መጥፎ የአፍ ጠረን

በተለምዶ መጥፎ የአፍ ጠረን የምንለው በሽታ ሃሊቶሲስ በመባል ይታወቃል።በስዎች መካከል የሚያሸማቅቅ በሽታ ሲሆን በአራስ መተማመናችን ላይ ጉዳት አለው።መጥፎ ሽታ ብዙ መንስኤዎች አሉት ።ጠረን ያላቸው ምግቦች መመገብ፣ማጨስ፣የአፍ መድረቅ፣የድድ በሽታ፣የሳይንስ በሽታ እና ሌሎች በሽታዎች የአፍ ጠረን ሊያመጡ ይችላንስ በሽታ የመጥፎ አፍ ጠረን መነሻ የአፋችን ጀርባ ወይም በጥርሶቻችን መሃል የሚገኝ የባከቴሪያ ከምችት ነው::በሽታን ለመከላከል የለን ጤንነትን መጠበቅ ይኖርብናል።ጥርስን በየጊዜው መቦረሽ ይኖርብናል።በቀን ውስጥ በቂ ውሐ መጠጣት ሌላኛው መፍትሄ ሲሆን ምግብ ከተመገቡ በኋላ አፋችንን በውሃ መጉመጥመጥ በጥርሳችን መሃል ያሉ የምግብ ፓርቲከሎችን ለማሶገድ ይረዳል።ከዚህ በተጨማሪም _ ለአፍ ጠረን መከላከያ ልናውላቸው የምንችላቸው የቤት ውስጥ መፍትሄዎች የሚከተሉት ናቸው፦

1.ቀረፋ

ቀረፋ በውስጡ ሲናሚክ አልዲሃይድ አሲድ የያዘ ሲሆን ይህ ዘይት መጥፎ ሽታን ከመሸፈን አልፎ አፋችን ውስጥ ያለውን የባክቴሪያ መጠን በመቀነስ ይታወቃል።መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመቀነስ የሚከተሉትን መተግበር ጠቃሚ ነው፡፡

*አንድ የሻሂ ማንኪያ ይቀረፋ ዱቄት በአንድ ብርጭቆ ውሐ ውስጥ አድርገው ያፍሉ

*ውሃውን አጥልለው ይጉመጥመጡበት

2.የፓርሲሊ ቅጠል

ፓርሲሊ ውስጥ ያለው ከሎሮፊል መጥፎ የአፍ ሽታን ለመቀነስ ይረዳል።ፓርሲሊ ቅጠል አቸቶ ውስጥ ነከረው ማላamm እንዲሁም እንደሌላ አማራጭ የፓርሲሊ ቅጠሉን ፈጭተው ጁሱን ቀስ ብለው መጠጣት።

3)የሎሚ ጭሚቂ

የሎሚ አሲዳማ ይዘት ጥርስዎ ወሰጥ የባከቴሪያ ዕድገት እንዲገታ ይረዳል።የሎሚ ሽታም እራሱ የአፍዎን ጠረን ለመደበቅ ይረዳል ስለሆነም አንድ ሻሂ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ውሃ ውስጥ ጨምቀው አማስለው ይጉመጥመጡት።ጨው ጨምረውም ማጉመጥመጥ ይችላሉ።ይህ መፍትሄ የአፍዎን ድርቀት በመቀነስ በአፍ ድርቀት የሚመጣን ሽታ ለመቀነስ ይረዳል።።

4.የፖም አቸቶ(አፕል ሳይደር ቪኒጋር)

ይህ አቸቶ የፒኤችዲ መጠን ባህሪው ለመጥፎ የአፍ ጠረን መፍትሄ እንዲሆን ያደርገዋል።የሚከተሉትን በቤትዎ አዘጋጅተው ይጠቀሙ

*አንድ ሻሂ ማንኪያ ፖም አቸቶ ከአንድ ብርጭቆ ውሃ ጋር አቀላቅለው ከምግብ በፊት ይጠጡ ምክንያቱም አቸቶው ጨጓራዎ ምግብ ለመፍጨትም ያግዘዋል።

*አቸቶውን ከውሃ ጋር አቀላቅለው በጉሮሮዎ ያስረቅርቁ

5.የመጋገርያ እርሾ

የመጋገሪያ እርሾ መጥፎ ሽታ በማሶገድ ይታወቃል።መጥፎ ጠረን የሚያስከትለውን የአሲድ አለመጣጠን በማሻሻል የአፍ ጠረናችችን ይቀንሳል።የአፍ ውሰጥ ባከተሪያ በመዋጋት መጥፎ ሽታን ያስቀራል።

*ግማሽ ሻይ ማንኪያ እርሾ በአንድ ብርጭቆ ውሐ አቀላቅለው በቀን አንዴ ይጉመጥመጡ

*ጥርሶዎን በእርሾ መቦረሽ የአፍዎን አሲዲቲ ይቀንሳል።ባክቴሪያ እንዳያድግም ይከላከላል።

6.ሻይ

ኖርማልም _ ሆነ የቅጠላቅጠል ሻሂ የአፍ ጠረን ለመከላከል ይጠቅማል።አረንጓዴ ሻይ ውስጥ ያለው አንቲኦከሲዳንት ፖሊፌኖልስ ባከቴሪያ አፋችን ውስጥ እንዳያድግ ይከላከላል።

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna