የእፅዋት ተዋፅዖ(ክፍል አምስት)

በቆሎ

ጥራጥሬ ከሚባሉት መካከል አንዱ በቆሎ ሲሆን የተለያዩ ሃገራት ለተለያየ አገልግሎት ያውሉታል።የበቆሎ እሸት ስንፈለቅቅ የምናገኘው ሃር መሳይ ነገር ጥቅም ይኑረው አይኑረው አስበነው የምናውቅ አይመስልም።እሸቱን ለመጥበስ ወይም ለመቀቀል ነው እንጅ ለሽፋኑም ሆነ እሸቱን ሸፍነውት ለነበሩት ፀጉር መሳይ ፋይበሮች ትኩረት አንሰጣቸውም፡፡ምንአልባትም ሽፋኑን የተጠበስ አልያም የተቀቀለ የበቆሎ እሸትን ለመያዝ ልንጠቀምበት እንችላለን።ሃርነት መሳዮቹን ነገሮች ግን ከእቁብ የማንቆጥራቸው ብዙዎቹ ነን ይሁን እንጅ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት መረጃዎች ያሳያሉ።

የበቆሎ እሸት ሃር ጥቅሞች የኩላሊት ጠጠርን ይከላከላል በመሆኑም ለዘመናት የኩላሊት ጠጠርን አሰቀድሞ ለመከላከል ጥቅም ላይ ውሏል ።የሽንት አወጋገድ እንዲኖርና በመገጣጠሚያዎች አካባቢ የክርሲታል (ቅንጣቶች)ክምችትን ለመቀነስም ይረዳል፡፡የበቆሎ እሸት ሃርነት የልብ ህሙምን ለመከላከልና ጥቅም የሌለው የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ የሚረዱ ስቲግማስቴሮል እና ሲቶስቴሮል የተሰኙ ንጥረ ነገሮች አሉት።ለኩላሊት ቅድመ መከላከል እንጂ በህመሙ ከተጠቃን በኋላ መፍትሄ አይኖረውም።በቫይታሚን ኬ የበለፀገ በመሆኑ የደም መርጋትን ለመቀነስ በአደጋ ይጠቅማል።በደም ወቅት ከፍተኛ ደም እንዳይፈስ ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይቆጣጠራል።በጣፊያ ላይ የተጎዱ ህዋሳትን መልሰው እንዲያገግሙ የኢንሱሊን መጠንን ከማሳደጉም በላይ የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ይቆጣጠራል።የበቆሎ እሸት ሃር መጠን የኮሊስትሮሊን በመባል በመሆኑም ጤናዎትን በባትላሉ ለማግኘት በቤትዎ ውስጥ እንዲህ ባለመልኩ ማዘጋጀት ይችላሉ። ለመቆጣጠር

1.አንድ ማንኪያ የሚሆን የተፈጨ የበቆሎ እሸት ሃር በአንድ ኩባያ ውሃ ማፍላት።ከፈላ በኋላ ማፍያውን በመከደን (15 ወይም ለ20 ደቂቃ እንዲቀዘቅዝ ማድረግ፡፡

2.ከቀዝቃዛው በኋላ ካስፈለገ አንድ ማንኪያ ማር ጨምረን መጠጣት እንችላለን።የምንጠጣው የበቆሎ እሸት ሃር ሻይ ካለንበት የጤና ሁኔታ እና የሰውነታችን ክብደት አንፃር ሊለያይ ይችላል።ብዙ ጊዜ ለወጣቶች የሚመከረው አንድ ስኒ ሻይ ሁኖ በቀን ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ እንዲወሰድ ነው፡፡ባለሙያዎች የበቆሎ ሃር ሻይን ከመተኛታችን በፊት መውሰድ እንደሌለብን ይመክራሉ።ማንም ሰው ይህን ሻይ የተለያዩ ህመሞችን ለማስታገስ ከመውሰዱ በፊት ሃኪሙን እንዲያማከር ይናገራሉ።ማሳሰቢያ የበቆሎ እሸት ሃር ሻይ ነፍሰጡሮች ባይጠጡ ይመከራሉ፡፡

እንዶድ ቅጠል

የእንዶድ ዛፍ አገር በቀል ከሆኑት ዛፎች መካከል አንዱ ሲሆን ብዙ ጊዜ ወንዝ ዳርን ተከትሎ ይበቅላል።ሳይንስና ቴክኖሎጅ ባልተፈጠረበት ዘመን የገጠሩ ህብረተሰብ የሚለብሰውን ልብስና የጎላውን ንፅህና የሚጠብቀው በእንዶድ ፍሬ ነበር።በአገራችን የጤና ባለሙያዎች በዚህ ዛፍ ላይ ጥልቅ የሆነ ጥናትና ምርምር በማድረግ ለህከምና አገልግሎት ባያውሉትም በባህላዊ መንገድ ግን የገጠሩ ማህበረሰብ ጤናውን እያከመበት ይገኛል።ለአብነት ያከልም፦

1.ስሩ ወይም ቅጠሉ ተደቆ በዉሃ ለቁርባን ወይም ወፍ በሽታ ይጠጣል።የስሩ መረቅ የጨብጥ በሽታ ያክማል።በአንስተኛ መጠን ካልሆነ ግን ሊገድል ይችላል።

2.የወንድ እንዶድ ስር ተደቆ በውሃ የውሻ በሽታን ለማከም ይጠጣል ወይም በጤፍ ቂጣ ይበላል።

3.የእንዶድ ቅጠል ጭማቂ ለእከክ በሽታ መቅባት እንዲሁም ለሆድ ትል ደግሞ መጠጣት ጠቃሚ ነው።

4.የፍሬውም ልጥፍ በቁስል ላይ ይለጠፋል።

በተጨማሪም ፍሬው ተደርቆ ተደቅቆ ለሳሙና መጠቀሙ ጥንታዊ ለማድረግ ነው።ከዚያም አልፎ ተርፎ አሳን በማደንዘዝ ረገድ ጠቀሜታ ስላለው አጥማጆች ጥቅም ላይ አውለውታል።በ1956 ዓ.ም አንድ ኢትዮጵያዊ ሳይንትስት ዶክተር አክሊሉ ለማ ባደረጉት ጥናትና ምርምር የእንዶድ ሳሙና ቀንድ አውጣን እንደሚገድል ለይተው አገኙ ታዲያ የብልሃርዝያ በሽታ በዛጎል ልባስ ስለሚፈጠር የብልሃርዝያ በሽታን በመከላከል እና በማዳን ረገድ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው በግኝታቸው አረጋግጠዋል በመሆኑም ለተሻለ ጥናትና ምርምር ያግዝ ዘንድ የእንዶድ ማዕከል አቋቁመዋል።ሌሎችንም አሰቸጋሪ ቀንድ አውጣዎች ለማጥፋት ስለሚችል እንዶድ በሰሜን አሜሪካ ትኩረትና ንብረት የአእምሮ ጥበቃ አግኝቷል።ከላይ እንደተገለፀው ይህ የዛፍ ተክል ለውሻ በሽታ መድሃኒት እንደሆነ ተነግሯል በመሆኑም ስለእብድ ውሻ በሽታ ታሪካዊ አመጣጥ ማወቅ ተገቢ በመሆኑ እንደሚከተለው ተብራርቷል።

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna