ጤና አዳም

በሳይንሳዊ ስሙ ሩታካሌፔንሲስ እየተባለ የሚጠራው ጤናአዳም አገራችንን ጨምሮ በሜዲትራያንና በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢዎች ይበቅላል፡፡ሩታ የሚለው ስም የጥንት የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም እጅግ መራራ ወይም ደስ የማያሰኝ ማለት ነው።የተክሉ መራራነት የመጣው በውስጡ ከሚገኘው ሩቶን ከተባለው ውህድ ነው፡፡በሳይንሳዊው ስሙ ላይ ካሊፔንሲስ የሚለው ስም የተሰጠው ከጥንቷ የሶርያ መንደር ካሌፕ ነው።ከጤናዳም ስር ነጥሮ የሚወጣው የኬሚካል ውህድ አልካሎይድ የሆኑ ክሎሮዶን ሰኪሚያኒን ፣ኩኩሳግኒና ግሬቮሊን ከኩማሪንስ ጋር ሩታልፒኒን ፣ካሌፒን እና ካሌፔንሲን ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የባህል ህክምና ጤናአዳም ለሆድ ህመም ፣ለትቅማጥ፣ለጆሮ፣ለልብ
ህመም፣ለኪንታሮት፣ለኢንፍሎንዛናከአንጀት መታወክ ጋር ለተያያዙ አገልግሎት ላይ ይውላል።የደረቀው ፍሬ ከተፈጨ በኋላ አፈልቶ በመጠጣት ለትቅማጥ ህከምና ሲውል ቅጠሉ ከተከተከተ በኋላ በውሃ ተደርጎ ለህፃናት ሆድ ህመም ይሰጣል።ተክሉ ተድጦ ሲልም ደግሞ ለኪንታሮት በሽታ ይወሰዳል።በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ አገሮች ደግሞ ከተከሉ ተዘፍዝፎ ከሚገኘው ፈሳሽ ለጉንፋን፣ለጆሮ ህመምና ለአንጀት መታወክ ይወሰዳል።

የጤናዳም ሽታ በጣም ጠንካራ በመሆኑ ሰዎች ጊንጦችን ከአካባቢያቸው ለማራቅ ይጠቀሙበታል ።በአልጀሪያ ሰዎች ተከሉ ከተዘፈዘፈ በኋላ የሚገኘውን ፈሳሽ በጠብታ መልክ በአፍንጫቸው ይወስዳሉ።በተለይ ለህፃናት ይህ ህከምና የሚሰጠው ለሚያስመልሰውና ትኩሳት ላለበት ነው በመሆኑም ጤናአዳም እንደ ቀንድ አውጣ፣እስስት አፅቂ ያሉ ነፍሳትን የማራቅ አቅም ስላለው በጓራችን ቢኖር ተመራጭ ነው እንዲሁም ለቁንጫም መድሃኒትም ነው፡፡በጡንቻ ላይ የሚያጋጥም ህመምን ፣ውጥረትና በወር አበባ ወቅት የሚያጋጥም ህመምን የማርገብ ሁኔታ ያለው ሲሆን መጠቀም ያለብን ግን የዕፅዋት ባለሙያን በማማከር መሆን አለበት።በሻይ መልክ መጠቀም ለሽንት ቧንቧ ፣ለአንጀትና በአጠቃላይ ለደንደኔ ኢንፌክሽን መድሃኒት መሆን ይችላል።

ጤናአዳም ለምግብ መመረዝ በተለይ ደግሞ ሳልሞኔላ የተባለውን ባክተሪያና ሌሎች አደገኛ ተዋህስያንን ሊከላከል ይችላል።ከዚህ በተጨማሪ የፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው ልንጠቀመው እንችላለን።ይህ ዕፅ ነርቮችን የማረጋጋት ኀይል ማለትም የአራጌነት ባህሪ እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ በመሆኑም የእንቅልፍ ማጣት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ብንጠቀመው ሊያረጋጋን ይችላል።በአንዳንድ መርዛማ እንሰሳት ለምሳሌ በእባብ ከተነደፍን ማርከሻ የሚሆንበት ሁኔታ ያለ ሲሆን ይኸውም የተነደፈው የነርቭ ስርዓት ላይ እክል በሚፈጥሩ የመርዝ አይነቶች ከሆነ ነው፡፡ከዚህ ባሻገር በአንጓ ላይ የሚያጋጥም ብግነትን ሰከን የማድረግ ኃይል ስላለው ችግሩ ያለበት ሰው አንድ ወይም ሁለት ብርጭቆ በሻይ መልከ ቢጠጣ እፎይታን ያገኛል።የጤናአዳም ዘይት በዘመናዊው ዓለም ለሳሙናዎችና ለኮስሞቲክስ ምርቶች ጥሩ ማዕዛ ጥቅም ላይ ይውላል።ይህ ዘይት መጠኑ ሲበዛ የመርዛማነት ባህሪ ስላለው በቀጥታ በቆዳ ላይ ለጥቅም አይውልም ነገር ግን ተመጥኖ ለቆዳ ቢውል የተለያዩ ጥቅሞችን እንደሚያስገኝ ጥናቶች ያሳያሉ።

የጤና አዳም የጎንዮሽ ጉዳት፦

ከጤና አዳም የሚወጣው ዘይት በሰውነት ላይ በቀጥታ ከተጠቀምን ሰውነታችን ውኃ ሊቋጥር ይችላል።በተለይ ደግሞ ፅንስ ያላቸው እናቶች በከፍተኛ መጠን ከተጠቀሙበት ፅንሳቸውን ሊያስወርድ ይችላል።ይህም በመሆኑ በዘመናዊው ዓለም የጤናአዳም ህክምና የተገደበ እየሆነ መጥቷል።ከጤናአዳም የሚገኘው ዘይት በብዛት ከተወሰደ ውርጃ ሊያሰከትል ይችላል።

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna