የእፅዋት ተዋፅዖ(ክፍል አራት)

ሙዝ

በኢትዮጵያ እንደተገኘ የሚነገርለትና በዓለማችን በስፋት አየተመረተ በስፋት ለምግብነት የሚውለው ሙዝ እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት።ሙዝ ከምግብ ይዘቱ በተጨማሪ ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስ ሊያስገኙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም አካቶ ይዟል።እነዚህ ንጥረ _ ነገሮች _ ለበርካታ በሽታዎች ፈውስ ከመሆናቸውም በላይ በሽታው ከመከሰቱ በፊት ለመከላከል የሚያስችለንን አቅም ያጎናፅፈናል።

ሙዝ ከፍራፍሬዎች የሚመደብ ሲሆን የሚበቅለውም የአየር ንብረቱ ሞቃት በሆነ ቦታ ነው።ሙዝ በውስጡ የካርቦሃይድሬት ንጥረ _ ነገሮችን የያዘ _ በመሆኑ ከፍተኛ ሃይል እንድናገኝ ይረዳናል።ሁለት ሙዝ በልተን በምናገኘው ሃይል ለዘጠና ደቂቃ አድካሚ የጉልበት ስራዎችን መስራት እንደምንችል ይነገራል።ብዙዎቻችን ሙዝን ለምግብነት በማዋል ለሰውነታችን ሃይልና ሙቀት ለማግኘት እንደምንችል ከማወቅ የዘለለ ነገር አሰብን አናውቅም ነገር ግን ሙዝ በውስጡ የያዛቸው ተፈጥሯዊ የስኳር ወይም የጣፋጭ ምንጭ የሆኑት ግሉኮስ ፣ስክሮስና ፍሩከቶስ የተባሉት ነገሮች ንጥረ ከሙዝ የፋይበር(የቃጫነት)ተፈጥሮ ጋር _ ተዳምረው መጠነ ሰፊ ጠቀሜታዎችን ይሰጣሉ።ከበርካታ የሙዝ ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶችን ከዚህ በታች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።

1.ለአእምሮ ዕድገት ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ ፖታሸየም ንጥረ ነገሮችን ይዟል። ይህም ንጥረ ነገር የአንጎልን የስራ በቃት ለማሻሻል እና ለማሳደግ እንዲሁም ንቁና ጤናማ አእምሮ እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው::

2.ለስትሮክ በሙዝ ውስጥ ያለው ፖታሽየም፣የደም ስርዓትን በማስተካከል ባልታሰበ ሁኔታና በድንገት የሚከሰተውን የስትሮክ ችግር ለመከላከል ያግዛል።ሙዝ በሰው ልጆች የአመጋገብ ስርዓት ውስጥ ተካቶ ዘውትር ለምግብነት የሚውል ከሆነ በስትሮክ ምክንያት የሚመጣውን ድንገተኛ ሞትና የአካል ጉዳት ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡

3.ለደም ግፊት ሙዝ በተፈጥሮው በውስጡ የሚይዘው ዝቅተኛ የጨው መጠን በመሆኑ የደም ግፊትን ለማረጋጋት ይረዳል።ከዚህ በተጨማሪ በውስጡ ያለው ፖታሽየም የደም ግፊትን ለማስተካከልና በግፊት ሳቢያ የሚከሰቱ ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

4.ለጨጓራ ህመም አብዛኛዎቻችን ሙዝ ከበድ ያለ ምግብ እንደሆነ በማሰብ የጨጓራ ህመማችን እንዳያባብስብን ስንናገር እንደመጣለን ይሁን እንጅ ሙዝ ለጨጓራችግሮች ሁነኛ መፍትሄ ነው።በባህሪው በጣም ለስላሳ በመሆኑ በጨጓራ ላይ መጨናነቅን የማይፈጥር ሲሆን የጨጓራ አካባቢን በመሸፈን የጨጓራ ውስጥ አሲድን በማስተካከልና በማመጣጠን የጨጓራ ቁስለት እንዳይፈጠር ለማድረግ ያስችላል።

5.ለድብርት _ ሙዝ በውስጡ የሚይዘውና ትራይፕቶፋን የተባለው ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ሴሮቶኒን የተባለ ሆርሞን እንዲፈጠር ያደርጋል።ይህ ሆርሞን አይነተኛ ተግባሩ ሰውነታችንን ከድካምና ከድብርት በማላቀቅ ወደተሻለ ስሜት ውስጥ እንድንገባ በማድረግ ነው፡፡

ለሆድ ድርቀት፦በሙዝ ውስጥ የሚገኘው ፋይበር ለምግብ መፍጨት _ ስርዓታችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ይሰጣል።የምግብ መፍጨት ስርዓትን የሚያከናውኑት የሰውነታችን ክፍሎች በቂ የውሃ መጠን እንዲኖራቸው በማድረግ ሆድ ድርቀትን ይከላከላል።አንጀት የተለሳለሰ እንዲሆን በማድረግ ከሰውነታችን መውጣት የሚገባቸው የማያስፈልጉ ነገሮች እንዲወገዱ ለማድረግ ይረዳል።

7.ለስኳር ህመም፦ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ የሆነ ቫይታሚን ቢ6 የያዘ ነው፡፡ይህም በደም ውስጥ የሚኖረውን ከፍተኛ የስኳር መጠን እንዲቀንስ በማድረግ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቆጣጡር ያስችለናል።ከስኳር መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የጥዋት ህመም ያስቀራል፡፡

8.ሙዝና የደም ማነስ ፦በሙዝ ውስጥ የሚገኘው የብረት ማዕድን ጠቀሜታው በደማችን ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የሔሞግሎቢን ምርት እንዲኖር _ ማድረግ ነው፡፡ይህም በሆሞግሎቢን እጥረት ሳቢያ የሚከሰተውን የደም ማነስ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡

9.ሙዝ ለስኳር፦ ከወተትና ከማር ጋር ተደባልቆ ለምግብነት ሲውል በከፍተኛ መጠጥ ወይም በስኳር ሳቢያ የሚከሰትን ሃንግኦቨር በቀላሉ ያስወግዳል።በመጠጥ ሳቢያ የተጎዳን ሰውነት እንዲነቃቃና _ ብርታት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድም ሙዝ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል።የሲጋራ እና መሰል ሱሶች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሱሱን ለማቆም እንዲችሉ ሙዝ ከፍተኛ አስተዋፅአ ያደርጋል።

በሞቃታማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ሠዎች ሙዝን ቢመገቡ ሰውነታቸው ሙቀትን እንዲቋቋም በማድረግ የተረጋጋና የተስተካከለ የሰውነት ሙቀት እንዲኖረን ያደርገናል።የሙዝ ተጨማሪ ጠቀሜታዎች በወባ ትንኝ የተነደፈ ሠው ወይም በማንኛውም ተናካሽ ወይም ተናዳፊ ነፍሳት የተነደፈ ሠው በሙዝ ልጣጭ የውስጠኛው ከፍል የተነደፈበትን ቦታ በደንብ በማሸት እብጠቱን መቀነስ ይችላል።ከዚህ በተጨማሪም ንድፊያው የፈጠረበትን የማቃጠልና የመለብለብ ስሜት ለማሰወገድ ይችላል።ጫማዎን _ ከጠረጉና ቆሻሻውን ካስወገዱ በኋላ በሙዝ ልጣጭ ቢወለዉሉት ጫማዎ እንደመስታውት ያበራል።ፍሪጅዎ መጥፎ ሽታ ካመጣብዎ አንድ ሁለት ሙዝ ቢያሰቀምጡበት የፍሪጅዎ ጠረን በቅፅበት ይቀየራል።ሰውነትዎ በድካም ወይም በህመም ከተጎዳ እና የምግብ ፍላጎት ከሌለዎ አንድ ሙዝ እንደምንም ይመገቡ።ወዲያዉኑ ሰውነትዎ ሲበረታና የምግብ ፍላጎትዎ ሲጨምር _ ይታወቅዎታል፡፡በአጠቃላይ ሁላችንም እንደቀላል የምናየውና ብዙም ትኩረት የማናደርግበት ሙዝ ለከፍተኛ የጤና ችግር የሚዳርጉነን በሽታዎች ለመከላከልና ለማሰወገድ ይረዳናል።ታዲያ ይህን የግል ሃኪምዎ የሆነውን ፈዋሽ ፍሬ በፍሪጅ ውስጥ ከተው እያበላሹት።ንፋስ ያለበትና ያልታመቀ አየር ለሙዝ የሚስማማ ነውና በዚያ ያኑሩት፡፡

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna