ወይባ ጢስ
Author: solomon
Date: 2025-03-05
ወይባ ጢስ
የወይባ ጢስ ጥሩ ገፅታ እና መልካም ጠረን እንዲኖረን ያስችላል ተብሎ ስለሚታሰብ አዘውትረው የሚታጠኑ በርካቶች ናቸው፡፡ሰውነትን በተለይም ወገብና ማህፀንን ለማጠንከር እንደሚረዳ ይነገራል።በወር አበባ ወቅት ህመምን ለመቀነስ እና መሃኖች መውለድ እንዲችሉ ለማድረግም የወይባ ጢስ አገልግሎት ይውላል።ያላገባች ሴት የወይባ ጢስ የምትገባው አምራ ለመታየትና ትዳር ለማግኘትም ነው፡፡የታጨችው ሴት ደግሞ ውበቷን ለማጉላት ትጠቀምበታለች።የወለዱ እናቶች ሰውነታቸው እንዲጠነክር ከወለዱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ጢስ ይገባሉ፡፡አግብታ የፊታችን ሴት ጢስ ስትገባ በትግረኛ"ዕጣን ግብኣ"እየተባለ ይነገርላታል።ቀትር ላይ ፀሐዩ ሠውነት እንደሚጎዳ ስለሚታመን የወይባ ጢስ መታጠን የሚጀመረው ምሽት አካባቢ ነው።ከታጠኑ በኋላ ሰውነታቸው እንዲቀዘቅዝ ለጥቂት ደቂቃዎች ከቤት አይወጡም።የታጨች ሴት አንዴ ታጥና ትወጣለች። የወለደች ሴት ግን እየገባችና እየወጣች ታጠናለች።ቅቤ እናቷ ላይ ይደረግላታል።ገንፎና ወተትም ይሰጣታል።ከግማሽ ሰዓት ጀምሮ ረዘም ላለ ጊዜ መታጠን ይቻላል።የሚታጠኑበት እንጨት የሚገባው ከከብት አዳሪ በሚሰራ ጎድጎድ ያለ ቦታ ነው።ከጉድጓዱ በላይ ሴቲቷ በምትታጠንበት ወቅት የምትለብሰው ሽማ የሚያርፍበት ከፍታ አለ።ሽማ ጢሱ እንዳይወጣ አፍኖ የሚይዝ ወፍራም ጨርቅ ነው። ከሸማው በላይ ደግሞ ከከብት ቆዳ የተሰራ ቁርበት ይለብሳል።አንድ ሴት ከመታጠኗ በፊት መላ ሰውነቷን ቅቤ ከተቀባች በኋላ ልብሷን አውልቃ ሸማና ቁርበት ደራርባ ጉድጓድ ባለው ቦታ ትቀመጣለች።ቅቤው ጢሱ ሰውነቷን እንዳይጎዳው ይከላከልላታል፡፡
በዕድሜ ከፍ ያሉና ልምዱ ያላቸው ሴቶች ረዘም ላለ ጊዜ ይታጠናሉ፡፡ገጠር አካባቢ በብዙዎች መኖርያ ቤት የወይባ ጢስ ያለ ሲሆን ከተማ ውስጥ ለወለደች ሴት ብቻ የሚያዘጋጁትም አሉ።በአካባቢው አንዲት ሴት በተደጋጋሚ ጢስ መግባቷ ጥንካሬዋንም ያሳያል።ወይባ ጢስ ለመገጣጠሚያ ጥንካሬ በተለይም ለማህፀን ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጥ ይነገራል።ሴቶች ከጢሱ በተጨማሪ እንሶስላ ይሞቃሉ፡፡ያልታጨች ሴት ደግሞ እጇን ብቻ ትቀባለች፡፡በአንፃሩ ያገባች ሴት እጇንና እግሯንም እንሶስላ ትቀባለች።በአካባቢው ሰዎች የሚተጫጩት በተለያየ ጊዜ ቢሆንም በአዲስ አመትና በጥምቀት በዓል ያመዝናል።ወንዶች የሴቶች ፀጉር ላይ ሳር በመስካት ወይም ሎሚ በመወርወር ፍላጎታቸውን ካሳዩ በኋላ ሽማግሌ ይልካሉ፡።የወይባ ጢስ አገልግሎቱን በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት የሚሰሩ ተቋሞች እየተበራከቱ ነው።ወይባ ጢስን ስቲምና ሳውናን ከመሰሉ በጢስ ኃይል ለውበትና ለጤና እንክብካቤ የሚውሉ መንገዶች ጋር የሚያነፃፅሩም አሉ።ሰለቱሪሰት መስህቦች የሚያትቱ ድረ-ገፆችም የወይባ ጢስን እንደአንድ መስህብም ያስቀምጣሉ።ከእነዚህ አንዱ ኢትዮጵያ ቱሪዝም ቲፕስ ዶት ኮም በተለያዩ አካባቢዎች በባህላዊ መንገድ የሚካሄዱ መዋቢያዎችን በሚል ከሚያሰቀምጣቸው መካከል የወይባ ጢስና ቆቆባ ጡሽ (ጢስ) ይገኝበታል።ከወባ ጢስ ጋር አያይዘው ብዙዎቹ የሚጠቅሷቸው ሳውናና ስቲም ከኢትዮጵያ ውጭም ዓመታትን አስቆጥሯል።ከውበት በተጨማሪ ሠውነትን ለማፍታታትና ለደም ዝውውር ፍቱን መድሃኒት እንደሆኑም ይነገራሉ፡፡
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna