ኩላሊት በሽታ

ከባድ የኩላሊት በሽታ ረጅም አመታት ቀስ እያለ ኩላሊታችን እየነዳ ከጥቅም ውጭ የሚያደርግ በሽታ ነው ከጊዜ በሽተኛው ኩላሊት ሙሉ በሙሉ ስራ ያቆማል።ከባድ የኩላሊት በሽታ ወይም ከሮኒክ ኪድኒ ዲዚዝ ሰዎች ከሚያስቡት በማህበረሰቡ የተንሰራፋ በሽታ ነው።ስር እስኪሰድ ድረስ ለረጅም ጊዜ ሳይታወቅ ኩላሊታችን የሚያጠቃ ነው።ኩላሊት ጤናው ወርዶ በ25% ብቃት መስራት ሲጀምር በበሽታው እንደተያዙ ማወቅ የተለመደ ነው:: የኩላሊት መስራት ማቆም እየበረታ ሲሄድ ሰውነታችን ውስጥ አደገኛ መጠን ያለው ቆሻሻ እና ፈሳሽ ይከማቻል።ለዚህ በሽታ ያለው ህከምና የኩላሊትን መዳከም ለማቆም ወይም የሚዳከምበትን ፍጥነት ለማዘግየት የሚሞከርበት ነው።ይህንንም ማድረግ የሚቻለው የበሽታው መነሻ የሆነውን በሽታ ለማከም እና ለማስታግስ በመሞከር ነው።ከሮኒክ የኩላሊት በሽታ ቀስ በቀስ ዘግይቶ ኩላሊታችን የሚያዳከምበት በሽታ ነው።አንዱ ኩላሊት መስራት ቢያቆምም ሌላኛው ያለችግር ሊቀጥል ይችላል።ብዙ ጊዜ ህመሙ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እሰኪሲደርስ እንደታመምን ላናውቅ እንችላለን።ህመም መሰማት ከጀመረ በኋላ ብዙ ጊዜ ህመሙን ማከም አይቻልም።ለኩላሊት በሽታ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በየጊዜው የኩላሊታቸውን ጤንነት እየተመረመሩ ማረጋገጥ አለባቸው፡፡በሽታው እንዳለብን በጊዜ በማወቅ ራሳችንን ከከባድ ኩላሊት በሽታ ማዳን እንችላለን።

የከባድ ኩላሊት በሽታ ምልክቶች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፦

*የደም ማነስ

*ደም የተቀላቀለበት ሽንት

*የጠቆረ ሽንት

*ንቁ አለመሆን

* የሽንት መጠን መቀነስ

* የእግር ፣የእጅ ፣የቁርሚጭሚት ማበጥ

*የድካም ስሜት ፣የደም ግፊት *እንቅልፍ እጦት

* የሚያሳከከ ቆዳ መኖር

*የምግብ ፍላጎት መጥፋት

*ወንዶች ላይ ብልትን ማስነሳት መቸገር

*በሌሊት ቶሎ ቶሎ ለሽንት መመላለስ

*የትንፋሽ እጥረት

*ሸንት ላይ ፕሮቲን መገኘት በፍጥነት የሚቀያየር የሰውነት ከብደት

*እራስ ምታት

የኩላሊት በሽታ ደረጃዎች

ጂኤፍአር ሬት(GFR rate) የኩላሊት ጤንነት የሚታወቅበት መለኪያ መሳርያ ነው፡፡የጂኤፍአር መጠን የኩላሊታችን ጤንነት ይነግረናል።

*ደረጃ አንድ፦የጂኤፍአር መጠናችን ጤነኛ ነው ቢሆንም ግን የኩላሊት በሸታ እንዳለ ታውቋል።

*ደረጃ ሁለት፦የጂኤፍአር መጠናችን ከ90ሚሊሊትር በታች ሲሆን ኩላሊታችን ውስጥ በሽታ እንዳለ ታውቋል።

*ደረጃ ሶስት፦የጂኤፍአር መጠናችን ከ60ሚሊሊትር በታት ነው።

*ደረጃ አራት፡-የጂኤፍአር መጠናችን ከ30ሚሊሊትር በታች ነው፡፡

*ደረጃ አምስት፦የጂኤፍአር መጠናችን ከ15ሚሊሊትር በታች ነው።በዚህ ጊዜ የኩላሊት ስራ ማቆም ያጋጥማል።

አብዛኛው የኩላሊት በሸታ ታካሚ በሽታው ከደረጃ ሁለት አያልፍበትም ነገር ግን ህመሙ እንዳይባባስ ህክምና በማድረግ የኩላሊትን ጉዳት መከላከል ተገቢ ነው፡፡ስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች አመታዊ ህከምና ማድረግ አለባቸው።ሽንታቸው ውስጥ ያለውን የፕሮቲን መጠን አለመታመሙን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ በመለካት ኩላሊታቸው

ህከምና

ኩላሊት በሽታን የሚያድን መድሃኒት የለም ነገር ግን የተለያዩ ህከምናዎች በሽታውን ለመቆጣጠር _ አገልግሎት ላይ ይውላሉ።ከባድ ኩላሊት በሽታ ያላቸው ሰዎች ብዙ መድሃኒቶችን መውሰድ ይገባቸዋል።

የደም ማነስ ህከምና

ደም ማነስ ያለባቸው የኩላሊት በሽተኞች የደም ዝውውር እንዲኖር አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ይኖርባቸዋል።እንዲሁም በሽታው ያለበት ህመምተኛ የአይረን ንጥረ ነገር ያላቸውን ከኒኖች መውሰድ ወይም በመርፌ መልክ ማግኘት ይኖርበታል።

ፎስፌት ባላንስ

የኩላሊት ህመም ተጠቂዎች ሰውነታቸው በተገቢው ሁኔታ ፎስፌት ማስወገድ ይቸገራል።ታካሚዎች በአመጋገባቸው ላይ ፎሰፌት እንዲቀንሱ ይመከራሉ።የወተት ምርቶች ፣ቀይ ስጋ እንቁላልና አሳ ፎስፌት ንጥረ ነገር ስለያዙ አይመከሩም።

የደም ግፋት

የኩላሊት በሽታ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ብዙ ጊዜ የደም ግፊታቸው በፍተኛ ነው::ኩላሊትን ለመጠበቅ ደም ግፊትን መተቸቡ ያሰፈልጋል።

ቆዳ ማሳከከ

እንደከሎሮፊናሚን አይነት መድሃኒቶች የቆዳን ማሳከከ ያስታግሳሉ።ህመምን የሚያሰታግሱ መድሃኒቶች ኩላሊት መስራት ሲያቆምና _ ሰውነት _ ውስጥ _ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ሲከማቹ ታካሚው የማቅለሽለሽ ስሜት ይሰማዋል።በዚህ ጊዜ እንደሳይከሊዛይን አይነት መድሃኒቶች ህመምን ያስታግሳሉ።

የመጨረሻ ደረጃ ህከምናዎች

ኩላሊት አቅሙ ተሟጦ ከ0-15% ደረጃ መሰራት ሲጀምር ከላይ የተዘረዘሩት ህከምናዎች ብቻቸውን በቂ አይሆኑም ።የመጨረሻ የኩላሊት ደረጃ የደረሱ ታካሚዎች ሰውነታቸው ውስጥ የሚከማቸውን ቆሻሻ እና ፈሳሽ ያለ እገዛ መቋቋም አይችሉም።ታካሚው ለመኖር በህይወት ዲያለሲስ ያስፈልገዋል።የኩላሊት ህመም የመጨረሻው ደረጃ ካልደረሰ በስተቀር ዶክተሮች ዲያሊሲስና ንቅለተከላ _ ለማድረግ አይመርጡም።

ዲያሊሲስ

ዲያሊሲስ በማሽን የሚደረግ የሰውነት ቆሻሻ ማጣራት ስራ ነው።ሁለት አይነት የዲያሊሲስ አሰራር አለ።አንደኛው ሂሞዲያሊሲስ ነው፡።ይህ የዲያሊሲስ አይነት ደም ከሰውነታችን ፓምፕ እየተደረገ በሠውነታችን ውስጥ አልፎ እየተጣራ እንዲገባ የሚደረግበት _ ህከምና _ ነው።ሶስት ሰአት የሚወስድ ህከምና ነው።የህከምና _ ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህን ህከምና በተደጋጋሚ ማድረግ ለታካሚው ጤና ጥሩ ነው።

ሌሊኛው የዲያሊሲስ አይነት ፔሪቶኒያል ዲያሊሲስ ሲሆን የታካሚ ደም በራሱ ሆድ ውስጥ እንዲጣራ ይደረጋል።ሆድ ውስጥ በሚገባ ካቴተር ውስጥ የዲያሊሲስ ውህድ በመጨመር ቆሻሻናፈሳሽ እንዲወጣ ይደረጋል።

ኩላሊት ንቅለ ተከላ

ከኩላሊት መስራት ማቆም በቀር ሌላ ኩላሊትን የሚጎዳ በሽታ ለሌላቸው ታካሚዎች ኩላሊት ንቅለ ተከላ ከዲያሊሲስ የተሻለ አማራጭ ነው።ቢሆንም ግን ንቅለ ተከላ ከማድረጋቸው በፊት ታካሚዎች የዲያሊሲስን ማሽን እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።ኩላሊት ለጋሹ እና ተቀባይ ተመሳሳይ አይነት የሴል ሰርፌስ ፕሮቲንና አንቲቦዲ ሊኖራቸው ይገባል።ካልሆነ የተቀባዪ ሠውነት ኩላሊቱን ላይቀበለው ይችላል።ብዙ ጊዜ የዘመድ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የተሻለ ለጋሾች ይሆናሉ፡፡
ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna