የእግር ህመም
Author: solomon
Date: 2025-03-12
የእግር ህመም
እግራችን የሰወሰነታችንን ጠቅላላ ክብደት ተሸካሚ በመሆኑ ሁልግዜም ጫና ይበዛበታል።በተለይም ከፍተኛ የሰውነት ከብደት ያላቸው ሰዎች ክብደታቸው በመገጣጠሚያዎቻቸው ላይ በሚፈጠረው ተደጋጋሚ ጫና ምክንያት የነርቭ ስርዓታቸው ሰለሚዛባ የእግሮቻቸው ጤና ለጉዳት ይዳረጋል።በዚህ ወቅትም የእግር መደንዘዝና የማቃጠል ስሜት ይፈጥርባቸዋል።ቀለ እያለም ችግሩ ወደከፋ ደረጃ ላይ ደርሶ እንደቀድሞው መራመድ ይሳናቸዋል።እንዲህ ያለው ሁኔታ በስፋት የሚታየው እድሜያቸው በገፋ፣ከመጠን ባለፈ የሰውነት ክብደት ባላቸውና ምንም አይነት የሰውነት እንቅስቃሴ በማያደርጉ ሰዎች ላይ ነው።የእግር _ ህመም _ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ሲሆን በዕድሜ የገፉ ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ለእግር ህመም የተጋለጡ መሆናቸውን ጥናቶች ይጠቁማሉ።ለበርካታ ሰዎች የእግር ህመም መነሻ ምክንያት ሁነው ከሚጠቀሱት በሽታዎች መካከል ዋንኛው የሪህ በሽታ መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት መረጃ 35% በመቶ ለሚሆነው ለእግር ህመም መነሻ ምክንያት እንደሆነ ይገለፃል።ካልስየም የተባለው ንጥረነገር በሰውነታችን ውስጥ በማከማቸት ካልስየም ፎስፌት ወደተባለ ጠንካራ ንጥረነገር ተለውጦ በመገጣጠሚያዎቻችን አካባቢ በብዛት በመጠራቀሙ ሳቢያ የሚከሰተው የሪህ በሽታ በሴቶችም ሆነ በወንዶች ላይ የሚታይ ቢሆንም ወንዶች በበሽታው የበለጠ እንዲጠቁና በወጣትነት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎችንም በስፋት በማጥቃት ለእግር ህመም እንደሚዳርግ መረጃው ይጠቁማል።በቀጣይነት ለእግር ህመም መነሻ ተብሎ የሚጠቀሰው የኩላሊት በሽታ ነው።በኩላሊቶቻችን ላይ በሚደርሱ የጤና ችግሮች ሳቢያ ኩላሊት መደበኛ ተግባሩን ማከናወን ሲሳነው ሽንት ከሰውነታችን ውስጥ ማስወገድ ያቅተዋል።በዚህ ወቅትም በእግራችንና በመላ ሰውነታችን ላይ እብጠት ይከሰትና መራመድ ያዳግተናል።በነርቭ ስርዓታችን ላይ መሰናከል የሚፈጥሩ ነገሮች በሚያጋጥሙን ጊዜም ችግሩ በእግሮቻችን ላይ መዛልን በማስከተል እንደልባችን ለመንቀሳቀስ እንዳንችል ያደርገናል።ይህም በአብዛኛው የሚፈጠረው በአከርካሪያችን ላይ የሚያልፈው ነርቭ በተለያዩ ችግሮች ምከንያት ሲጎዳ ነው።ለነርቭ ስርዓታችን መዛባት በምክንያትነት ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል የደም ቧንቧ መታወከ ፣የዲስከ መንሸራተት እና በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ አደጋዎች እንዲሁም ኢንፌክሽኖች ይገኙበታል።አብዛኛውን የታዳጊ አገራት ህዝቦችን የሚያጠቃው ኢንፌክሽን የአከርካሪ አጥንት ቲቢ ሲሆን ይህ የጤና ችግር በአከርካሪ አጥንታችን ላይ ሲከሰት ህከምና በፍጥነት ማግኘት ይገባል።ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን አንዱን አልያም ሁለቱንም እግሮቻችን ሊያዝላቸው ወይም ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሊያደርጋቸው ይችላል።ከዚህ በተጨማሪም በአከርካሪ አጥንታችን ንብርብሮች ላይ በሚፈጠሩ እጢዎች ሳቢያ በነርቮቻችን ላይ ጫናና የስራ መስተጓጎል ሲፈጠር ሂደቱ ከተስተጓጎለበት የነርቫችን ከፍል በታች ያለው እግራችን ጤናው በእጅጉ ይቃወሳል፡፡
በጭንቅላታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ዕጢዎች ኢንፌከሽኖችንና ፈንገሶች እንዲሁም በጭንቅላት ውሰጥ የፈሳሽ መጠን መብዛትና የደም ዝውውር መዛባት፣የነርቭ ስርዓታችንን በማቃወስ በእግሮቻችንን ላይ የጤና ችግር ያስከትላል።የእግሮቻችን ጤና ከደም ዝውውርና ከነርቭ ሰርዓት መታወክ እንዲሁም ኩላሊትና ልብን ጨምሮ ከሌሎች የውስጥ ደዌ በሽታዎችና ከአደጋ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ሊታወክና እንደልብ ከመንቀሳቀለ ሊያግደን ይችላል፡፡
የእግራችን ጤና በታወከ ጊዜ በተለያዩ መንገዶች በሚሰጥ ህከምና ልንድን እንችላለን።አንዳንድ ጊዜ ግን መዳን _ የማይችሉና ታማሚውን እስከ ዕድሜ ፍፃሜው ድረስ ህመምተኛ የሚያደርጉ የእግር ህመም አይነቶች አሉ፡፡ለእግር ህመም የሚሰጡት የህክምና አይነቶች ከቀላል የነርቭ ህክምና እስከ ቀዶ ህክምና ድረስ የሚዘልቁ ሲሆን በደም ዝውውር መዘጋት ሳቢያ የተከሰተ የእግር ህመም የተዘጋውን የደም ዝውውር በመክፈት የታማሚውን ጤና ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚያሰችል የህክምና ዘዴ አለ።የእግር ህመም ከመከሰቱ በፊት በእነዚህ መንገዶች መከላከል ይቻላል፦
*የሰውነት ክብደትን መቀነስ
*ቀለል ያሉና ምቾት የሚሰጡ ጫማዎችን መጠቀም
*የኩላሊት ፣የጉበት፣የልብና የደም ግፊት በሽታዎችን በወቅቱ መታከም ዋንኛዎቹ የእግራችንን ጤና መጠበቂያ መንገዶች ናቸው።
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna