የጥርስ ህመም
Author: solomon
Date: 2025-01-10
የጥርስ ህመም
ጤንነቱ የተጠበቀ ጥርስ ለባለቤቱ ውብ ገፅታን ከማጎናፀፉ በላይ ከሰዎች ጋር ያለመሳቀቅ ለማውራት እና እንደልብ ለመሳቅ ያስችላል።ያለአፍረትና መሳቀቅ ለመሳሳም ጤናማ ጥርስ የሚለግሰው ንፁህ የአፍ ጠረን ወሳኝነት አለው።ጥርሳችንን በተለያዩ ምከንያቶች ጉዳት ሊደርስበትና ተፈጥሯዊ ውበቱን ሊያጣ ይችላል።ለጥርስ ህመም ከሚያጋልጡ በርካታ ምክንያቶች መካከልም ጥርስን ባግባቡ አለማፅዳትና የፍሎራይድ እጥረት ዋንኞቹ እንድሆኑ የጥርስ ህከምና ባለሙያዎች ይገልፃሉ።የጥርሳችንና የድዳችን ጤንነት ለመጠበቅ እጅግ በቀላል መንገድ ጥዋትናማታ ጥርስን በቡርሽና በጥርስ ሳሙና እንዲሁም ምግብ ከተመገብን በኋላ አፋችንን በመጉመጥመጥ በጥርሳችን ውስጥ የሚቀሩ የምግብ ትርፍራፊዎችን ማስወገድ ይኖርብናል።የጥርሳችንን ጤና ለመጠበቅ ካልቻልን በአለማችን አጅግ አደገኛ የጤና ቀውስ ከሚያስከትሉ በሽታዎች አንዱ ለሆነው የጥርስ ኢንፌከሽን ልንጋለጥ እንችላለን።ጥርሳችንን ከጭንቅላታችንና ከመላው የአካል ከፍላችን ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን ይህ የአካላችን ከፍል ሲታመም ጉዳቱና ችግሩ ጭንቅላታችንን ጨምሮ በመላው የሠውነታችን ከፍሎች ላይ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል የጥርስ ህከምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።የጥርስ ኢንፌክሽን በሽታ በየትኛውም የዕድሜ ከልል (ከሰትና ማንኛውንም ሠው ሊያጠቃ የሚችል በሽታ እንደሆነ የሚናገሩት ዶክተሩ ምግብ ከተመገብን በኋላ አፋችንን በመጉመጥመጥ በጥርሳችን መሃል የሚቀሩ ትርፍራፊ ምግቦችን የማናፀዳ ከሆነ ለባከቴሪያ መራቢያ ምቹ ሁኔታን እንፈጥራለን፡፡በርካታ ባከቴሪያዎች በቀላሉ በአፋችን ውስጥ ከተራቡ በኋላ ጥርሳችንን እንዲቦረቦር ፤መንጋጋችን እንዲበሰብስና እንዲቆስል በማድረግ ለጥርስ ኢንፌክሽን ሊያጋልጡን ይችላሉ።እነዚህ ባከቴሪያዎቻ የአፋችን ውስጠኛው ከፍል እንዲቆስልና መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲፈጠር ከማድረግ በላይ የአንገት አካባቢን ቆዳን በመብላት ተጠቂው የመተንፈሻ ቱቦ ችግር እንዲያጋጥመው ያደርጋሉ፡፡
አየር ወደ ታማሚው ልብ እና ሳንባ እንደልብ እንዳይደርስ በማገድ ልብ፣ሳንባና አእምሮ ላይ ችግር ይፈጥራሉ።ይህ ሁኔታም ታማሚው የአየር እጥረት እንዲያጋጥመው በማድረግ ለሞት ሊዳርገው እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ።አንድ ሰው በጥርስ ኢንፌክሽን በሽታ ሲጠቃ ምንም አይነት ምልክቶችን አያሳይም።ችግር እንደተከሰተ በተጠቂው ሰው ላይ የሚታይ የጤና መቃወስ አይኖርም።
በዚህ ምክንያትም በርካቶች ችግሩ መኖሩን እንኳን ሳያውቁ ለከፋ የጤና ጉዳት ይዳርጋሉ።በድድ ላይ የሚከሰቱ ኢንፌከሽኖችና እብጠቶች በወቅቱ ተደርሶባቸው በቶሎ ህከምና ካላገኙ በድድና በምንጋጋ ጅማቶች ላይ አደገኛ ጉዳት ያስከትላል።ከዚህ በተጨማሪም በኢንፌከሽኑ የሚፈጠሩ ባከቴሪያዎች በአፋችን በኩል ወደ ውሰጣዊ ሰውነታችን ይገቡና ወደልባችን በማምራት ልብ ተፈጥሯዊ ተግባሩን በአግባቡ እንዳያከናውን ሊያደርጉትና ጉዳት ሊያስከትሉበት ይችላሉ።በጥርስ ኢንፌክሽን የተጠቁ ሰዎች ከሌሎች ጤናማ ሰዎች ይልቅ በቀላሉ በልብ በሽታ ሊያዙ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።ሌላኛው ለጥርስ ህመም መንስኤነት በዋንኛነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል አንስተኛ የፍሎራይድ ይዘት ያላቸውን ፈሳሽ መጠጣት ሲሆን ሰውነታችን በቂ የፍሎይራድ መጠን ሳያገኝ ሲቀር ጥርሳችንም ሆነ ድዳችን ለከፋ የጤና ችግር ይጋለጣል።ተጣርተው በፕላስቲክና _ በጠርሙስ እየተሞሉ ገቢያ ላይ የሚውሉ ውሃዎች በአብዛኛው በውስጣቸው የሚይዙት የፍሎራይድ ማዕድን በውስጣቸው እንደሌለ በባለሙያዎች ይነገራል።ከዚህ ጋር ተያይዞም ህብረተሰቡ ለመጠጥነት የሚገለገልባቸውን የፕላስቲከ ውኋዎች የማዕድን ይዘት የማየትና የማወቅ ልምዱ እምብዛም ነው።በመሆኑም ህብረተሰቡ የቀረበለትን ሁሉ ያለጥያቄ እና ዕውቀት እንዲጠቀምና ለተለያዩ የጤና ችግሮች እንዲጋለጥ እያደረገው ነወ።እያንዳንዱ የሚጠቀማቸዉ ምግቦችና መጠጦች ምን አይነት ቫይታሚንና ማዕድኖች በምን ያህል መጠን እንደሚይዙ ማወቅ ይገባል።
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna