የሀሞት ጠጠር
Author: solomon
Date: 2024-12-20
የሃሞት ጠጠር
የሃሞት ጠጠር ለስርዓተ ምግብ መፍጨት የሚያገለግሉት ፈሳሾች በመጠጠር በሃሞት ከረጢት ውስጥ በሚጠራቀሙበት ወቅት የሚከሰት ነው።የሃሞት ከረጢት ሾጠጥ ያለች በቀኝ ጎናችን ከጉበታችን ስር የምትገኝ አካል ናት።
የህመም ምልከቶች
የሃሞት ጠጠሩ በሃሞት መተላለፊያ ቱቦ ውስጥ ከተሳካና ቱቦውን ከዘጋው የሃሞት ጠጠር ህመም ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ።እነርሱም፦
*ድንገታዊ የሆነና እየጨመረ የሚመጣ በቀኝ የላይኛው ሆድዎ አካባቢ ህመም መሰማት
*ድንገታዊ የሆነና እየጨመረ የሚመጣ ጨጓራዎ ባለበት አካባቢ በጡትና ጡት መካከል ባለው አጥንትዎ መጨረሻ ህመም ሲሰማ
*ትኩሳትና ብርድ ብርድ የማለት ስሜት ካለበዎ
*አይኖርም ወይም ቆዳዎ ወደ ቢጫነት ከተለወጠ
*የሆድ ህመምዎ አላስቆም አላስቀምጥ ካለዎ
*በሁለቱ ትከሻዎ መሃል በጀርባዎ ህመም መሰማት ናቸው፡፡
በመሆኑም የሃሞት ጠጠር ህመም ከደቂቃዎች እስከ ተወሰነ ሳዓታት ድረስ የሚቆይ በመሆኑ የህመም ምልክቶች ካለበዎ ባስቸኳይ የህክምና ባለሙያዎችን ያማክሩ፡፡
ለሃሞት ጠጠር መከሰት ምክንያቶች፦
ለሃሞት ጠጠር መከሰት ምክንያቶች በትክክል ምን እንደሆነ አይታወቅም ነገር ግን የህክምና ባለሙያዎች ለጠጠር መፈጠር ምክንያት ይሆናሉ ያሉትን እንዲህ አስቀምጠውታል።
*ሃሞትዎ ብዙ ኮሌስትሮል ካለው፡-ኮሌሰትሮሉ ከመጠን ካለፈ በመጀመርያ ወደ ክርሲታልነት ከተለወጠ በኋላ የሃሞት ጠጠር እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
*በሃሞትዎ ውስጥ በጣም ብዙ ቢሉሩቢን የሚባለው ኬሚካል ካለ፦የቢሊሩቢን ኬሚካል በብዛት መገኘት የሃሞት ጠጠር እንዲፈጠር ያደርጋል።
*ሃሞት በአግባቡ _ ከሃሞት _ ከረጢትዎ ውስጥ የማይወገድ ከሆነ፦የሃሞት ከረጢትዎ ሃሞትን በአግባቡ የማታሰወግድ ከሆነ ሃሞት ከመጠን በላይ ሰለሚወፍር ለሃሞት ጠጠር መፈጠር
ምከንያት ይሆናል ሰለሆነም ለሃሞት ጠጠር መፈጠር ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
*ሴት መሆን
*ከመጠን በላይ ክብደት መኖር
*ነፍሰጡር ሴቶች
*ስብነት የበዛባቸውን ምግቦች ማዘውተር
*ኮሌስትሮል የበዛባቸውን ምግቦች ማብዛት
*የፋይበር ይዘት የሌላቸው ወይም አንስተኛ ይዘት ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር
*በቤተሰብ ውስጥ የሃሞት ጠጠር ያለባቸው መኖር
*የስኳር ህመም
*ዕድሜዎ አርባ ዓመትና ከዚያ በላይ መሆን
*ክብደት የሚቀንሱ ሰዎች
*ኮሌስትሮልን _ ለማውረድ _ ሆርሞን ያለባቸው መድሃኒቶችን መውሰድ ናቸው፡፡
የሃሞት ጠጠር ህክምና
ጠጠሩን ለማሰወገድ የሚደረግ ቀዶ ህክምና፦የሃሞት ጠጠር ህመም በተደጋጋሚ ሊከሰት ስለሚችል የህክምና ባለሙያዎች የሃሞት ከረጢትዎ በቀዶ ጥገና እንዲዎጣ ሊያደርግልዎ ይችላል::
የሃሞት ጠጠርን መከላከል
የሃሞት ጠጠር ህመም በተለያዩ ምክንያቶች ሊመጣ እንደሚችል ቀደም ሲል በስፋት ከላይ ተገልጿል ይሁን እንጅ ይህን በሽታ ቀድመን ለመከላከልና ብሎም ለመቀነስ የሚከተሉትን መንገዶች በመተግበር መፍትሄ ማግኘት ይቻላል፡፡
*ያመጋገብ መርሃ-ግበርዎን ያለመዝለል፦ለብዙ ሳዕታት ሳይመገቡ መቆየት ለሃሞት ጠጠር የመጋለጥ ዕድልዎን ይጨምራል
*ክብደትን ቀስ በቀስ መቀነስ፦ክብደትን ሲቀንሱ ቀስ በቀስ መሆን አለበት ።ክብደትን በፍጥነት መቀነስ ለሃሞት ጠጠር መፈጠር ምክንያት ሊሆን ይችላል።በሳምንት አንድ ኪሎ ግራም ለመቀነስ ማቀድ
*ጤናማ ከብደትን መጠበቅ፦ ከመጠን በላይ ውፍረትንና ክብደት መኖር ለሃሞት ጠጠር መከሰት ምክንያት ናቸው፡፡የሚመገቡትን የካሎሪ መጠን በመቀነስና የሚሰሩትን አካል ብቃት እንቅስቃሴ በመጨመር ክብደትዎን አመጣጥኖ መጠበቅ ያሻል።አንዴ ጤናማ ክብደት ላይ ከደረሱ በኋላ ጤናማ አመጋገብ መከተልና መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ክብደትዎን መጠበቅ ያሰፈልጋል፡፡
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦ https://t.me/kidusmikaelhikmna