የአጥንት ህመም
Author: solomon
Date: 2025-12-12
የአጥንት ህመም
አጥንት በሰውነታችን ውስጥ በጣም ጠቃሚ ከሆኑት ክፍሎች አንዱ ነው።
የሰውነታችን ቅርፅ ተጠብቆ እንዲቆይ ከማድረጉ በተጨማሪ ጡንቻዎቻችን ባሉበት ተጠብቀው የሚቆዩት አጥንቶቻችን ላይ ተሰካክተው ስለሚገኙ ነው።አጥንት ላይ የሚከሰት ህመም ያን ያህል የተለመደ አይደለም አጥንታችን ላይ ህመም ካጋጠምን ግን ጉዳዩ እንዲሁ በቸልታ የሚታለፍ ስላልሆነ በቶሎ ወደ ሀኪም ቤት በመሄድ አስፈላጊውን ምርምራ እና ህክምና መከታተል ያስፈልገናል።የአጥንት ህመም የሚያስከትሉ ህመሞች እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ።
-አጥንት ላይ የተከሰተ አደጋ(መውደቅ፣ግጭት፣ስብራት)
-የአጥንት መቦርቦር
ይሄ ብዙ ጊዜ ሚከሰተው በእድሜ በገፉ ሰዎች ላይ ነው።
-የሪኬትስ በሽታ(በህፃናት ላይ የሚከሰት አጥንትን የሚያቆለምም በሽታ)
-የአጥንት ብግነት
-የደም(ነጭ የደም ሴሎች)ካንሰር፣የአጥንት ካንሰር፣ከሌላ የሰውነታችን ክፍል ወደ አጥንታችን የተሰራጨ ካንሰር
የፓለታይሮይድ ሆርሞን መብዛት
የአጥንት ህመም ሲከሰት ምን ማረግ ይኖርብናል?
ምንጩ ያልታወቀ የጥንት ህመም ካጋጠሞትና ህመሙ ከጥቂት ቀናት በላይ ከዘለቀ በቶሎ ወደ ሀኪም ቤት በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ ህክምና ያድርጉ።
የተሰበረ አጥንትማሸት ወይም ማሳሸት ጉዳቱ እንዲባባስ ስብራቱ በቶሎ እዳይድን እና የደም ስሮች፣የነርቭ ስሮች ላይ ከባድ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።
የአጥንት ህመም እንዳይከሰት እንዴት መከላከል እንችላለን።
-አቅምን ያገናዘበ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
-እንደወደቅን ወይም ከባድ ግጭት እንዳአጋጠመን ጥንቃቄ ማድረግ(በተለይ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
ህፃናት የሪኬትስ በሽታ እንደያዛቸው የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ ይረዳል።
-ለህፃናት እንደ አሳ ዘይት ያሉ በቫይታሚን ዲ የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
-ህፃናትን በየቀኑ ጠዋት ላይ የፀሀይ ብርሀን ከ20-30 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ እንዲያገኙ ማድረግ
-እንደ ወተት ያሉ በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን አዘውትረው መጠቀም።
▪️እንዲሁም የጣዝማ ማር እኛ ጋር ታገኛላችሁ።በብዛትም እናስረክባለን።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት ያለው ህንፃ ንግድ ባንክ ያለበት ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna
Tiktok: https://www.tiktok.com/@st.mikael.tradi.medicine?_t=ZM-8xh6Ap1Zfx0&_r=1
YouTube: https://youtube.com/@kidusmikaeltradionalmedicine?si=HqtJJp8jxVlRs8rq