ስለ ቡዳ እና ሰለአይነ ሰብ ስለ አይነ ጥላ ስለ ሾተላይ

1ኛ ቡዳ ማለት ለምሳሌ አንድ ትኩስ ወጣት ጉበዝ አንዲት ቆንጆ ሴት በአይኑ አይቶ ሁሉመናዋንም በአእምሮው ተመልክቶ በልቡ ውስጥ ይቀርፀታል በህሊናው እየተመላለሰች ስለምትመጣ ከእርስዋ ጋር በምኞት አብሮዋት ይሄዳል እንዲሁ በአይኑ ላይ ክፉ መንፈስ ያደረበት ግለሰብ ለእርሱ ደስ ከሚለው ሰው ላይ አይኑ ያርፈል በዚህም ጊዜ ከአንዱ ወደ አንዱ እንደሚተላለፍ በሽታ እንዲሁም ከሚወደው ላይ ያርፈል
ስለዚህ ቡድሃ ከሚለው ቃል ቡዳ አይነ እኩይ ከሚለው አይነ ሰብ የሰው አይን ተብሏል።

2ተኛ ዓይነ ጥላ ከአስተዳደግ እና ከአደገበት ህዝብ ባህል የተነሣ ደንጋጣ እና አፈራም ከሆነ ዓይነ ጥላ አለው ገርጋሪ አለው እየተባለ ሲነገር እርሱም ነገሩን ሰምቶ በግብር ያውለዋል።

3ተኛ በተለይ አንዲት ሴት በውስጥዋ ችግር ካለባት በምትፀንስበት ጊዜ ከአንድ ወር እስከ ሠስት ወር ድረስ እንዳይረጋ እና እንዳያድግ በጥብጦ ደም የሚያፈስ ነው ወይም አራት ወር ካለፈው በሆድ ውስጥ አጥንት ሆኖ የሚያኖር ነው በዚህ ጊዜ የዋጊኖስ ቅጠል በወተት ቀቅሎ መጠጣት ነው።
ሌላው ሕፃኑ ከተወለደ በሆላ ደህና ማደግ ሲጀምር ደንገት የታመመ መሰቃየት ይጀምራል፣ይህ ችግር እናቱ ከመውደዱዋ የተነሳ ስታየው ይደነግጣል ስታቅፈው ይጨነቃል የእናቱን ጠረን ይጠላልና ይሞታል ለዚህ አይነቱ ወላጅ እናቱ ብዙ ግዜ ማቀፍ ፣መሳም ፣አተኩሮ ማየት በእጅዋ መዳበስ የለባትም ለዚህ ስለ ዓይነ ስብና ቡዳ

1ኛ የጂባራ ቅርፊት የእፅመናሄ ቅርፊት የግመሮ የግዜዋ የታሪግጣ ስራቸው ወቅጦ ማጠን ወይም መታጠን

2ኛ ሰለዓይነ ጥላ
የግዜዋ ስር የጤና አዳም የምስርች ቅጠል ኮረሪማ አብሮ ቀቅሎ በማር መዋጥ

3ተኛ ሰለ ሾተላይ
የማርያም መቀነት፣የግዜዋ ስር ፣የሎሚይ የጡንጅት ተቀጽላቸው ወቅጦ በነጭ ማር ለውሶ ጽንሱ ከተጸነሰ ጀምሮ በየሳምንቱ ወይም በየሁለት ሳምንት ግማሽ ማንኪያ መዋጥ ነው።

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna