ኪንታሮት
Author: solomon
Date: 2024-11-25
ኪንታሮት
ስሙ ብንጀምር በአማረኛ የተሰጠው "ኪንታሮት"የሚል ቃል ትከከለኛ ሁኔታውን የሚገልፅ አይደለም።ምክንያቱም የጤና ችግሩ የሚከሰተው በፊንጣጣና በታችኛው ሸለላ አንጀት አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች መላላትና መለጠጥ እንዲሁም በደም በመወጠር ማበጥና መግተርተር ነው፡፡ይህ ሁኔታ ሰዎች እግር ላይ ተቆጣጥሮ እና አብጦ እንደሚታየው ግትርትር ደም መላስ በሽታ ነው፡፡ኪንታሮት መነሻ ምክንያቱ ብዙ ሊሆን ይችላል።አብዛኛውን ጊዜ ግን በደም ስሮች ላይ በሚፈጠር ጫና የሚከሰት ነው።በመሆኑም በወሊድ ወቅት የሚኖረው ምጥ ወይም አይነምድር _ ለመፀዳዳት ሲባል የሚደረግ ማማጥ ሽለላ አንጀትና በፊንጢጣ አካባቢ ግፊት የሚጨምር በመሆኑ ሊፈጠር ይችላል።የጠቀስናቸው እንቅሰቃሴዎች በፊንጢጣ እና በትልቁ አንጀት አካባቢ ካሉት ደም መላሽ ቧንቧዎች የሚመለሰውን ደም ሊያግዱ ይችላሉ።በዚህ መንገድ የፊንጢጣ ኪንታሮት ተብለው የሚጠሩ ግትርትር የደም መላሽ ቧንቧዎች ይፈጠራሉ፡፡ከፍተኛ ስቃይም ሊያሰከትሉ ይችላሉ።ይህ ሁኔታ በሽለላ አንጀት ውስጥ የሚፈጠር ወይም በፊንጢጣ ቆዳ ስር የሚፈጠር ሊሆን ይችላል
በመሆኑም በሁለት ተከፍሎ የውሰጥ እና የውጭ ኪንታሮት ይባላል። ሀ)የውስጥ ኪንታሮት፦የውስጥ ኪንታሮት የሚገኘው በሸለላ አንጀት ውስጥ ሲሆን በግልፅ የማይታይ ነው በመሆኑም ብዙም ምቾት የመንሳት ነገር ላይኖር ይችላል ነገር ግን በምንፀዳዳበት ወቅት በሚደርስበት ጫና ጉዳት ስለሚገጥመው ደም መፍሰስና ህመም ሊከሰት ይችላል።የውስጥ ኪንታሮት በማማጥ ወቅት
በሚደርስበት ጫና ወደ ፊንጢጣ አሞጥሙጦ ሊወጣ ይችላል።ይህ ሁኔታ ሲያጋጥም ከፍተኛ ህመም ሊከሰት ይችላል።
ለ)የውጭ ኪንታሮት፦የውጭ ኪንታሮት ደግሞ የሚፈጠረው በፊንጢጣ ቆዳ ስር ሲሆን ሊያብጥ ፣ሊያሳከከና የደም መፍሰስ ሁኔታ ሊኖረው ይችላል፡፡አንዳንዴ ደግሞ በረጋ ደም የሚፈጠር ኪንታሮት ይኖራል።ይኸውም በውጨኛ ፊንጢጣ ደሃ ደም ስሮች ውስጥ ደም በመሰብሰብ ሊረጋ ይችላል።ይህም ውጠ ጤት እርጉዝ ደም ይባላል።ይህ _ ሁኔታ ሲፈጠር እብጠት፣ከፍተኛ ህመም፣መለብለብና እንደመጅ ያለ ያለ በፊንጢጣ አካባቢ ደድሮ የሚቀር ሊሆን ይችላል። የኪንታሮት በሽታ ምልክቶች
የኪንታሮት በሽታ የተለያዩ ምልክቶች የሚያሳይ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፦
*ስንፀዳዳ ምንም ህመም የለለው ደም መፍሰስ
*በፊንጢጣ አካባቢ የማሳከክና የመቆጣት ሁኔታ
*በምንፀዳዳበት ወቅት ከፍተኛ ህመም መሰማት
*ስንቀመጥ ሕመምና ምቾት ማጣት
*ሰገራ በሚጠረግበት ጊዜ በመጥረጊያው ላይ የደም እንጥፍጣፊ ማየት
*በንክኪ ወቅት ከፍተኛ ህመም መሰማት
*በሽንት ቤት መቀመጫ ላይ የደም ጠብታዎች ማየት
*በፊንጢጣ አካባቢ የተቆጣጠሩ እብጠቶች መታየት
*በፊንጢጣ አካባቢ እንደመጅ ያለ እብጠት ሊፈጠር ይችላል
ይህ በሽታ የሚፈጠረው በሸለላ አንጀትና በፊንጢጣ አካባቢ ማለትም በዓይነምድር መውጪያ የአንጀት ክፍል የሚገኙ የደም ስሮች ከሚገባው በላይ በመላላትና በመለጠጥ እብጠት ሲፈጥር ነው፡፡በደም _ ስሮች ውስጥ ደም እንደሚዘዋወሩ መጠን በተለጠጡ፣በላሉ ደም ስሮች ውስጥ የሚተላለፍ ደም ግፊት በመፍጠር የደም ስሮች የበለጠ በመለጠጥ እንዲወጠሩ ያደርጋል።በዚህ መንገድ የተፈጠረ እብጠት ለመቀመጥም ሆነ ለመፀዳዳት ችግር በመፍጠር ህመም ያስከትላል።
የኪንታሮት ጤና ችግር እንዳለብን እንዴት ይታወቃል?
ደም ከሰገራ ጋር ወይም በፊንጢጣ መውጣት ከኪንታሮት በተጨማሪ ከአንጀት የጤና ችግሮች ጋር ተያያዥነት ያለው ምልክት ሊሆን ይችላል በመሆኑም ይህ ዘዴ ብቸኛ ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም ነገር ግን ከሰገራ ጋር የሚታይ ደም የኪንታሮት ሁኔታ መኖሩን ሊያመለከት ይችላል።ከደም በተጨማሪ ሃኪሞች አኖስኮፒ እና ሴግሞይዶስኮፒ የተባሉ መሳርያዎችን ተጠቅመው ምርመራዎችን በማድረግ የኪንታሮት ሁኔታ መኖሩን ሊያዉቁ ይችላሉ፡፡አኖስኮፒ ፊንጢጣና አካባቢውን ለማየት የሚያሰችል ሲሆን ሴግሞይዶስኮፒ ደግሞ በፊንጢጣ አድርጎ እስከ ትልቁ አንጀት ክፍል አርቆ ማየት የሚችል መሳርያ ነው፡፡አነዚህ መሳሪያዎች የካሜራ ዓይን ያላቸው በመሆኑ ችግሩ ያለበትን የአካል ክፍል በደንብ የሚያሳዩ ናቸው፡፡
የሚሰጠው ህክምና ምንድን ነው?
የኪንታሮት _ ህመም አብዛኛውን ጊዜ ከአኗኗር ዘይቤ ጋር የሚያያዝ ሁኔታ አለው በመሆኑም ችግሩ ሲያጋጥም በመጀመሪያ መፈተሽ ያለብን እሱን ነው።ለምሳሌ የሆድ ድርቀት ሊያመጡ የሚችሉ ምግቦችን የምናዘወትር ከሆነ፣በአንድ ቦታ ለረዥም ሠዓት ያለእንቅስቃሴ የምንቀመጥ ከሆነ፣የዕለት ኑሯችን ውጥረት የበዛውና ሌሎች ተመሳሳይ ዝንባሌዎች ካሉን እነሱን በማስተካከል ልዩነቶችን ማየት አለብን። day
በህከምናው የተለያዩ መድሃኒቶች ሊታዘዙና ሊወሰዱ ይችላሉ።ሃኪምና የመድሃኒት ባለሙያተኛነትን በማማከር ሊወስዱ ይችላሉ።የጤና ችግር እየተባባሰ ከሄደ ደግሞ እስከ ቀዶ ጥገና የሚደርሱ ህከምና ሊያሰፈልግ ይችላል።ከቀዶ ጥገና በፊት የሚቋጥረውን እብጠት በሙቀት ሐይል በማኮማተር ለመቆጣጠር የሚያሰችል ሕክምና ያለ ሲሆን እንደ አማራጭ ሊቀርብ ይችላል።በቀዶ _ ህክምና _ ሁለት አይነት ህክምናዎች ሊሰጡ ይችላሉ።አንደኛው ያበጠውን አካል በጎማ ማሰር ሲሆን ሌላኛው ደግሞ አካሉን ቆርጦ _ _ ማውጣት ሊሆን ይችላል።የኪንታሮት በሸታ በብዙዎቹ ላይ የሚከሰት የጤና ችግር ሲሆን ከአራት ሰዎች ሶስቱ በህይዎት ዘመናቸው ያጋጥመዋቸዋል ተብሎ ይገመታል።በተለይ ህመሙ ለረጅም ሰዓት በሚቀመጡ ሠዎች ላይ ሊበረታ ይችላል።የኪንታሮት በሽታ መታከም የሚችልና የአኗኗር _ ዘይቤ _ ላይ _ ለውጦችን በማድረግ ልንከላከለው የምንችለው ነው፡፡ይህን የጤና ችግር ለመከላከል ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡
ከጥንቃቄ እርምጃዎች መካከል ዋንኛዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
*ከጥጥ የተሰሩ የውስጥ ሱሪዎችን መልበስ
*ንፅህናን በዕየለቱ መጠበቅ
*ችግሩ ያለበትን አካባቢ ከማከከ መቆጠብ
*የሆድ ድርቀት ሲያጋጥም ምጥ ሊያባብስ ስለሚችል በፕሮቲን የበለፀጉና ሰገራን የሚያለሰልሱ ምግቦች መመገብ ፣ካልሆነም የሰገራ ማለስለሻ መድሃኒት መጠቀም
*ልስልስ ያላሉና ሊቧጥጡ የሚችሉ የሰገራ መጥረጊያዎችን አለመጠቀም
*በፊንጢጣ አካባቢ የህክምና የቁስለት ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ሌሎች በሽታዎች ስላሉ ሃኪም ዘንድ በመቅረብ ማረጋገጥ እና
*በዕየለቱ በቂ ፈሳሽ መጠጣት አስፈላጊ ነው
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦https://t.me/