመፋለም ይቻላል። አንድ ሻይ ማንኪያ የተላጠ ዝንጅብል በአንድ ብርጭቆ ውሃ በጥብጦ ጥዋት መጠጣት አይነ ምድርን ለማቅጠን ወይም ቁርጠትን ለማስወገድ ይረዳል።
▪️እንዲሁም የጣዝማ ማር እኛ ጋር ታገኛላችሁ።በብዛትም እናስረክባለን።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት ያለው ህንፃ ንግድ ባንክ ያለበት አንደኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna
Tiktok: https://www.tiktok.com/@st.mikael.tradi.medicine?_t=ZM-8xh6Ap1Zfx0&_r=1
YouTube: https://youtube.com/@kidusmikaeltradionalmedicine?si=HqtJJp8jxVlRs8rq