ትርፍ አንጀት በሽታ
Author: solomon
Date: 2024-12-25
ትርፍ አንጀት
በትልቁ አንጀት መጀመሪያ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀኝ የሆዳቸን የታችኛው ከፍል ይገኛል፡።ቁመቱም እሰከ 9 ሳንቲ ሜትር ሊደር ይችላል።ወፍራም ግድግዳም አለው።ትርፍ አንጅት ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለው ለረጅም ጊዜ ሲታመን የኖረ ሲሆን አ.ኢ..አለ 2007 በተመራማሪዎች በተደረገ ጥናት ግን ጥቅም ተደርሶበታል።እንደተመራማሪዎች ከሆነ ትርፍ አንጀት ጠቃሚ የሚባሉትን ባክቴሪያዎች የሚያስጠልል ሲሆን እንዳለው እንዲደምር መቀላቀልና አጣዳፊ ተቅማጥ ባሉት የጤና መጓደል ጠቃሚ ባክቴሪያዎች ካስጠለላቸው በማውጣት በጠፉት የሚተካ መሆኑን መስከረዋል።ለትርፍ አንጀት በሽታ አብዛኛውን ጊዜ የቀዶ ጥገና ህክምና የግድ ስለሚያስፈልግ ህመምተኛን በአስቸኳይ ህክምናውን ማግኘት ወደሚችልበት ሆስፒታል መውሰድ ያስፈልጋል።የትርፍ አንጀት በሽታ የሚከሰተው ከትልቁ አንጀት ጋር የተጣበቀው ጣት የመሰለው ተቀጥላ ወይም ትርፍ አንጀት ሲቆስል ነው፡፡የሚገኘውም በታችኛው የሆድ ክፍል በቀኝ በኩል ሲሆን አንዳንድ ጊዜም ያበጠ የትርፍ አንጀት ሲፈነዳ የሆድ ብግነት ያስከትላል።የአንጀት አቃፊ በመግልና በበሽታ ተዋህሲያን ተበክሎ ሲቆስል የሚደርስ አደገኛ የሆድ ህመም ብግነት ይባላል።
የትርፍ አንጀት በሽታ ምክንያቶች
በባለሙያተኞች ጥናት መሠረት ለትርፍ አንጀት በሽታ ምክንያት ናቸው ተብለው የሚጠቀሱ ሁለት ምክንያት አሉ።
1.በአንዳች በሽታ ልከፍት ምከንያት በሆድ ውስጥ የሚፈጠር ማመርቀዝ፦ በሆድ ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የሚያጋጥም ልከፍት ወደ ማመርቀዝ ደረጃ ሲደርስ ያለ ሁኔታ በመስፋፋት ወደ ትርፍ አንጀት በመዝለቅ የሚያጋጥምና
2.ቁራጭ ሰገራ በትርፍ _ አንጀት ውስጥ _ _ ተቀርቅሮ መቅረት፦ ደረቅና ጠንካራ የሆነ ቁራጭ ሰገራ በትርፍ አንጀት ውስጥ በሚቀረቀርበት ወቅት በሰገራው ውሰጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች የትርፍ አንጀቱን በመመረዝ እንዲታሙም ስለሚያደርጉ ነው የሚል ነው።
የትርፍ አንጀት ምልክቶች፦
*የማያቋርጥና እየጨመረ የሚሄድ የሆድ ህመም
*ህመሙ በመጀመሪያ እምብርት
አካባቢ ይጀምርና ወዲያውኑ ወደታችኛው ቀኝ የሆድ ክፍል ይዞራል።
*መጠነኛ ትኩሳት የሆድ ድርቀት ፣ተውከት ይኖራል፣የምግብ ፍላጎት ይቀንሳል።
*እንደጦር የሚወጋ ህመም ከተሰማዎ የትርፍ አንጀት ህመም መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ትርፍ አንጀት መሆኑ ጥርጣሪ ከገባን፦ * በአስቸኳይ የቀዶ ጥገና ሕከምና ሊያገኝ ወደሚችልበት ሆስፒታል መላከ
*የሚበላም ሆነ የሚጠጣ ነገር መሰጠት የለበትም።ሆዱንም ማጠብ አይገባም ።በሽተኛው ከሰውነቱ ብዙ ፈሳሽ ወጥቶ ድካም ከተሰማው ጥቂት ውኃ ወይም ስኳርና ጨው የተቀላቀለበት ፈሳሽ ፉት እንዲል በማድረግ መርዳት ተገቢ ነው::
*ግለስቡ ከትክሻው በግማሽ ቀና ብሎ እንዲቀመጥ ማድረግ ለህመምተኛው ምቾትን ሊሰጥ ይችላል።
ያም ሆነ ይህ በምግብ እንሽርሽሪት መዋቅር ላይ ከሚያጋጥሙ በሽታዎች መካከል አብዛኛዎቹ በተዛባ አመጋገብና አኗኗር ዘይቤ አማካኝነት የሚከሰቱ ናቸው፡፡አብዛኛው ህዝብም በነዚህ በሽታዎች ይጠቃል።በተለይ የጨጓራ ህመም የብዙ ሰዎች የጤና ችግር ሲሆን ፣የሆድ ድርቀትና ትቅማጥ የሚያስከትል የውስጥ ደዌ የጤና ችግርም በስፋት ይታያሉ።አብዛኛውን ጊዜ የምግብ እንሽርሽሪት ስርዓት ላይ የሚያጋጥሙንን የጤና ችግሮች የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል መቆጣጠር የሚቻል ሲሆን በዚህ ዘዴ መቆጣጠር የማይቻሉትን ደግሞ ህክምናን በመከታተል ፈውስ ማግኘት ይችላሉ፡፡
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna