የልብ ድካም ምንድን ነው?
Author: solomon
Date: 2025-01-03
የልብ ድካም ምንድን ነው?
አንድ ሰዉ ሮልበስ ድካም ሲያጋጥመው የደም ዝውውርን በሚያግድ ነገር አክስጅን የያዘ ደም ወደ ልብ መድረስ ሲያቅተው ነው።ይህ ማለት ወደልብ የሚደረግ የደም ዝውውር ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ ማለት አይደለም።ልባችን የሚደርሰው የደም መጠንም ትንሽ እንኳ ቢቀንስ የልባችን ጡንቻ ደም መርጨት ይቸገራል።የልብ ድካም ዋና መንስኤ የልብ ወይም የደም ባንቧ በሽታ ሲሆን ይህ ብዙ ጊዜ የሚፈጠረው የደም ቧንቧችን ውስጥ በሚፈጠር ክምችት የደም ቧንቧችን ሲዘጋ ነው፡፡ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን የደም ቧንቧችን ግድግዳ ላይ ፕላክ እንዲከማች ያደርጋል።እንደካልስየም ፣ፊብሪን እና የሴሎች ቆሻሻ የመሳሰሉ ነገሮች በደንብ ቧንቧ ሲያልፉ ክምችቱ ላይ አብረው ይጨመራሉ፡፡የልብ ድካም ምልክቶችን መከታተል ህይወትዎን ሊያድን ይችላል።አንድ ሲዲሲ የልብ ድካም ከሚያጋጥሟቸው ሰዎች ግማሾቹ ሆስፒታል ሊደርሱ ሲሉ ወይም ህክምና ክትትል ከማግኘታቸው በፊት ይሞታሉ፡፡
የልብ ድካም ስሜቶቹን ህመሙ ከማጋጠሙ ከቀናት በፊት አስቀድሞ ማወቅ ይቻላል፡፡ይህን ስሜት ችላ ሳንል ተገቢውን ህክምና በማድረግ ህይወታችንን ከአደጋ መጠበቅ እንችላለን።ብዙ ሰዎች ከልብ ድካም
አስቀድመው የሚመጡ ስሜቶችን ተከታትለው ቢመረምሩ ከበሽታው ሊድኑ ይችሉ ነበር።ከልብ ድካም በፊት የሚያጋጥም የደረት Vango ከፍተኛ ቀለል ያለ ህመም ነው።ብዙ ታማሚዎች ደረት ላይ ምቾት ያለመሰማት ብለው ይገልፁታል። ደረታችንን ላይ የሚሰማ ጫና ወይም ጥብቅ ያለ ስሜት ሊሰሙን የሚችሉ ስሜቶች ናቸው::
ሀ)እስቴብል ደረት፦ይህ የህመም አይነት የጠበበ የደም ቧንቧ ላይ ጫና የሚፈጥር ከባድ የአካል እንቅስቃሴ ባደረግን ቁጥር የሚሰማን የደረት ህመም አይነት ነው፡፡እረፍት ስንወስድ ህመሙ ይጠፋል።
ለ)አንስቴብል የደረት ህመም፦ ይህ የህመም አይነት በማንኛውም ጊዜ ሊፈጠር ይችላል።አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የለብንም።መነሻውን መተንበይ አይቻልም፡፡ህመሙ የሚቆይበት ጊዜ ከእስቴብል ህመም አይነት ይበልጣል።የደረት ህመም ከጊዜ ጊዜ ቀስ እያለ ስለሆነ እየጨመረ የሚመጣው ብዙ ሰዎች የልብ ህመም ሊሆን ይችላል ብለው አያስቡም፡፡ይልቅ የህመሙን መነሻ የዕድሜ መጨመር ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማድረግ ውጤት አድርገው ይፈሩጁታል።አንድ ሰው በልብ ህመም በሸታ መጠቃቱን የሚያሳዩ ነገሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦
1.የልብ ምት መቆራረጥ
አልፎ አልፎ የልባችን ምት ሊዘል ይችላል ወይም ከቁጥጥር ውጭ መርገብገብ ይጀምራል።እነዚህ ስሜቶች ፓልፒቴሽን ተብለው ይታወቃሉ፡፡ምቾት ማጣት፣ፍርሃትና የመደንገጥ ስሜት ኣብረውት ይኮታላሉ።ጭንቀት፣መደንገጥ፣መድሃኒትና ከፍተኛ መጠጥ እንዲሁም ቡና መጠጣትን ስሜቱ እንዲከሰት ሊያደ ይችላሉ ነገር ግን እነዚህን ነገሮች ትተን ስናርፍ የልባችን ቶርታ ወደቀድሞው ሁኔታ ይመለሳል ነገርግን ፓልፒቴሽን የልብ ህመም መገለጫ ሊሆንም ይችላል።ፓልፒቴሽን ጋር አብሮ የማዞር ስሜት ከተሰማን ጤናችን አደገኛ ሁኔታ ላይ ሊሆን ስለሚችል ተገቢውን ህክምና ማድረግ ያስፈልጋል።የልብ ትርታ መቆራረጥ ወይም ፓልፒቴሽን ለረጅም ጊዜ የሚሰማዎት ነገር ከሆነ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ ስሜቱ እየበረታ ከመጣ ወደ ህከምና ቦታ መሄድ ይኖርብዎታል፡፡
2.የትንፋሽ እጥረት
ማንኛውም አይነት አካላዊ እንቅስቃሴ ካደረጉ በኋላ ከፍተኛ የሆነ የትንፋሽ እጥረት ካጋጠመዎ የልብ ህመም መገለጫ ሊሆን ስለሚችል ተገቢውን _ ምርመራ _ ማድረግ ያሰፈልጋል።ደረጃ መውጣትም ሆነ ቀላል እንቅስቃሴ ትንፋሽዎን ሊያሳጥር ይችላል።በልብ በሽተኞች ላይ በተደረገ ጥናት እንደሚያመላክተው የትንፋሽ እጥረት የሚያጋጥማቸው ህመምተኞች የሞት እድላቸው በንፅፅር የሰፋ መሆኑን አረጋግጧል።
3.ከፍተኛ ላብ
የደም ቧንቧ ወደ ልብ ደም ማስተላለፍ ሲቸግረው ማንኛውም አይነት የአካል እንቅስቃሴ ልብን ጫና ውስጥ ይከታል።እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ሠውነትዎ ሙቀቱን ለመቆጣጠር ሙቀትና ላብ ያመነጫል።የላብን መጨመር ብዙ ሰዎች እንደጥንቃቄ ምልከት አይወስዱትም።በትንሽ እንቅስቃሴም የላብ መጠንዎ መጨመሩን ካስተዋሉ ልብዎ በተገቢው መጠን እየረጨ እንዳልሆነ እና ስራውን ለመስራት ከፍተኛውን ሐይል እንደሚያስፈልገው እየነገረዎት ይሆናል።
4.ማቅለሽለሽ
የደም ቧንቧዎ መዝጋት ሲጀምር ልብዎ ደም ለመርጨት ይከብደዋል።ይህም ሁኔታ ደም ወደጨጓራ በተገቢዉ ሁኔታ እንዳይሄድ ያደርገዋል።ይህ ሲከሰት የማቅለሽለሽ ስሜት ይፈጠራል። የማስታወከና የሆድ ህመም ከላብና ማዞር ጋር የሚያጋጥምዎ ከሆነ የተዘጋ የደም ቧንቧ ምልክት ሊሆን ስለሚችል ዶክተር ጋር መሄድ አለብዎ፡፡
5.መድከምና ማዞር
ማንኛውም አይነት የልብ ድካም ሰውነትዎን ያደክማል።ልብ ስራውን ለመስራት ከፍተኛ ሃይል ሲያስፈልገው የመድከም ስሜት ይሰማወታል።ትንሽ ወይም መጠነኛ እንቅስቃሴ አድርገው የድካም ስሜት ከተሰማዎ የልብ ሐኪም ማማከር ተገቢ ነው፡፡
6.ብልትዎን ለግንኙነት ማስነሳት ከከበደዎ
ለተከታታይ ቀናት ብልትዎን ለግንኙነት ማስነሳት ከተቸገሩ የልብ ድካም ምልክት ሊሆን ይችላል።ብልታችን ብዙ ጊዜ በደም ዝውውር _ መገታት የመጀመሪያ ተጠቂ ነው፡፡የወንድ ብልት የሚቆመው በውስጡ ደም ስለሚሞላ ነው።የተዘጋ የደም ቧንቧ
ይህ እንዳይከሰት ያደርጋል።የብልት መዳከም ከ3-5 ዓመት ውስጥ ለሚፈጠር የልብ ህመም ጠቋሚ ይችላል። ያለምንም ሌላ ምክንያት ብልትዎን ማስነሳት ከተቸገሩ የልብ በሽታ ተጠቂ ሊሆኑ ስለሚችሉ ተገቢውን ክትትል ማንሩ ተገቢ ነው።
7.የጆሮ መጨማደድ
ጆሮዎ ላይ የሚፈጠር መጨማደድ የደም ቧንቧ መጨማደድ ምልከት ሊሆን ይችላል።እ.ኤ.አ በ2006 የታተመ ጥናት እንደሚናገረው የልብ በሽታ ካጋጠማቸው 520 ሰዎች ውስጥ 55% የጆሮ መጨማደድ እንዳጋጠመው ይናገራል።የጆሮ ላይ መጨማደድ ካጋጠመዎ የደም ቧንቧ መዘጋት ጠቋሚ ሊሆን ስለሚችል ተገቢውን ህክምና ማድረግ ያሰፈልጋል፡፡
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna