እፅዋት ተዋፅዖ (ክፍል ሥስት)
Author: solomon
Date: 2025-02-10
እፅዋት ተዋፅዖ (ክፍል ሥስት)
የሎሚ ጥቅሞች
ሎሚ ከፍራፍሬ ምግቦች ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የተለያዩ ጥቅሞች አሉት።ሎሚ ለጤና ጥቅሞች ምክንያት እንዲሆኑ ያደረጉት በውስጡ የተከማቹ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ናቸው።ከእነዚህም ውስጥ እንደ ቫይታሚን ሲ፣ቫይታሚን ቢ6 ፤ቫይታሚን ኤ ፣ቫይታሚን ኢ ፣ፍላቱ ኒያሲን ታያሚን ሪብፍላቪን፣ፓንቶቴኒክ አሲድ
ኮተር፣ካልሲየም፣ማግኒዚየም፣ፖታስየም፣ዚንክ፣ፎስፎረስና ፕሮቲን ይገኛሉ።ሎሚ በውስጡ ፍላቮኖይድ የሚገኝበት የፍራፍሬ አይነት ነው፡፡ይህም አንቲኦክሲዳንት እና ካንሰርን የመዋጋት ባህሪ ያለው ደብልቅ ነው።ከሎሚ የጤና ጥቅሞች መካከል የምግብ መመረዝን ለማከም ፣የምግብ አለመፈጨትን ፣የሆድ ድርቀትን፣የጥርስ ችግሮችን እንዲሁም ትኩሳትን ፣የውስጥ ደም መፍሰስን፣የመገጣጠሚያ ብግነትን፣ሪህን ለመፈወስ፣ውፍረትን ለመቀነስ፣የመተንፈሻ አካልን ችግር ለመቅረፍ፣የደም ግፊትን ለማከም፣የሚረዳ ሲሆን ፀጉርንና ቆዳን ለማከም ይረዳል።ለዘመናትም በመድሃኒትነት ባህሪ የታወቀ ነው።በአጠቃላይ የምግብ መመረዝ እንዲሁም ተቅማጥ ሲያጋጥመዎት ሆዳችን የማፅዳት አቅም ስላለው በጣም ቀላሉ አማራጭ የሎሚ ጭማቂ መጠጣት ነው፡፡
የምግብ ፍላጎት መጨመሪያ ዘዴዎች
ዘውትር ጤናአዳም በባዶ ወይም በቡና መውሰድ የምግብ ፍላጎትን በእጅጉ ይጨምራል።ከጤና አዳም በተጨማሪ የምግብ ፍላጎትን የሚጨምር በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1.ዝንጅብል
2.ሎሚ፣ብርቱካን
3.ኮረሪማ
4.ነጭ ሽንኩርት
5.ፕሮፓዬቲከስ ናቸው
ፕሮፓዬቲከስ ከጤናማ እና ጠቃሚ ባክተሪያዎችና የሊጥ እርሾ የሚቆምም የጨጓራ እና የአንጀት የምግብ መሳለጥ እና መፍጨት እንዲሁም ከጠቃሚ ባክቴሪያዎች የሚሰራ መድሃኒት ነው፡፡ጠቃሚና ጎጅ ባከቴሪያዎች ያሉ ሲሆን ፕሮቫዬቲከ ከጠቃሚ ባከቴሪያ በፋብሪካ የሚዘጋጅ ነው።ጠቃሚ ባከቴሪያዎች ጎጅ ባክቴሪያዎችን ያመከናሉ።ይህም በተለምዶ እሾህን በሾህ እንደሚባለው ማለት ነው፡፡ሚጥሚጣ አዋዜ የምግብ ፍላጎት በአስደናቂ ሁኔታ ይጨምራሉ እንዲሁም የተሰተካከለ የምግብ _ አምሮትን ለመጨመር የሚከተሉት አማራጮችንም ይጠቀሙ።ዘውትር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እስፖርት መሰራት በቂ ቀዝቃዛ ውሃ መውሰድ በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ ከመውሰድ ትንሽ ትንሽ ምግብ አለፍ አለፍ እያሉ ብዙ ጊዜ መጠቀም አነስ ያለ ጣፋጭ ምግብ ቅባት ያልበዛበት በሰአት እየጠበቁ መውሰድ፣ቡና መቀነስ አስፈላጊ ይሆናል።የምግብ ማጣፈጫዎች ጨው፣ዝንጅብልም ፣አዝመሪኖ፣ሎሚ፣ኮረሪማ ደስተኛ በሚሆኑበት ሰአት ይመዝገቡ።ከቤተሰብዎና ከጓደኛዎ ጋር እየተዝናኑ ይመገቡ፡፡መልካም እይታና መአዛ ያላቸው ምግቦች ያዘጋጁ፡፡የጥርሰዎንና የአፍዎን ንፅህና ቶሎ ቶሎ ያስጠብቁ።ከበድ ያለስራ ይስሩ እንዲሁም እንቁላል፣ቅቅል ስጋ፣የድንች ቅቅል፣ቲማቲም፣በአዝመሪኖ የስጋ ጥብስ፣እርጎ በድንብላል ዱቄት በእንጀራ ወይም በሚጥሚጣ፣የጤፍ ጨጨብሳ በወተት፣የምግብ ፍላጎትን የሚጨምር የቤት ውስጥ አማራጮች ናቸው፡፡
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna