የወር አበባ
Author: solomon
Date: 2024-11-29
የወር አበባ
የወር አበባ ማለት አንድ ሴት ለአቅመ ሄዋን ከደረሰች ማለትም በዕድሜዋ ከ14-16 አመት በላይና ብሎም እስከ 50 አመት እድሜ ድረስ ከጭንቅላት ጀምሮ እሰከ ማህፀን ድረስ ባሉ የተለያዩ የሰውነት አካሏ በመታገዝ በየወሩ የምታስተናግደው ተፈጥሯዊ ዑደት ነው።አመጣጡም ከ21-35 ቀን ባሉ ቀናት ውስጥ ሲሆን በመጣበት ወቅት ከሁለት እሰከ ስምንት ሳምንት ቀን ሊቆይ የሚችል ሲሆን መጠኑም በአማካይ ከ30 ሚሊ ሊትር እስከ ሰማንያ ሚሊ ሊትር ያለምንም ሕመም ወይንም መሰተጓጉል የሚፈስ ከሆነ ይህ ጤናማ አፈሳሰስ ይባላል።
የወር አበባ መዛባት የሚከሰተው በትክክለኛው ጊዜውን ጠብቆ ባለመምጣቱ ነው፡፡ አንዲት ሴት የወር አበባዋ መጠኑን ከጨመረ ከድሮው በጣም ቀላ ካለ ወይንም ወፈር ያለ ሁኖ ቀደም ሲል ትጠቀምበት የነበረውን ሞዴስ መጠን ከፍ ሲያደርግ ወይንም ቶሎ ቶሎ እንድትቀይር ሲያስገድዳት ሁኔታው ወደ መዛባት ማምራቱን ያሳያል።የወር አበባ መዛባት ምክንያት ምንድን ነው ለሚለው ጥያቄ ምላሹ የተለያዩ ናቸው፡፡አንደኛው ኦርጋኒክ የሚባል በማህፀን ውሰጥ የሚታይ የማህፀን ችግር መመልከት ብንጀምር በማህፀን ግድግዳ ላይ የሚበቅል ማዮማ የሚባለው ዕጢ እና ሌሎችም ዕጢዎች የወር አበባን ከሚያበዙ ችግሮች መካከል ናቸው፡፡ሌላው በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገሮች ከአባላዘር በሽታዎች ጋር ተከትለው የሚከሰቱ የኢንፌክሽን አይነቶች እንዲሁም የማህፀን የቆየ ኢንፌክሽን እና በዕድሜያቸው ከፍ ያሉ ወይም ልጅ የሆኑ ሴቶች የማህፀን እንቁላል ማፍሪያ ወይንም ኦቫሪን ቲዩመር የሚባሉ ሆርሞን በሚያመርቱት አማካኝነት የወር አበባን እጅግ እንዲበዛ ያደርጉታል ይሁንና የሚገርመው ነገር የወር አበባ ከሌላው ህመም ጋር የሚገናኝ መሆኑ ነው፡፡
የወር አበባ መዛባት ከውስጥ ደዌ በሽታዎች ጋር ይገናኛል በመሆኑም የተለያዩ የውሰጥ ደዌ በሽታዎች ለችግሩ በምክንያት ይጠቀሳሉ።
የወር አበባ መርጋትና አለመርጋትን ከሚቆጣጠሩት የሰውነት ከፍሎች ውስጥ ለምሳሌ የቆየ የጉበት በሽታ ያለባት ሴት ኢሰትሮጅን የተባለው ንጥረነገር በትክክል እንዳይመረት ስለሚያደርግ የወር አበባን ሊያዛባ ይችላል።ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ያለባቸው ሴቶችም በዚህ ችግር እንደሚጠቁ የታወቀ ነው፡፡ከእንቅርት ጋር በተያያዘ የሚከሰት ታይሮድ እንዲሁም የደም መርጋት ችግር ጋር በተያያዘ የወር አበባ መዛባት ሊከሰት ይችላል።ባጠቃላይ የወር አበባ መጠን መብዛትና ጊዜውን አለመጠበቅ ሊከሰት የሚችለው በማህፀን የውሰጥ ችግር ወይንም እንቁላል ማምረቻ አካባቢ እና በሌሎችም የውስጥ ደዌ እንዲሁም የአካል መታወክ ሊሆን እንደሚችል ግልፅ ነው።ባጠቃላይ የወር አበባ መዛባትን ችግር ስንመለከት ከራሱ ከማህፀን ወይንም ከእንቁላል ማፍሪያው ሊሆን ስለሚችል አንዲት ሴት የወር አበባዋ በዛ ብሎ ስትመለከት ወደህክምና ይገባታል።የወር ባለሙያ በመቅረብ አበባ መዛባት ይገናኛል።
በመውለጃ ምክንያቱን ማወቅ ከእርግዝና ጋር ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች ሊያውቁት የሚገባው ነገር ከእርግዝና ጋርም በተገናኘ የወር አበባ መዛባት ሊከሰት እንደሚችል ነው።እንዲሁም ከወሊድ ወይም ውርት ከተከሰተ በኋላ የወር አበባ መዛባት ሊከሰት ይችላል ምክንያቱም በወር አበባ ዑደት ወቅት የሚፈልቁ ሆርሞኖች በትክክል ጊዜያቸውን ጠብቀው ባለመምጣታቸው እና አንዱ ተቀብሎ ወደሌላኛው የሚያስተናግድበት ሂደት በመሰናከሉ ምክንያት ነው።አንዳንዴ ደግሞ ከወር አበባ መጠን ባለፈ ለመዛባቱ በምክንያትነት የሚጠቀስ ባልተለመደ ሁኔታ እንዳሰኘው በ10 ወይም በ 15 ቀን እየተመላለሰ ድንገት ሊታይ ይችላል።የዚህም ምክንያቱ ከዕድሜ ጋር በተያያዘ በተለይም ዕድሜያቸው ትንሽ ገፋ ያሉ ሴቶች ላይ የሚከሰት የማህፀን በር ወይንም የማህፀን ካንሰር ወይንም በማህፀን ግድግዳ ውስጥ ከሚበቅሉ ዕጢዎች መንሴነት የወር አበባ መዛባት ሊከሰት ይችላል።ብዙውን ጊዜ ዕድሚያቸው ወደማረጥ የደረሱ ሴቶች የወር አበባ ጊዜያቸው ከ35 ቀን በላይ 40 እና ከዚያም በላይ ቆይቶ ሊመጣ ይችላል።ይህን አይነት ችግር የሚገጥማቸው ሴቶች በአብዛኛው ከሆርሞን መዛባት ወይንም ደግሞ ከክብደት ጋር በተያያዘ ወይንም በህይወታቸው በጣም በሚያስጨንቅ ሁኔታ የሚኖሩ እንዲሁም የቆዩ ኢንፌክሽኖች ያለባቸው ሴቶች የወር አበባ መዛባትን ሊያሰከትልባቸው ይችላል።እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች ሲከሰቱ ከሃኪም ጋር መመካከር ያስፈልጋል።የወር አበባ መጠን ማነስ ለወር አበባ መዛባት አስተዋፅኦ አለውን?መልሱ አወ ነው። አንዳንድ ግዜ መጠኑ በጣም ያነሰ እንዲሁም በሚፈስበት ቀንም ከሁለት ቀን ያነሰ ሊሆን ይችላል።
ለዚሁም ምክንያት ከሚሆኑት መካከል በማህፀን ግድግዳ የወር አበባን ዑደት የሚያስተናግደው ከፍል ችግር ሲያጋጥመው ኢንፌክሽኖች ወይንም የወር አበባ መቆጣጠሪያ ክኒኖችን ለረጅም ጊዜ ተጠቅመው ከሆነ ሆኖ ከታይሮድ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የሚከሰት ነው ስለዚህ አንዲት ሴት የወር አበባ መዛባት ሲያጋጥማት መውሰድ ያለባት እርምጃ መንስኤው ምን እንደሆነ ለማወቅ ወደህክምና ተቋም በመሄድ የህክምና ባለሙያውን ማማከር፤ተገቢውን ምርመራና ሕክምና ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦https://t.me/