የጉበት በሽታ
Author: solomon
Date: 2025-01-13
የጉበት በሽታ
የጉበት በሽታ በአሁኑ ሰአት ብዙ ሰዎችን እያጠቃ የሚገኝ እና መፍትሄ ያልተገኘለት መሆኑ ይታወቃል።በአጠቃላይ አምሰት አይነት የጉበት በሽታ የቫይረስ አይነቶች ሲኖሩ እነዚህም፦
ሄፓታይተስ፣ኤ፣ቢ፣ሲ እና ዲ ይባላሉ።ከእነዚህ ውስጥ ግን በሽታን በማምጣት የሚታወቁት ቢ እና ሲ የተባሉ ሲሆኑ ሄፓይታይተስ ቫይረስ፣ዲ እና ኢ ደግሞ ብዙም የተለመዱ አይደሉም።ያልጠናበት ህመምተኛን ስናይ የሚያሳያቸው ምልከቶች ትኩሳት፣ድካም የማለት ድካም ማቅለሽለሽ፣የምግብ _ _ ፍላጎት ማጣት፣የሠውነት ስሜት ሽፍታ እንዲሁም የመገጣጠሚያ ህመም ሲሆኑ ትኩሳት በጊዜ ሂደት እየቀነስ የሚመጣ ሲሆን በስመጨረሻም የታካሚው ሰውነት እና አይኖቹ ቢጫ መሆን ሊኖር ይችላል።የጠና የጉበት ህመም በሽታ ባለባቸው ሰዎች ላይ ግን በአብዛኛው የሚታዩ ምልክቶች ባይኖሩም እንደድካምና የመዛል ሰሜት ይታይባቸዋል።በሽታው ሳይታከም ከቆየ ወደ ጉበት ካንሰር ሊለወጥ ይችላል፡፡ታማሚው ያለበትን የጉበት ቫይረስ አይነት ለመለየት ቀለል ያለ የደም ምርመራ ማድረግ ይቻላል።የእያንዳንዱን አይነት የጉበት በሽታ ከዚህ በታች ቀርበዋል።
1.ሄፓታይተስ ኢ፦ ይህ አይነቱ የጉበት ህመም የሚተላለፈው በቫይረስ የተበከለ ምግብ እና መጠጥ በመውሰድ ነው።ህፃናት ላይ ምንም አይነት ምልክት የማያሳይ ሲሆን አዋቂዎች ላይ ግን ከላይ የተገለጡትን ምልክቶች እንደ መሆን፣ድካም፣ማቅለቅለሽ ምልክቶች ይስተዋላሉ፡፡ አይን ቢጫ
2.ሄፓታይተስ ቢ፦ ሄፓታይተስ ቢ እንደ ሲርሆሲስ እና የጠና የጉበት ህመም በማምጣት ይታወቃል።መተላለፊያ መንገዶችን ስናይ አንደመርፌ እና ምላጭ የመሳሰሉ የተበከሉ ስለታማ ነገሮች ከእናት ወደ ልጅ እና የግብረ ስጋ ግንኙነት ይጠቀሳሉ፡፡
3.ሄፓታይተስ ሲ፦ ልክ እንደ ሄፓታይተስ ቢ ሁሉ ሄፓታይተስ ሲም ለጉበት ካንሰርና ሲርት ሆሲስ ለሚባለው ለጠና የጉበት ህመም የሚዳርግ ሲሆን መተላለፊያ መንገዶችም ተመሳሳይነት አላቸው፡፡እስከዛሬ ድረስ ሄፓይታይተስ ሲን ለመከላከል የሚያገለግል ክትባት ያልተገኘ ሲሆን የሄፓታይተስ ሲ በሽታ ታማሚዎችም የተለየ የሚያሳዩት ምልክት የለም።በሽታው መኖሩን ለማወቅ የደም ምርመራ ማድረግ የሚቻል ሲሆን ወደህክምና አማራጮች ስንመለከት በሳምንት እንደጊዜያችን የሚሰጥ የመርፌ ህክምና እና ከ24-48 ሳምንታት የሚዋጥ መድሃኒት ይገኙበታል፡፡
ጠቃሚ ምክሮች
*የአልኮል መጠጣና ሲጃራ ማጨስ ማቆም
*በቂ እረፍት ማድረግ
*ጫና የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎችን ከማድረግ መቆጠብ
*እንደስርሆሲስና የጉበት ጮማ መኖራቸውን ለማረጋገጥ በየጊዜው ክትትል ማድረግ
*ከታማሚ ጋር በጋራ የሚኖሩ ሰዎች ካሉ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ መኖሩን ለማረጋገጥ የደም ምርመራ ማድረግ እንዲሁም ክትባት መውሰድ እና ህክምና መውሰድ ጀምረው ከሆኑ ደግሞ ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት ህክምናዎትን በሚገባ መከታተል ያሰሰፈልጋል።
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna