አሪቲ ሜሲያ አንዋ
Author: solomon
Date: 2025-04-16
አሪቲ ሜሲያ አንዋ
አርቲ ሜሲያ በጣም ብዙ ዝርያ ያለው ሲሆን አሪቲ ሜሲያ አንዋ ይህንን አይነት በአዲስ አበባ ውስጥ በጥቂት ቦታ ማግኘት ይቻላል። በጣም ጥሩ የሆነ መኣዛ አለው ደጋ ወይም ወይና ደጋ እርጥበት ባለው ቦታ ላይ ግንጣዩን በመትከል ማልማት ይቻላል። እሩቅ ቦታ ወስዶ ለመትከል ከተፈለገ ግንጣዩን በፕላስቲክ ከረጢት ውስጥ አስቀድሞ መትከል እና ከፀደቀ በሗላ ማጏጏዝ ነው ከሚፈለገው ቦታ ከደረሰ መሬቱን በደንብ አለስልሶ ላስቲኩን በጥንቃቄ አንስቶ መትከል ነው ብዙ ቀናት መንገድ ላይ የሚቆይ ና በአንድ ቀን የሚተከል ከሆነ ግንጣዩን ወረቀት ወይም ጋዜጣ በውሃ አርሶ በመጠቅለል እና በማጏጏዝ ቀላል ዘዴ ነው ቅጠሉን በጥላ እና ነፈሻማ ቦታ አድርቆ በሸክላ ወይም ጠርሙስ አሽጐ ማስቀመጥ ለብዙ ጊዜ የማቆያ ዘዴ ነው።
የአርቲሜሲያ አጉዋ ቅጠልን በመዘፍዘፍ በሻይ መልክ ማዘጋጀት ነው የደረቀውን ወይም እርጥቡን ቅጠል ለአዋቂዎች አንድ ሻይ ማንኪያ ለህፃናት ግማሽ
የሻይ ማንኪያ በአንድ ኩባያ የፈላ ውሃ ውስጥ ለአስራ አምስት ደቂቃ መዘፍዘፍና መጠጣት ነው።ይህ አጠቃቀም የሆድ ውስጥ ጥገኛ ትላትሎችን ያስወግዳል ሐሞት ከጉበት እና ጣፊያ በቀላሉ እንዲላቀት ይረዳል የወር አበባ ፍሰት ያስተካክላል ትኩስት ይቀንሳል የአባሉ አካላት ስራ ይፈጥናል ለመተንፈሻ አካል ህመም እንዲሁም እንዲሁም ለአስም ማስታገሻ ይሆናል እንደ በሽታው አይነት በቀን ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ መጠጣት ነው ምሬት የለው ቢሆንም ቃናው ጥሩ ነው ለአንድ ሳምንት በተከታታይ መጠቀም ይቻላል ነገር ግን በአንድ ሳምንት በላይ በተከታታይ መውሰድ አይገባም ከመጠን በላይ የተወሰደ እንደሆነ የጐንዮሽ ጉዳት ሊያስከተል ይችላል።
አርቲሜሲያ የሚዘጋጅበት እቃ ብረት ሳይሆን ሸክላ መሆን አለበት ለማንኛውም አይነት በሽታ ቢሆን ነፍሰጡር እናቶች አርቴሜሲያን ለመድሀኒትነት ፈፅሞ መወሰድ የለባቸውም።
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
▪️እንዲሁም የጣዝማ ማር እኛ ጋር ታገኛላችሁ።በብዛትም እናስረክባለን።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት ያለው ህንፃ ንግድ ባንክ ያለበት ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna