የራስ ፀጉር መሳሳት

የራስ ፀጉራችን በየወሩ በአማካኝ 90 በ100 ዕድገት በማንኛውም ጊዜ የሚያከናውንበት ነው ነገር ግን የፀጉራችን ዕድገት 20 በ100 ከማደግ የሚያርፍበት ጊዜ አለው፡፡ይህም በእረፍት ላይ ያለ የፀጉራችን ከፍል ከ2-3 ወራት በላይ ጊዜ ተወግዶ በምትኩ አዲስ ፀጉር ይበቅላል።በዚህ ዑደት በየቀኑ ጥቂት የፀጉር ክፍላችንን ማጣት የተለመደ ነው።ብዙ ሰዎች መጠነ ሠፊ ለሆነው የፀጉር ማጣት ቸግር ይጋለጣሉ።
ለዚህም ብዙ ወንዶች፣ሴቶች እና ሀፃናት በጉዳቱ ሰለባ ይሆናሉ።ፀጉር ማጣት ወይም መነቀል ምክንያቶቹ ብዙ ናቸው፡፡
ለምሳሌ ለ2 ወይም 3 ወራት በቆየ ውስጥ የፀጉር መቀነስ ከፍተኛ ቢሆንም ጊዜያዊ እንጂ ዘለቄታዊ አለመሆኑን የህከምና ባለሙያዎች ይናገራሉ ነገር ግን አመንጪ በሆነው የሆርሞን ችግር ምክንያት የፀጉር መነቀል በታይሮድ ዕጢ ህክምና ሊቃለል ይችላል።የወንድና የሴት ዘር አመንጪ በሆኑት አሰትሮጅን የሚከሰተውን የፀጉር መነቀል ለመከላከል የሁለቱን ዘር አመንጪዎች ሚዛን በህክምና በማስተካከል ችግሩ ሊወገድ ይችላል።ብዙ ሴቶች ልጅ በወልዱ ከ3 ወራት በኋላ የፀጉር መነቀል ተከስቶባቸዋል።ይህን አይነት የፀጉር መነቀል ለመከላከል የሁለቱን ዘር አመንጪዎች ሚዛን በህክምና በማስተካከል ችግሩን ማሰወገድ ከተቻለ የችግሩ መንስኤ ሊሆን የሚችለውን ምክንያት _ ከሆርመን ችግር ጋር የተዛመደ ነው።ከሆርመን ችግር ወጣ ብለን ለፀጉር መነቀል ምክንያት እየሆነ የመጣውን የአካባቢን ብክለት ተከትሎ የከባቢ አየር በመሳሳቱ ወደ ምድር የሚዘልቁ ጎጅ ወርጮች አልትራ ቫዩሊት ወይም በሰለጠነው ዓለም አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ችግር ሁኖ በተደጋጋሚ እየተነገረ ነው፡፡

የሠው ልጅ በተፈጥሮው የሚያበቅላቸው ፀጉሮች እንደሚኖርበት ሃገር እና አየር ጠባይ የተለያየ መሆኑ የሚታወቅ ነው።በተፈጥሮ ፀጉራችንን በተለምዶ ከርዳዳ እና ሉጫ እያልን ለሁለት ብንከፍለውም ፀጉር እንዲበቅል ከሚያደርጉ ሆርሞኖች እንደአየሩ ፀባይ እና እንደቆዳ ቀለጣቅል የተለያዩ ናቸው። በመሆኑም በተፈጠርንበት አካባቢ ከቤተሰባችን ከወረስናቸው ሆርሞኖች ይዘን የተወለድናቸው ፀጉር ላይ ያልተለመደ ጎጅ ጨረር ሲያርፍ የመነቀልና የመለጠጥ ዕድሉ የጎላ ነው።ምንም እንኳ የኮሰሞቲክስ አምራች ካምፓኒዎች ፀጉርን ከተለያዩ አደገኛ ጨረሮች የሚጠብቁ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ቅባቶችና ሎሽኖች እየተመረቱ ለገቢያ ቢያቀርቡም መስፈርታቸው የህዝባቸውን ፍላጎትና የራሳቸውን የአየር ፀባይ መሠረት ያደረጉ በመሆናቸው አጥጋቢ መፍትሄ ሊገኝ አልተቻለም።
ከዚህ ውጪ ለፀጉር መነቀልና መሳሳት ምክንያት እንደሆነ የሚነገረው እርግዝናን ለመከላከል የሚወሰዱ እንክብሎች ሴቶች በተፈጥሮ የሚያመነጩትን ሆርሞኖች እንዲቀይር በማድረግ ወይም በማዛባት ለችግሩ ምክንያት እንደሆነ የእርግዝና ተመራማሪዎች በቅርቡ ያቀረቡት ጥናት ይጠቁማል፡፡

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna