ጉበት

ጉበት መርዛማ ንጥረ ነገሮች በደም አማካኝነት ወደ ተለያዩ የሠውነታችን ክፍሎች ውስጥ ዘልቀዉ ገብተው ጤናችን አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በርቱ ተጋድሎ የሚያደርግ የሠውነታችን ክፍል ነው።በምንመገባቸው ምግቦችና መጠጦች እንዲሁም ለተለያዩ በሽታዎች ማከሚያነት በምንወስዳቸው መድሃኒቶች ውስጥ የሚገኙና ለሠውነታችን አላሰፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ሁሉ በጉበት _ አማካኝነት እየተመረጡ እንዲወገዱ ይደረጋል፡፡ቀይ የደም ሴሎቻችን የአገልግሎት ዘመናቸውን ሲያጠናቅቁ የሚወገዱትም በዚሁ በጉበታችን አማካኝነት ነው።ከዚህ በተጨማሪም ጉበታችን ፋቲ አሲድ ፣ፕሮቲን፣ጉሉኮስና በሽታን ለመከላከል የሚያሰችሉ ንጥረ ነገሮችን እያመረተ ለሠውነታችን ክፍሎች እንዲዳረሱ ያደርጋል።የዚህ የሰውነታችን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ሰጪ የሆነው የሰውነታችን ክፍል በህመም መጠቃት በሰውነታችን ስርዓት _ ዑደት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል።ጉበትን በእጅጉ በመጉዳት ከሚታወቁ ነገሮች መካከል የመጠጥ አልኮል ዋንኛው ነው።በአልኮል ሳቢያ የሚከሰተው የጉበት ስብ በሽታ በርካቶቹን ለሞት እየዳረገ እንደሚገኝ የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡አልኮል አመጣሽ በሆነው የጉበት ሰብ በሽታ የተጠቁ ሰዎች አምስት አመት በህይዎት የመቆየት ዕድላቸው 50% በመቶ ብቻ ነው።በሽታው የጉበትን የመስራት አቅም በፍጥነት የሚያዳክምና ከአገልግሎት ውጪ የሚያደርግ በመሆኑ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ለህልፈተ የሚዳርጋቸው እድል ከፍተኛ ነው።በሽታው ምንም አይነት ምልክቶችን ሳያሳይ ሊቆይ እንደሚችል ከ75% በላይ የሚሆኑት የጉበት ስብ ህሙማን በበሽታው የመያዛቸውን ምልከት የሚያሳዩት ጉበታቸው የመጨረሻ ደረጃ ላይ ሲደርስና ውሃ መያዝ ሲያቅተው ነው፡፡የበሽታው ስርጭት በአገራችን በተለይ ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑና አልኮል አዘውታሪ ሰዎች በበሽታው የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ እንደሆነና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው ህፃናትም ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው፡፡የጉበትን ጤና በማቃወስ ከሚታወቁት ነገሮች መካከል አንዱና ዋነኛው በሆነው ስብ የተጠቃ ጉበት ለጉበት ስብ በሽታ የሚያጋልጥ ሲሆን ይህም በሁለት ምክንያቶች የሚከሰትና ጉበትን ወደ ቃጫነት በመለወጥ ከጥቅም ውጭ የሚያደርግ በሽታ ነው።የጉበት ስብ በሽታ ከሚከሰትባቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው የአልኮል መጠጥ ሲሆን ሌላው ከአልኮል ውጪ በሆኑ ሌሎች ምክንያቶች ማለትም ለተለያዩ በሽታዎች ማከሚያነት የምንወስዳቸው መድሃኒቶች እንዲሁም የስኳር በሽታ፣ውፍረት፣ጉሉኮስ የማከማቸት ችግር፣ኮፐርናዚንክ የተባሉ ማዕድናትን ሰውነት ውስጥ ማከማቸት ለጉበት ስብ በሽታ መነሻ ምክንያት ሁነው ይጠቀሳሉ፡፡የአልኮል መጠጦች በጉበት ስብ በሽታ ለመጠቃት 40 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል።የአልኮል መጠጦች ለጉበት ስብ በሽታ መነሻ የሚሆንባቸውን መንገዶች የአልኮል መጠጦችን በምንጠጣበት ጊዜ በአልኮሉ ውስጥ የሚገኙና ለሠውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች ጥቅም ላይ ከዋሉ በኋለ ቅሪቱ ንጥረ ነገር በጉበታችን ውስጥ ያልፋል።በዚህ ጊዜም የጉበታችን ሴሎች ጉዳት ይደርስባቸዋል።ይህ ደግሞ ጉበታችን በአግባቡ ስራውን እንዳያከናውን ያደርገዋል።ጉበታችን በአግባቡ ስራውን ማከናወን ሲሳነው ወደሠውነታችን የጉበትና በጉበት አማካኝነት መጣራት የሚገባቸው ንጥረ ነገሮች በሰውነታችን ውስጥ ዝም ብለው ይከማቻሉ።በዚህ ጊዜም ጉበታችን ከመጠን በላይ በሆኑ ስቦች እንዲጨናነቅ ያደርጋል።ይህ ሁኔታ ደግሞ የጉበታችንን ሴሎች ወደ ቃጫነት በመቀየር ጉበታችን ስብን ማመንጨትና መጠቀም እንዳይችል እንዲሁም ውሃ መያዝም እንዲያቅተው ያደርገዋል።ጉበት ሲታመም ፈሳሽ የሚቋጥር አቅሙን ያጣል።ይህም ፈሳሽ በሆዳችን ውስጥ እንዲጠራቀም በማድረግ ሆዳችንን ያሳብጠዋል።መጣራት ሲኖርባቸው ሳይጣሩ ቀርተው በሰውነታችን ውስጥ የተጠራቀሙት መርዛማ ንጥረ ነገሮች በደም አማካኝነት ወደ ጭንቅላታችን ውስጥ ገብተው ያስቱናል።በተጨማሪም ራሳችንን ግልኮስ፣ፋትና በሽታን የሚከላከሉ ንጥረ ነገሮች በሰውነታችን ውስጥ መመረታቸው መከማቸታቸውና በጥቅም ላይ መዋላቸው ያቆማል።ከአልኮል ውጪ የጉበት ስብ በሽታን ከሚያስከትሉ ነገሮች መካከል የሚጠቀሰው ለተለያዩ ህመሞች የምንወስዳቸው የተለያዩ ይዘቶች ያሏቸው መድሃኒቶች ናቸው፡፡በተለይ ቴትራሳይክሊን ፣የደም ብዛት መድሃኒቶች፣ለካንሰር _ ህሙማን የሚታዘዙ መድሃኒቶችና ሆርሞኖች አብዛኛውን ጊዜ ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር መድሃኒቶች ተደራርበው እንዳይወሰዱ ለማድረግ የሚሞከረው በመድሃኒቶች ሳቢያ የሚከሰቱ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ለመቀነስ በማሰብ ነው፡፡የጉበት ስብ በሽታ ምንም ዓይነት ምልክቶችን ሳያሳይ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚደርሰው ጉበቱን ከጥቅም ውጭ ከሆነና ለመዳን እጅግ አስቸጋሪ በሚሆንበት ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ነው።አንዳንድ የጉበት ስብ በሽታ ህሙማን የእግር ማበጥ ፣የአይን ቢጫ መሆን፣በቀኝ ጎን በኩል የህመም ስሜቶች መኖር ሊያጋጥማቸው እንደሚችልም ጥናቶች ያሳያሉ።በሽታው ስር ያልሰደደ ከሆነና ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ከመሆኑ በፊት ከተደረሰበት በተለያዩ ቫይታሚኖችና መድሃኒቶች በሽታውን አክሞ ማዳን ይቻላል ነገር ግን ከጥቅም ውጭ ለሆነ ጉበት የሚሰጥ ህክምና በአገራችን አይሰጥም፡፡አልኮልን አዘውትሮ አለመጠጣት፣መድሃኒቶችን አብዝቶ አለመጠቀም፣በአመጋገብ ላይ ጥንቃቄ ማድረግና የአካል በቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የጉበት ስብ በሽታን ለመከላከል ይረዳሉ፡፡

የጉበት ስብ በሽታ መንስኤዎች፦
*የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መጠቀም
*በደም ውስጥ ያለ የስብ መጠን ከፍተኛ መሆን
*የስኳር ህመም
*በዘር ውስጥ የጉበት በሽታ ተጠቂ መኖር
*ለሌላ በሽታ የሚወሰዱ መድሃኒቶች መብዛት
*ከሃኪም ትዕዛዝ ውጭ እና ከተገቢው በላይ መጠኑ ከፍ ያለ መድሃኒት መውሰድ ለምሳሌ የሚወሰድ መድሃኒት፣ ፓራሲታሞል፣ለእርግዝና
*ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል መጠን መኖር
*የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መኖር
*ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች አብዝቶ መመገብ ናቸው፡፡

የጉበት ስብ በሽታ ምልክቶች፦

1.የምግብ ፍላጎት መቀነስ
2.የክብደት መቀነስ
3.የሆድ አካባቢ ህመም
4.የድካም ስሜት መኖር
5.ማዞርና ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት
6.ማቅለሽለሽ እና ወደ ላይ ማለት
7.በሆድ የላይኛው የቀኝ ከፍል ከፍተኛ ህመም መኖር ናቸው::

ጉበት በከፍተኛ ደረጃ ስትጎዳ እና ቁስለት ሲፈጠር፦

1.በሆድ አካባቢ በፈሳሽ መሞላት እና እብጠት መኖር
2.የቆዳና የዓይን አካባቢ ወደ ቢጫነት መቀየር
3.በቀላሉ መድማት
4.ራስ መሳት የሚከሰቱ ምልክቶች ናቸው፡፡

የጉበት በሽታ መከላከያ ዘዴዎች የሚከተሉት ናቸው፦

*ከሃኪም ትዕዛዝ ውጪ መድሃኒት አለመውሰድ
*የአልኮል መጠጥ አብዝቶ አለመጠቀም
*የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
*ቅባትነት ያላቸውን ምግብ አለመመገብ ሲሆኑ የጉበት ስብ በሽታ ከተከሰተ ግን በቤት ውስጥ በሚከተለው መንገድ ማከም ይቻላል።

1.የፖም አቸቶን መጠቀም(Apple cider Vinegar)
2.የሎሚ ጭማቂን በቀን ከ2-3 ጊዜ መጠጣት
3.በቀን ከ3-4 አርንጓዴ ሻይ መጠጣት
4.ግማሽ የሻይ ስኒ እርድ ከግማሽ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሃ ጋር በማዋህድ በቀን ሁለት ጊዜ መጠጣት
5.መጨናነቅን ማቆም
6.ፓፓያን መመገብ
7.በቀን ከ8-10 ብርጭቆ ንፁህ ውሃ መጠጣት
8.አትክልትና ፍራፍሬን አዘውትሮ መመገብ
9.በቂ እረፍት ማድረግ
10.የሠውነት ክብደትን መቆጣጠር
11.በየጊዜው ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ክትትል ማድረግ ናቸው፡፡

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna