ላብ
Author: solomon
Date: 2025-01-15
ላብ
ላብ በጣም ጥሩ ነገር ነው ምክንያቱም ሰውነትዎን ለለሚያቀዘቅዝልዎ ነገር ግን ከመጠን ያለፈ ሲሆን የሚያሳቅቅ እና የሚያስፈራ ችግር ይሆናል።ላብ የቆሸሽን ከማስመሰሉ በተጨማሪ ባከቴሪያዎች ከመጠን በላይ እንዲራቡ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። ይህም ሁኔታ መጥፎ የሰውንት ጠረን እንዲኖር የደርጋል።ዘውትር የሚለብሱት የሸሚዝ ልብስ መዲኖር የሰጨንቅዎት ይሆናል ይሁንና ይህን ችግር ለመቅረፍ ይረዳዎት ዘንድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በአግባቡ ይተግብር የረዳን
*የቡናና ሻይ አወሳሰደዎን ይቀንሱ
ካፌየን ለብዙዎቻችን ተመራጭ ትኩስ መጠጣችን ሲሆን የነርቭ ስርዓታችን ይንቃቃል።ይህ እንዲሆን ባንፈልግም የላብ አመንጭ አጢዎቻችን _ በእጥፍ እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል ሰለዚህ ትኩስ ነገሮችን መጠቀም ማቆም የሚደገፍ ሃሳብ ነው፡፡
*በብዛት ውሃ መጠጣት
አብዛኛው ላብ የሚሰራው ከውሐ ስለሆነ የላብ መጠንን ለመቀነስ የውሐ አጠቃቀማችን መቀነስ አለብን ማለት አይደለም።በቀን 8-12 ብርጭቆ ውሐ በአማካኝ መጠጣት ተገቢ ነው።ይህን ማድረጋችን ሰውነታችን እንዲቀዘቅዝ ያደርገዋል ስለዚህ ሰውነታችን ራሱን ለማቀዝቀዝ ላብ አያመነጭም *ሲጋራ ማጨስና ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት ያቁሙ
እነዚህ ሁለት ልምዶች በቶኖች የሚገመት መርዛማ ነገሮችን ወደሠውነታችን እንዲገቡ ያደርጋሉ ስለሆነም እነዚህን መርዛማ ነገሮች ከሰውነታችን ለማስወገድ ከመጠን በላይ ያልበናል።በተጨማሪም ሲጋራ ማጨስና አልኮል ከመጠን በላይ መጠጣት ለጤንነታችን ጎጅ ስለሆኑ አይመከርም።
*በፀረ ኦከሲዳንት የበለፀጉ ምግቦችን ይመገቡ
ፍራፍሬ እና አትከልቶች ፀረ ኦከሲዳንት በውስጣቸው ይዘዋል በመሆኑም በሰውነት ውስጥ ያሉ መርዛማ ነገሮችን ለማከሸፍ ይረዳል።እነዚህ ፍራፍሬዎች እና አትከልቶች መርዛማ ነገሮችን ሰለሚያከሽፏቸው ከሰውነታችን ውጪ ለማሶገድ ላብ ማላብ አያስፈልግም፡፡አንዳንድ የፀረ ኦክሲደንት ምንጮች ወይን፣ቀያይ ፍሬዎች፣ለውዝ እና ብርቱካናማ ቀለም ያላቸው ፍራፍሬዎች ናቸው፡፡
*ከሚያቃጥሉ ምግቦች እራስዎን ያርቁ
የሚያቃጥሉ ምግቦች ለጤንነታችን በጣም ጠቃሚ ናቸው ነገር ግን በብዛት እንዲያልበን ስለሚያደርጉ _ አይመከርም።ምንም እንኳ ለኢትዮጵያውያን ትኩስ ነገር መተው ከባድ ቢሆንም የሚያቃጥሉ ምግቦች የሠውነት ሙቀትን በመጨመር ከመጠን በላይ እንዲያልበን ያደርጋሉ።የላብ አመንጪ እጢዎቻችን ወደ ስራ በመግባት ሰውነትን ያቀዘቅዛሉ፡፡
*ጭንቀትና ፍርሃትን ያስወግዱ
ፍርሃትና ጭንቀት የላብ አመንጪ እጢዎች ከመጠን በላይ በስራ እንዲጠመዱ ያደርጋቸዋል።ይህም ውጥረት ስጋትና ሃሳብን ለመቀነስ የሚወስዱት እርምጃ ነው።የተለያዩ ዘና የሚያደርጉ አስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በመስራት ከላይ የተጠቀሱትን ትግሮች በመቀነስ የሚያልበነን የላብ መጠን መቀነስ ይቻላል።
*ከቤት ከመውጣትዎ በፊት ቀዝቃዛ ሻወር ይውሰዱ።
ቀዝቃዛ ሻወር በማንኛውም ምክንያት ያላበንን ላብ ለማስወገድና የሰውነታችንን ሙቀት ለማመጣጠን ይረዳናል።ቀዝቃዛ ሻወር በሚወሰድበት ጊዜ ፀረ-ባከቴሪያ ሳሙናዎችን በመጠቀም የሰውነትን ጠረን ማስተካከል ይቻላል።በሙቅ ውሐ ሻውር መውሰድ ያለብዎትን ከመጠን ያለፈ የላብ ችግር ያባብሳል።
*የብብትዎን ፀጉር ያስወግዱ
ላብ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚያልቡን የሰውነታችን ከፍሎች ውስጥ አንዱ ብብት ነው፡፡የላብ ማድረቂያ ምርቶችን ከመጠቀም ባሻገር የብብት አካባቢ እንዲቀዘቅዝ ፀጉርን ማሶገድ ጥሩ ሃሳብ ነው።በተጨማሪ የብብት ፀጉርን መላጨት ሽታ አምጪ ባከቴሪያዎችን እንዳይራቡ ያደርጋቸዋል፡፡
*ትከከለኛ የሆኑ ልብሶችን መልበስ
ከተፈጥሮ ነገር ውጪ የተመረቱ ልብሶችን እንደኮተን ፣ላይለን እና ውል ዓይነት ልብሶች የሠውነት ቆዳዎችን እንዲተነፍስ ያደርጋሉ።ሰው ሰራሽ ፋይበሮች ሙቀትን በማሞቅ ብዙ ላብ እንዲያልበን ያደርጋሉ።ሳሳ ያሉ ልብሶችን መልበስ በቂ የሆነ አየር በልብስና በቆዳ መካከል እንዲዘዋወር ያደርጋሉ።ደብዛዛ እና ቀለል ያሉ ልብሶችን መልበስ ይመከራል።በተለይም ጥቁር ቀለም ያላቸው ልብሶች ሙቀትን ይሰበስባሉ።
*ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረትን ያስወግዱ
ከመጠን ያለፈ ወይም በጣም ወፍራም ሠዎች በከፍተኛ ሁኔታ ያልባቸዋል ምከንያቱም ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ሙቀት ስላላቸው ነው።በእውነት ከዚህ የላብ ችግር መውጣት የሚፈልጉ ከሆነ ሸንቀጥ ለማለት ይሞከሩ።
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna