የጀርባ ህመም
Author: solomon
Date: 2024-12-06
የጀርባ ህመም
አብዛኛውን ጊዜ በእድሜ ፣በአደጋ እንዲሁም ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የጀርባ ህመም ይከሰታል።ታድያ ከዚህ ህመም ለመዳን በቀላሉ በቤታችን ሁነን የተለያዩ ዘዴዎችን መጠቀም እንችላለን፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦
ሀ) ጀርባችንን ከቅዝቃዜ መጠበቅ፦ለረጅም ጊዜ ሲያሰቸግረን የኖረ የጀርባ ህመም ካለብን ሁሌም ጀርባችንን ብርድ እንዳይመታው ተጠንቅቀን ብርድ እንዳይመታው መጠበቅ አለብን፡፡ለዚህም ይረዳ ዘንድ አዘውትረን ትኩስ የሆኑ ምግቦችብቻ መመገብ ይመከራል፡፡
ለ)ነጭ ሽንኩርት መመገብ፦በዕየለት ምግባችን ውስጥ ነጭ ሽንኩርት እንዲገባ አድርገን መጠቀም ለጀርባ ህመም ፍቱን መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
ሐ)በሶቢላ፦ _ ለጀርባ ህመም _ ፍቱን መድሃኒት መሆኑ ተነግሯል።በሶ ቢላውን ውሃ ውስጥ በመጨመር በደንብ እንዲፈላ ካደረግን በኋላ ለብ እንዲል አድርገን ጨው ጨምሮ በመጠጣት የጀርባ ህመምን ማከም ይቻላል።
መ)ባህር ዛፍ እና በሰናፍጭ ዘይት ጅርባን መታሸትም የጀርባ ህመምን ለማከም ይይረዳል።
ሠ) ማንኛውም ዓይነት መታሻ በመጠቀም ጀርባን መታሸትም ህመሙን ለማስታገስ ይጠቅማል፡፡
ረ)ጠበቅ ያለ ፍራሽ ላይ መተኛት የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖረን በማድረግ የጀርባ ህመምን ይቀንሳል፡፡
ሰ)የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግም የጀርባ ህመምን ለማከም ወይም ለመቀነስ የሚረዳን ዘዴ ነው።
ሸ) አቀማመጥን ማስተካከል፦በምንሰራበት ቦታ ወይንም በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ በምንቀመጥበት ጊዜ ለጀርባችን የሚመቹ መቀመጫዎች ላይ ተስተካክሎ መቀመጥ ሌላኛው የጀርባ ህመምን ከሚቀንሱ መፍትሄ ውስጥ አንዱ ነው።
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦https://t.me/