የፀጉር ጤና
Author: solomon
Date: 2025-01-22
የፀጉር ጤና
ለፈጣን የፀጉር እድገት በቤትዎ ውስጥ የሚከተሉትን ዘዴዎች ቢከተሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ዘዴ 1 - ሩዝ ለፀጉር እድገት
2 የቡና ስኒ ሩዝ በ2 ኩባያ ዉኃ ለ5 ደቂቃ ያህል ማፍላት፣
ዉኃዉን አጥልለን ለብ ሲል ፀጉራችንን አዳርሰን በመቀባት ለጥቂት ደቂቃዎች ቆዳችንን ማሳጅ ማድረግ፣
ከ30 እስከ 45 ደቂቃ ያህል አቆይተን መታጠብ ለፀጉር እድገት እና ልስላሴ ተመራጭ ነዉ፡፡
ዘዴ 2 – ቀይ ሽንኩርት ለፀጉር እድገት
ሽንኩርት ዉኃ ዉስጥ በመቀቀል በዉኃዉ ፀጉሮን መታጠብ እና አቆይቶ በንጹህ ዉኃ ማለቅለቅ ፡፡ ይህንን ለአጠቃቀም ቀላል የሆነዉን
ዘዴ በመጠቀም አስገራሚ ዉጤት ያገኙ፡፡
ዘዴ 3 - የኮኮናት ዘይት ለፀጉር እድገት
ፀጉር _ በፍጥነት እንዲያድግ በየቀኑ የኮኮናት ዘይት በማሞቅ የፀጉርን ቆዳ አዳርሶ በመቀባት ቆዳዉን በደንብ ማሸት በጣም ዉጤታማ ለፀጉር እድገት ወሳኝ ነገር ነዉ፡፡ በየቀኑ የፀጉርን ቆዳ ለ1 ደቂቃ በማሸት ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ዉጤቱን ማየት ይችላሉ፡፡(የወይራ ዘይት መጨመር እንችላለን)
የፀጉርን ቆዳ በሞቀ የኮኮናት ዘይት ማሸት ሴሎቹ እንዲነቃቁ ያደርጋል፡፡
ዘዴ 4 - እንቁላል ለፀጉር እድገት
እንቁላል ነጩን ብቻ ለመምታት ፀጉርን በመቀባት ፀጉርዎ ፈጣን እድገት እንዲኖረዉ ማድረግ ይቻላል፡፡
እንቁላሉን ፀጉርዎ እስከ ጫፉ ድረስ በመቀባት ጠንካራና ጤናማ ፀጉር እንዲኖሮዎት ያድርጉ፡፡
ዘዴ 5 - የኮከ ቅጠል ለፀጉር እድገት -
የኮክ ቅጠል - 100 ግራም በአንድ ሊትር ዉኃ ለ15 ደቂቃ ያህል - መቀቀል፣ አዉርደን ለብ ሲል ፀጉራችንን በዉኃዉ መታጠብ እና ቆዳችንን በማሸት በላስቲክ ሸፍነን ከ1 ሰዓት ቡኋላ በንጹህ ዉኃ ማለቅለቅ ለፀጉር እድገትን ያፋጥናል ፣ የፀጉር _ መሳሳትን ይከላከላል፡፡
ዘዴ 6 - እሬት(ኦሊቬራ) ለፀጉር እድገት
አንድ የኦሊቬራ ቅጠል በመሰንጠቅ ዉስጡ ያለዉን ዝልግልግ ፈሳሽ በማዉጣት ፀጉራችንን እስከ ስሩ በማዳረስ መቀባት፣ ቆዳችንን ለጥቂት ደቂቃ ማሳጅ ማድረግ፣ ለ30 እስከ 45 ደቂቃ ያህል በላስቲክ ሸፍኖ ማቆየት ፣ ከዛ መታጠብ፡፡
ለፀጉር እድገት፣ ለፀጉር መነቃቀል እና መሳሳት እንዲሁም ለፎረፎር እሬት (ኦሊቬራ) መድኃኒት ነዉ፡፡
ዘዴ 7- የሰልብያ ቅጠል ፈጭቶ መቀባት ፣የራስ ክምር _ ከውሀ ጋር በመፍጨት በወፍራሙ መቀባት ፣ የልት ቅጠል ስሩን በጠጅ ከዘፈዘፉ በኋላ መቀባት ፣ የኑግ እና የዋግ ስር እና ቅጠላቸውን ወቅጦ በወፍራሙ በመጭመቅ መቀባት እና የቁራ ሀረግ ፈጭቶ መቀባት ፀጉርን ከማሳደግ ባለፈ ለማጥቆርም ይረዳል ፡፡
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna