ግራዋ
Author: solomon
Date: 2025-02-28
ግራዋ
የተክሉ ሳይንሳዊ ፀባይ ቁጥቋጥ ወይንም የትንሽ ዛፍ መጠን ሲኖረው እስከ አስር ሜትር ድረስ ሊረዝም ይችላል።ሲያብብ ደግሞ ንቦቹ ይወዱታል።ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተከል ነው፡፡ይህ ተክል በወፍ ዘራሽ መንገድ የሚበቅል ነው፡፡በብዛት የሚበቅልበት መልክዓምድር በተለይ በጠፍ መሬት ፣በደን ዳርቻ እና በአውድማ አጠገብ ሲሆን ቁመቱ ከ1700-3000 ሜትር ከፍታ ድረስ ያድጋል።ይህ ተክል ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የውስጡ ፈሳሽ ለሚያሰቀምጥ በሸታ በመድሃኒትነት ይጠቅማል።ደረቁ አበባም የሆድ ድርቀት ለማከም ሲያገለግል የወባ በሽታን ለማከምም ጥቅም ላይ ውሏል።ቅጠሎቹ አንዳንዴ በጌሾ ፋንታ ጠላን ለመስራትም ይጠቅማል።በእሳት የበሰሉ ቅጠሎችንም እንደምግብ መመገብ ይቻላል።እንግዲህ የግራዋ ተከል ጥቅሙ ዘርፈ ብዙ በመሆኑ ማንኛውም ታካሚ ቤት ውስጥ አዘጋጅቶ ከበሽታው ሊፈወስ ይችላል።ዝግጅቱም፦
1.ቅጠሉን አድቅቆ በውሃ ከበጠበጡ በኋላ ቢጠጡት ለኮሶቮ ትል፣ለወስፋት እና ለሆድ ቁርጠት ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡
2.የቅጠሉን ጭማቂ ብግነት ለአንጓ (እንጥል ሲወርድ)መጠጣትም ከህመሙ ይፈውሳል።
3.እንዲሁም የግራዋ ፣የሰንሰልና የእምቧጮ ቅጠል ጭማቂ ለሆድ ቁርጠት ወይም ለወባ በሽታ ይሰጣል።በመሆኑም ይህ ተከል ለመድሃኒትነት በቤት ውስጥም ይሁን በባለሙያ ተዘጋጅቶ መጠቀም ይቻላል።
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna