ዲስክ መንሸራተት

የዲስክ መንሸራተት በብዙ ሠዎች ላይ የሚከሰት ህመም ሲሆን በከፍተኛ የህመም ስሜትና ድካም የሚፈጠር ችግር ነው።አንዳንድ ጊዜ በእጅ ላይ የማደንዘዝ እና የድካም ስሜት ይፈጠራል።አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ በተቃራኒው ምንም አይነት ስሜት አይኖረውም፡፡ዲስኩ የነካው ነርቭ ከሌለ የህመም ስሜት አይሰማነም፡፡የዲስክ መንሸራተት ምልክቶች ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ በራሳቸው ጊዜ ሊጠፉ ይችላሉ።የህመም ስሜቱ የሚገልፅ ከሆነ ግን ቀዶጥገና ሊኖር ይችላል፡፡በዚህ ፁህፍ የዲስክ መንሸራተት ምልከቶችን ፣ህከምናና ቅድመ ጥንቃቄ መንገዶችን እንዳስሳለን።

ህከምና

የዲስክ መንሸራተት ከፍተኛ የህመም ስሜት ሊፈጥር ይችላል ነገር ግን ተገቢውን ህክምና በማድረግ ስሜቱን ማስታገስ እንችላለን፡፡የዲስክ መንሸራተት የሚያጋጥማቸው ሰዎች በአራት ሳምንት ውስጥ ያገግማሉ፡፡የህመም ስሜት ከሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች በመቆጠብ እና የተወሰኑ እንቅስቃሴዎች በማድረግ እንዲሁም የህመም መድሃኒቶችን በመውሰድ ህመሙን ማስታገስ እንችላለን፡፡

መድሃኒቶች

የህመም ክኒኖች እንደ ኢቡፕሮፊን(lbuprofen) አይነት የህመም መድሃኒቶችን በመውሰድ የህመም ስሜቱን በተወሰነ ደረጃ መቀነስ እንችላለን።የነርቭ መድሃኒቶች ጋባፔንቲን(gabapentin) ፣ፕሬጋባሊን(pregabalin) እና ዱሎክሴቲን(duloxetine) የመሳሰሉ መድሃኒቶች የነርቭ ህመምን ለማስታግስ ይረዳሉ።ናርኮቲከስ የህመም መድሃኒቶች የህመም ስሜቱን ማስታገስ ካልቻሉ ኮዲን( Codine) ወይም ሌላ የናርኮቲከ መድሃኒቶች ይታዘዛሉ ነገር ግን እነዚህ መድሃኒቶች ማቅለሽለሽ፣ ግራ መጋባት እና የሆድ ድርቀት ስሜቶችን ሊፈጥሩ ይችላሉ።በኮርቲዞን መወጋት ህመሙ የተፈጠረበት ቦታ ላይ ኮርቲዞን በቀጥታ መወጋት የህመ ስሜቱን ሊቀንስ ይችላል ነገር ግን ይህን መድሃኒት አዘውትሮ መወጋት ሌላ የጤና መዘዝ ሊያመጣ ይችላል።የኢ ፒራ መርፌ(Epidural injection) X.ፒዱራል በተባለው የሰውነት አካል ላይ የሚደረግ መርፌ መወጋት ነው።መርፌው በውስጡ የተለያዩ የህመም ስሜትን የሚያስታግሱ መድሃኒቶች በውስጡ የያዘ ነው።

ቴራፒ

የሰውነት ቴራፒስቶች ህመሙን የሚቀንሱ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን ለማግኘት ይረዱናል።ቴራፒሰቶች ከሚከተሉት ማስታገሻዎች ውስጥ የተወሰነውን እንድንሞክር ይመከሩናል፦

ገመድ

ከብደትና ፑሊ በመጠቀም በተጎዳው ቦታ ላይ ጫና በመፍጠር ለአጭር ጊዜ አንገትን በብሬስ ማሰር፣ኤሌክትሮቴራፒ፣የኤሌትሪክ ኢምፐልስ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የህመም ስሜትን ያሰታግሳል፡፡

የአልትራሳውንድ ህክምና

የተጎዳውን ክፍል በአልትራሳውንድ ድምፅ በማከም የደም ዝውውር በተሻለ ሁኔታ እንዲካሄድ ማድረግ ይቻላል።

ቀዶ ጥገና

ከላይ የተጠቀሱት ህከምናዎች ህመሙን ማስታገስ ካልቻሉ የማደንዘዝ ስሜት ከቀጠለ ወይም ሽንትን የመቆጣጠር ብቃት መውረዱን ከቀጠለ ቀዶ ጥገና ህክምና _ _ ማድረግ ይመከራል።በቀዶ ጥገናው ወቅት አብዛኛውን ጊዜ ወጣ ያለው የዲስክ ክፍል ብቻ ይወገዳል።ይህ ቀዶ ጥገና ኦፕን ዳይሴክቶሚ(disectomy)ይባላል።ብዙ ጊዜ የላፓራስኮፒክ መንገድን በመጠቀም ይከናወናል።ሐኪሙ ሆድ ውስጥ ትንሽ ቀዳዳ ይከፍትና ሆድን አልፍ ጅርባ አጥንት ላይ ቀዶ ጥገና ያከናውናል።በዚህ መንገድ ቀዶ ጥገና ማካሄድ የጀርባ አጥንት አካሎችን ከማስወገድ ያድናል።የጀርባ አጥንት ነርቮችም ሳይነካኩ ቀዶ ጥገናውን ማከናወን ይቻላል።የተለመደ ባይሆንም አንዳንድ ጊዜ ሙሉ ዲስኩ መወገድ ይኖርብታል።ዲስኩን አስወጥቶ በብረት በመተካት ቀዶ ጥገናም ሊፈፀም ይችላል።

መንስኤዎች

የጀርባ አጥንት ቨርተብሬ የሚባሉ የ26 አጥንቶች ስብስብ ነው።በቨርተብሬዎች መሃከል የሚገኙ ርብራብ መሰል ከፍሎች ናቸው።እነዚህ ዲስኮች የጀርባ አጥንትን ባለበት ደግፈው ይይዛሉ።ሰውነት ከባድ ሃይል ሲያስተናግድ ሃይሉን የሚያምቁ ክፍሎች ናቸው፡፡ዲስክ ጠንካራ ሽፋን ያለው ሲሆን በውስጡ ግን ለስላሳ የሆነ ፈሳሽ ነው።የዲስከ መንሸራተት የሚባለው በዲስክ ግድግዳ ላይ በሚፈጠር ቀዳዳ ምክንያት የሚፈጠር የውሰጥ ፈሳሽ መውጣት ነው።ይህ ወፍራም ፈሳሽ ነርቮችን የሚረብሽ ፋብረ ነገር በውስጡ የያዘ ነው።ይህ መረበሽ ከፍተኛ ህመም ሊፈጥር ይችላል፡።

የዲሰከ መንሸራተት ዋነኛ መንስኤ ከጊዜ ጋር የሚፈጠር የጀርባ እንቅስቃሴ ውጤት ነው።ዲስክ ከእድሜ ጋር ውኃማ ይዘቱን ያጣል።ይህ የፈሳሽ መቀነስ በዲስክ ላይ ከፍተት እንዲፈጠር ምከንያት ይሆናል።የዲስክ መንሸራተት መቸ እንደተፈጠረ ማወቅ ያስቸግራል፡፡

*ተጋላጭነት

የዲስክ መንሸራተት በየትኛውም ዕድሜ ሊከሰት የሚችል ህመም ነው ነገር ግን ብዙ ጊዜ የሚፈጠረው እድሜያቸው በ20ዎቹ ወይም በ30ዎቹ ውስጥ ያሉ ሰዎች ላይ ነው፡፡

የጤናችግሮች

በጣም ያልተለመደ ቢሆንም በዲስክ መንሸራተት ምክንያት ከዳሌ በታች ያለው የነርቭ ክምችት ሊጨማደድ ይችላል።ይህ ሲሆን በዘላቂነት የሚቆይ የድካም _ ስሜት ፣የሽንትና ሰገራ መቆጣጠር ብቃት መዳከም እና ስንፈተወሲብ ይፈጠራል ስለሆነም የሚከተሉት ስሜቶች ሲፈጠሩ የህክምና ባለሙያ ያማክሩ

ሀ)የሰገራ እና ሽንት መቆጣጠር ብቃት ሲዳከም

ለ)ንሯችንን በሚረብሽ ደረጃ የድካም ስሜት ከተሰማን

ሐ)በውስጥ ታፋ እና እግር ጀርባ የሚፈጠር የማደንዘዝ ስሜት ናቸው፡፡

ቅድመ ጥንቃቄ

የሚከተሉትን መንገዶች በመከተል እራሳችንን _ ከዲስክ መንሸራተት መጠበቅ ይኖርብናል።

ለምሳሌ፦

ሀ)ከፍተኛ የሠውነት ክብደት እንዳይኖርዎ መጠንቀቅ

ለ)ክብደት ሳያነሱ የሰውነት አቋምን ማስተካከል

ሕ)የዲስክ መንሸራተት ምልክቶች ካዩ በቂ እረፍት መውሰድና ተገቢውን ህክምና ማከናወን።

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna