የአስም በሽታ

አስም ሳንባችንና የትንፋሽ ቧንቧችንን ለረጅም ጊዜ አጥቅ የሚቆይ የበሽታ አይነት ሲሆን ከመቶ ሰው አምስቱ በበሽታው ይያዛል።

ምልከቶቹ፦

የአስም ምልክቶች ከሚባሉት መካከል ትንፋሽ ማጠር፣የደረት ማጥበቅ፣ሲተነፍሱ ማፏጨት እና ሳል ናቸው፡፡እነዚህ ስሜቶች የሚመነጩት የመተንፈሻ ባንቧችን ሲጠብ ወይም ሲቃጠል ነው፡፡በአንዳንድ ሰዎች ላይ እነዚህ ስሜቶች በቋሚነት ሲከሰቱ ሌሎች ላይ ግን ህመሙ በሚነሳበት ወቅት ብቻ ያጋጥማሉ።አስም _ በየትኛውም የዕድሜ ክልል ሁነን ሊይዘን ይችላል።አስም ያለባቸው ሰዎች ለትንፋሽ ቧንቧ ህመም ተጋላጭ ናቸው፡፡ቤተሰብ ውስጥ አንድ ሰው አስም ካለው ሌሎች ላይ የመኖር እድሉ ከፍ ይላል፡፡የአስም ህመም በቀዝቃዛ አየር ፣ከባድ የአካል እንቅስቃሴ እና በጭንቀት ሊነሳ ይችላል።አለርጅን ተብለው የተጠቃለሉ በአካባቢያችን የሚገኙ የኬሚካል ይዘት ያላቸው ንጥረ ነገሮች ህመሙ እንዲነሳብን ያደርጋሉ፡፡ለምሳሌ ፦ የአበባ ዱቄት፣የእንሰሳት ፀጉር፣አቧራ፣አንዳንድ ምግቦች፣ሽቶ፣የሲጋራ ጭስና የመሳሰሉት ንጥረ ነገሮች አለርጅ ሊሆኑ ይችላሉ።እነዚህ አለርጅኖች የትንፋሽ ባንቧችን እንዲያብጥ እና የቃጠሎ ስሜት እንዲሰማው ያደርጋሉ።የበለጠ አከታር እንድናመነጭ እና የትንፋሽ ቧንቧ ጡንቻ እንዲጠብ ምክንያት ይሆናል።አየር በቀላሉ ማስገባትና ማስወጣት አንችልንም።በዋንኛነት የደረት ኢንፌክሽን ህመም ባለባቸው ላይ ህመሙ ይጠናል ይሁንና አስም በብዙ የጤና ባለሙያዎች እንደከባድ ህመም አይታይም ፡፡የህመሙ ስሜት ከባድ አለመሆኑ እና ህመሙን በቀላሉ መቆጣጠር የሚያሰችሉ ህከምናዎች መብዛት ከባድ ህመም ተብሎ እንዳይፈረጅ ምክንያት ሁኗል ቢሆንም ግን አስም በቂውን ክትትል ካላገኘ ኑሯችንን ያውካል።አብዛኛው ሰው የአስም በሽታን ተቆጣጥሮ መኖር ይችላል ነገር ግን ጥቂት ሰዎች ላይ በሽታው ለህይዎት የሚያሰጋ ሁኖ ይገኛል።በተለይ ደግሞ ህመሙ ሲነሳ ወዲያው ክትትል ካላገኘ ከመከበዱም የተነሳ ሞት ሊያሰከትል ይችላል።

አስም ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል?

የአስም ህመም እየመጣ የሚሄድ ዓይነት ህመም ነው፡፡የሚሰሙን ህመሞች ከጊዜ ጊዜ ይለያያሉ፡፡በብዙ ሰዎች ዘንድ ህመሙ አልፎ አልፎ የሚመጣ ነገር ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ግን በየቀኑ ይታመማሉ።የምናደርገው ህክምና የህመሙን ስሜት በማሰታገስ አንድ የህመም ዙር ለተወሰነ ሰዓት ወይም ደቂቃዎች ብቻ እንዲቆይ ማድረግ ይችላሉ፡፡ያለህክምና ህመሙ ለቀናት የሚቆይበት ሁኔታም አለ።አንዳንድ ልጆች ዕድሚያቸው ሲጨምር ህመሙ ይለቃቸዋል፡፡አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ህመሙ የሚጀምራቸው በተወሰነ የአመት ወቅት ሲሆን ለረጅም አመታት ብቻ ወይም ሙሉ ህይዎታችንን ሊዘልቅብን ይችላል።ታዲያ ለዚህ በሸታ መከላከያው እና መቆጣጠሪያው ዘዴ አስምን የሚያድን ዘዴ ባለመኖሩ ህመሙ ሲከሰት ስሜቱን የሚያስታግሱ መድሃኒቶችና በህመሙ ወቅት ለመተንፈስ የሚረዳ 'ኢንሄለር በመጠቀም የህመሙን ስሜት ማስታግስ እንችላለን።


ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna