የዕፅዋት ተዋፅዖ(ክፍል አንድ)
Author: solomon
Date: 2025-02-04
የዕፅዋት ተዋፅዖ(ክፍል አንድ)
በአገራችን ከተዘወተሩት አባባሎች መካከል ጎመን በጤና የሚለው አንዱ ይሁን እንጅ ጎመን ለጤና የሚለው አባባል እምዛም አይታወቅም።የጎመን ወይም የአረንጓዴ ተከል አይነቶችና የጤና በረከቶቻቸውን በጥቂቱ እናያቸዋለን።ሰላጣን መመገብ ለደም ግፊት ህመምተኞችና ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ላላቸው ሰዎች የሚመከር ሲሆን የደም ውስጥ ሰር መጠንንም ይቀንሳል።ሠላጣ በውስጡ የያዘው ካልስየምና ፎስፎረስ ለአጥንት ጤናማነት ጠቃሚ ሲሆን ሴሊኒየም የሚባለው ንጥረ ነገር ደግሞ የሠውነታችን ቆዳ እንዳያረጅና የአንጀት ካንሰርን የመከላከል አቅም እንዲኖረው ያደርጋል።ከዚህ ጋር ተያይዞም የጀርመን ሰላጣ ሰውነታችን ካንሰር እንዲዋጋ አቅም የሚሰጥ ሲሆን ከዛም ባለፈ ለቡጉር፣ለፀጉር መነቀል እና ሌሎችንም ይከላከላል።
ቆስጣ
ቆሰጣን መመገብ የጉበት፣ የአንጀት፣የማህፀን እና የፕሮሰቴት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን ከነዚህም በተጨማሪ ለጡንቻ መዳበር ጠቃሚነት አለው፡፡ቆስጣ ከቫይታሚን ሲ በተጨማሪ በብዙ አንታይኦክሳይዶችን በርካታ ፕሮቲን የበለፀገ ነው።እነዚህም የሰውነትን በሽታ የመከላከልን አቅምን ይጨምራል።ቆስጣም በውስጡ ያሉትን ንጥረ ነገሮችን እንዳያጣ ብዙ መብሰል የለበትም፡፡
ሱፍ
የሱፍ ተከል ዓመቱን በሙሉ ልናገኘው የምንችለው እና በርካታ የጤና ጥቅሞችን ሊያስገኝልን የሚችል የቅባት እህል ነው::
ብዙዎቻችን በተለይ የሱፍ ፍትፍትን ለብቻውም ሆነ በተለምዶ በየአይነቱ በምንልው የምግብ ዝርዝር ላይ እንደ አይነት ጨምረን እንመገበዋለን።
ይሁንና ሱፍ ከምናስበው በላይ በርካታ ጥቅሞችን ለሰውነታችን እንደሚያበረከትስ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?
እኛም ታዲያ ሱፍ ለጤናችን ከሚያበረክታቸው እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች መካከል የተወሰኑትን ለማየት ወደድን፦
1.ካንሰርን ይከላከላል፣
ሱፍ ሴሊኒየም የተባለው ንጥረነገር መገኛ እንደመሆኑ መጠን የሰውነት ህዋስ (ሴል) ጉዳትን በመከላከል ለካንሰር እንዳንጋለጥ ያግዛል፣
2.ለአጥንት ጥንካሬ፣
ሱፍ ከካልሲየም ውጪ ለአጥንት ጥንካሬ ጠቃሚ የሆኑ ማዕድናትም መገኛ ነው፡፡
ካልስየም፣ ማግንዚየም፣ ኮፐርን የመሳሰሉ ማዕድናትን በውስጡ በመያዙም ለአጥንታችን ጤንነት እና ጥንካሬ ተመራጭ ነው።
በተጨማሪም ሱፍ ቫይታሚን ኢ በውስጡ ስለሚገኝ ከአተነፋፈስ ጋር ለተያያዙ ህመሞች ፍቱንነቱ ይነገርለታል፡፡
3.ጭንቀትን ያስወግዳል፣
በሱፍ ውስጥ የምናገኘው የማግኒዚየም ማዕድን የነርቭ ስርዓትን የማነቃቃት ባህሪ ስላለው በቀላሉ ለጨንቀት እንዲሁም ለከባድ የራስ ምታት እንዳንጋለጥ ያግዛል፡፡
4.ለንፁህ እና አንፀባራቂ ቆዳ፣
በሱፍ ውስጥ በበቂ መጠን የምናገኘው ቫይታሚን ኢ ፥ ዩ ቪ ሬይስ የተሰኘው እና በቆዳ ላይ ጉዳት የሚያደርሰውን የጨረር አይነት በመከላከል እንዲሁም ቆዳችንን በማሳመር ማራኪ ቆዳ እንዲኖረን ያስችላል፡፡
5. በሰውነት ውስጥም ሆነ ውጪ የማቃጠል ስሜትን ለመግታት፣
በሰውነት ውስጥም ሆነ ውጪ የሚከሰትን የማቃጠል ስሜት ለመግታት፣ በመገጣጠሚያ አካላት ላይ የሚደርስ ህመምን ለማስቆም እና ለጨጓራ ህመም መፍትሄው አሁንም ሱፍን አዘውትሮ መመገብ ነው።
6.የልብ ህመምን ለመከላከል፣
በቀን ከግማሽ ኩባያ ያነሰ ሱፍን ከምግብ ገበታችን ዝርዝር ውስጥ በማካተት ጎጂ የኮሌስትሮል መጠንን ከደም ቧንቧችን ላይ እንዲወገድ በማድረግ የልባችን ጤንነት በእጅጉ እንዲጠበቅ ማድረግ እንችላለን፡፡
እርጎ
ማጣፈጫ ያለገባበት እርጎ እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ይነገራል።እርጎ የቫይታሚን ዲ ምንጭ ነው።ቫይታሚን ዲ የሠውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓት በማስተካከል በተፈጥሯዊ መንገድ በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል።
እርድ
ይህ ቅመም የሰውነትን መቆጣት ስለሚቀንስ ለአርትራይትስ በሽታ ለአመታት ሰዎች ሲጠቀሙበት ይታያል።ውጤቱም አስደናቂ ነው።እርድ በውስጡ በከፍተኛ መጠን ኩርኩሚን የተባለ ንጥረ ነገር ይይዛል።ይህም ቀለሙ ቢጫ እንዲሆን እና በእንቅስቃሴ ምክንያት የሚመጣ የጡንቻ ጉዳትን እንደሚቀንስ ይነገራል።በተጨማሪ ንጥረ ነገሩ በጥናት የተረጋገጠ በሸታ ለመከላከል አቅምን የመጨመር እና በቫይረስ የሚመጡ በሽታዎችን ለማቋቋም እንደሚረዳ አሳይተዋል፡፡
አረንጓዴ ሻይ
አረንጓዴ 5 ¡ ጥቁር ሻይ ፍላቮኖይድ በተባለ አንታኦክሲዳንት የሞላ ነው።አረንጓ ሃይለኛ ንጓዴ ሻይ ከጥቁር ሻይ በተሻለ በተጨማሪ ሌሎች የሰውነትን አንታይኦክሳይዶንቶችንም በውስጡ ይይዛል፡፡ይህም በሽታ የመከላከል ስርዓት እንደሚያግዝ
ይነገራል።እንዲሁም አረንጓዴ ሻይ ሊቴኒን የተባለ አሚኖ አሲድ ምንጭ ነው፡፡ይህም ጀርምን ለመዋጋት የሚያስፈልግ ውህደት በመጨመር ሰውነትን እንደሚያግዝ ይነገራል።
ሌላው በቫይታሚን የበለፀገ ሲ ፍራፍሬ ነው።በተጨማሪም ፓፓዬ የምግብ መፍጨት ስርዓትን የሚያሳልጥ እና የሴሎችን መቆጣት የሚቀንስ ውህድ አለው።ፓፓዬ በውስጡ ፖታሽየም ፣ማግኒዢም እና ፎሌት ስለሚይዝ ለጤና እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡
ብሮክሊ
ይህ አትክልት በቫይታሚን ሲ እና በፋይበር የበለፀገ ሲሆን በውስጡ የያዛቸው ንጥረ ነገሮች በሽታን የመከላከል አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡፡የሳንባ እና የካንሰር ህመሞችን የመከላከል አቅም አለው፡፡
ጥቅል ጎመን
የተለያዩ አይነት የጎመን ዝርያዎች ያሉ ሲሆን ሁሉም በቫይታሚን ኤ፣ሲ፣ካልሴም _ _ እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች የበለፀጉ ናቸው።በአውስትራልያ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው እነዚህን አረንጓዴ ተክሎች መመገብ ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል።
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna