ዳማ ካሴ(የምች መድሃኒት)
Author: solomon
Date: 2025-02-24
ዳማ ካሴ(የምች መድሃኒት)
ወደ 85 ሺህ የሚጠጉ እፅዋት ለህከምና አገልግሎት ሊውሉ እንደሚችሉ በሰነድ ደረጃ ተመዝግቦ ይገኛል።ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ዳማ ካሴ ዕፅዋት አንዱ ነው።ዳማ ካሴ አገር በቀል ተክል ሲሆን በሳይንሳዊው ስሙ ኦሲመም ላሚፎለም እየተባለ ይታወቃል።በኦሲመም ስር 150 የሚጠጉ ሌሎች ዘመዳማ ተክሎችም ይገኛሉ።ተከሉ ሁለገብ የሆነ የመድሃኒትነት ባህሪ ያለው ሲሆን ጠቃሚ የሚባሉ የተለያዩ ዘይቶችም በማጠንከር ዘዴ ከተክሉ ይገኛሉ፡፡
ዳማ ካሴ በባህላዊ ህክምና ከተክሉ የሚገኙ ጭማቂ ለተለያዩ የዓይን በሽታዎች ፣ለራስ ምታት፣በተለይ ትኩሳት ሲያጋጥም በብሃላዊው አጠራር "ምች"እየተባለ ለሚጠራው የህመም ምልክት ይወሰዳል።በተጨማሪም ለምለም ቅጠሉ ተጨምቆ ሲጠጣ ለተቅማጥ፣ለአሜባ፣ለሳልና ለሌሎችም ህመሞች ፈውስ ማግኘት ይቻላል።በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ከቆዳ ከአንጀትና ጨጓራ ህመም ጋር ተያያዥነት ላላቸው ህመሞች ይወሰዳል።በጥናትም እንደተረጋገጠው ተከሉ ለተለያዩ ችግሮች አስተማማኝ የሚባል የፈውስ ባህሪ እንደሚያሳይ ነው፡፡ተከሉ የፀረ ወባ ገቢርነት እንዳለውም ይታወቃል።ቅጠሉን ማጨስም የወባ ትንኞችን ከአካባቢ እንደሚያርቅ ታይቷል።
በተጨማሪም ፀረ-ፈንገስና ፀረ ነፍሳት ባህሪ አለው፡፡እንዲሁም ትኩሳትን ያበርዳል።ፀረ ብግነት ፀባይም አለው፡፡በአገራችን ዳማ ካሴ ለረጅም ጊዜያት አገልግሎት ላይ እንደዋለ ይታወቃል።እንዲህ ያሉ ከእፅዋት የሚገኙ መድሃኒቶችን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው ከህመማችን መፈወስ እንችላለን።
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna