የሳንባ ነቀርሳ
Author: solomon
Date: 2025-01-18
የሳንባ ነቀርሳ
የሳንባ ነቀርሳ(ቲቢ)በባክቴሪያ አማካኝነት የሚሙጣ በሽታ ነው።ባክቴሪያዎቹ በየትኛውም የሠውነት አካል ላይ ካረፉ እራሳቸውን ካበዙና ሠውነታችን እራሱን መከላከል ካልቻለ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ሊይዘን ይችላል።የሳንባ ነቀርሳ በሽታ በሳንባ ውስጥ መገኘት የተለመደ ነው። በሽታው ከሚያሳያቸው ምልክቶች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡እነሱምቻ
*በትንሹ ከሶስት ሳምንት በላይ የሚዘልቅ መጥፎ ሳል
*በደረት አካባቢ የሚሰማ የደረት ስሜት
*ደም የተቀላቀለ ወይንም ደም የለለው አከታ
*የድካም ሰሜት
*ትኩሳት
*በምሽት ጊዜ ማላብና ሌሎችም
አንድ ሰው በባክቴሪያው ከተያዘ በኋላ የቲቢ በሽታ እንዲከሰት የሚያፋጥኑ የተለያዩ አጋላጭ ነገሮች አሉ።ከእነዚህም ጥቂቶቹ ፦
*በኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ተይዘው ከሆነ ከዚህ በፊት በቅርብ ጊዜ በባክቴሪያው ተጠቅተው ከነበረ
*ሌሎች የጤና እክሎች ካለብዎት ፣የአልኮል መጠጥ ሱስ እና አደንዛዥ ዕፅ የሚጠቀሙ ከሆነ
*ከዚህ በፊት የቲቢ በሽታ ኑሮብዎት በሚገባ ህከምና ያላገኙ ከሆነና የተዳፈነ ቲቢ(latent TB Infection) ሲያጋጥም
*ባከቴሪያው ሠውነታችን ውስጥ በሽታውን ሳያስከትል ዝም ብሎ ሊኖር ይችላል።ይህም የሚሆነው የሰውነት በራሱ በሽታን የመከላከል ኀይል ባከቴሪያው እንዳያድግና እንዳይራባ ስለሚያግደው ነው።እንደዚህ አይነት ሠዎች ባከቴሪያው ወደሌላ ሰው እንዲራባ አያደርጉም ነገር ግን ባክቴሪያው የሠውነትን በሽታ የመከላከል አቅም አሸንፎ ማደግ ከጀመረ የቲቢ በሽታን ያስከትላል።
*የሳንባ ነቀርሳ(TV disease)
*ሰውነት በሽታን የመከላከል አቅሙ ሲደከምና ባከቴሪያው ለመራባት ዕድሉን ሲያገኝ ያን ጊዜ የሳንባ ነቀርሳ በሽታን ያስከትላል።የተያዘውም _ ሰው የበሽታ ምልከቶችን ማሳየት ይጀምራል።ለሌሎች ሰዎች የማስተላለፍ አቅም አለው።ይሁንና አንዳንድ ሰዎች ባክቴሪያው በሰውነታቸው ውስጥ ቢኖርም እስከመጨረሻው የባክቴሪያው ተሸካሚ ብቻ ሁነው ሳይታመሙ ይኖራሉ።አንዳንዶች ደግሞ ወዲያውኑ ይታመማሉ።ሌሎችም ከተወሰነ ዓመት በኋላ ሊታመሙ ይችላሉ።
*በተለያዩ ምክንያት የሰውነታቸው የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም ወይም ኢሚውን ሲስተም የተዳከሙ ሰዎች በሽታውን በቀላሉ ያሳያሉ፡፡ለምሳሌ በኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በሽታ የተጠቁ ሰዎች በቀላሉ የቲቢን በሽታ ያሳያሉ ምክንያቱም ቫይረሱ በዋናነት የተፈጥሮን የመከላከል ብቃት ስለሚያዳከም ነው፡፡
መከላከያዎቹ፦
*በቤት ውስጥ የታመመ ሰው ካለ ጥንቃቄዎችን ማድረግ
* የቤትና ትራንሰፖት ቦታዎች ላይ አየር እንዲዘዋወር ማድረግ
*የሳል አልያም ሌሎች ምልክቶች ሲኖሩ በቶሎ ህከምና ማድረግ ተገቢ ነው
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna