ንዴት
Author: solomon
Date: 2025-01-29
ንዴት
ልጅዎ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ቁጣ ወይም ከሌሎች ጋር ዘውትር የመጋጨትና የመጨቃጨቅ ልማድ አለባቸውን? በመሰረቱ የተለመደና ጤናማ ስሜት ቢሆንም ስር የሰደደ
ንዴት ፣ድንፋታና ከቁጥጥር ውጭው የወጣ ንዴት ግን አደገኛ ውጤት ይኖረዋል።የንዴት ስሜት መጥፎ አይደለም፡፡ በውስን ሁኔታዎ የንዴት ስሜት መስማት ተገቢ ነው፡፡ልዩነቱ ልጅዎ ለንዴት ስሜታቸው የሚሰጡት ምላሽ ነው።ብዙ ጊዜ ንዴት የሌሎች ስሜቶች ሽፋን ነው።ይህም በዋናነት ልጆችዎን ለሚያሰጨንቃቸው ነገር ምላሽ ነው፡፡ልጅዎን ለመርዳት መማር ጠቃሚ ነው ምክንያቱም ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ንዴት የልጅዎን አካላዊ ጤናን ይጎዳል።ንዴት የከፍተኛ ደረጃ ውጥረትና ጭንቀት መንስኤ ነው፡፡በተከታታይ ከፍተኛ ደረጃ ውጥረት ላይ መስራት ለእርስዎ ጤንነት መጥፎ ነው።ስር የሰደደ ንዴት ልጅዎን ለልብ በሽታ ፣ለስኳር በሽታ ፣የመነመነ በሽታን የመቋቋም ስርአት፣የእንቅልፍ ማጣትና ለከፍተኛ የደም ግፊት ሁኔታ ያጋልጣል።ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ንዴት የልጅዎን የአእምሮ ጤና በጊዜ ሂደት ይጎዳል።ስር የሰደደ ንዴት የአእምሮን ከፍተኛ ሐይል መጠን ይወስዳል እናም በልጅዎ አስተሳሰብ ላይ ያጠለሽበታል፡፡ተረጋግቶ ትኩረት ማድረግ፣ትልቁን እድልና ህይወትን ማስደሰት ይሳናቸዋል።ለውጥረት፣ለድብርት እና ለሌላ የአእምሮ ጤና ችግሮች ሊዳርጋቸው ይችላል፡፡
ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ንዴት የልጅዎን የቀለም ትምህርት ስኬት ይፈታተናል ሰለሆነም በመምህራንና በክፍል ጓደኞቹ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ሊያደርስ ይችላል ከዚህ በተጨማሪም ግለኛና ከሌሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ይሸረሽራል።እጅግ በጣም ከሚወዱት ሰው ጋር ባለ የግንኙነት መስመር ላይ የመጨረሻ ጠባሳ ያሳርፋል።ስር የሰደደ ብርቱ ንዴት በሌሎች ለመታመን እነሱን በቅንነት ለማናገር ያውካል ወይም ምቾት አይሰጥም ምክንያቱም ሌሎች ሰዎች እነሱ ምን እንደሚያደርጉ ወይም ምን እያደረጉ እንደሆነ ፈፅሞ ማወቅ ስለማይችሉ ነው::
ንዴትን የመቆጣጠር ክህሎት
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሃሳቦች ንዴትን በተሻለ መንገድ እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል አጋዥ ፍንጮች ናቸው፡፡
1.ንዴት ጤናማ ነው
በተወሰኑ ሁኔታዎች ንዴት ጤናማ እንደሆነ ለህፃን ልጅዎ ያሳውቋቸው፡፡የብቀላ ሰሜት ቢሆንም _ እንኳ ተግባራዊ እስካልተደረገ ድረስ ጤናማ ነው፡፡በንዴት ሌሎችን መጉዳት እና ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ቁጣ ተቀባይነት የለውም፡፡
2.ለጥቂት ደቂቃዎች የእረፍት መንፈስ ወይም አዝናኝ ተግባር እንዲያስቡ ማስተማር
3.የሁከት አጫሪ ተደራሽነታቸውን መወሰን
4.መርዳትና ማበረታታት
ለልጅዎ ሰለፍርሃታቸውና ሰለአሉታዊ ስሜቶቻቸው እንዲያወሩ ማበረታታትና ለመረዳት መሞከር 5.ስጋትዎን ማሳየት
ስለልጅዎ ስሜቶች ያልዎትን ስጋትና እንደሚንከቧ ከቧቸው ማስተማር
6.ድጋፍ መሻት
እነዚህ ምልከቶች በጊዜ ሂደት ከቀጠሉ የአእምሮ ጤና ባለሙያ ማናገር
7.ርጋ ይበሉ
በተናደደ ልጅ ላይ መጮህ ወይም ማንባረቅ ልጆች አደጋ ውስጥ እንደሆኑ የሚሰማቸውን ስሜት ያጠነክርላቸዋል።
8.ልጆች ስሜታዊ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ መርዳት
በሰሜታቸው ደስተኛ የሆኑ ህፃናት ቆጣቸውን በአግባቡ ይቆጣጠሩታል፡፡
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna