የሆድ ድርቀት
Author: solomon
Date: 2024-11-22
የሆድ ድርቀት
የሆድ ድርቀት የአንጀት ጡንቻዎች የእንቅስቃሴ ድግግሞሽ በቁጥር ሲያንስ ወይም ዓይነ ምድራችንን ለማስወገድ መቸገር ሲሆን ይህ ሁኔታ ለጥቂት ሳምንት _ ወይም ከዚያ በላይ ቆይታ ሊኖረው ይችላል።በዚህ እንቅሰቃሴ መሃል ያለው የጊዜ ልዩነት ከሰው ሰው ይለያያል።አንዳንድ ሰዎች በቀን ሶስት ጊዜ እንቅሰቃሴ ሲኖራቸው ሌሎች ደግሞ በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ይኖራቸዋል።ያለምንም የአንጀት ጡንቻዎች እንቅስቃሴ ሶስት ቀን ከሆነ በጣም አረጅምና አደገኛ ሲሆን ከሶስት ቀን በኋላ _ ዓይነምድራችን ሰለሚደርቅ ለማስወጣት አሰቸጋሪ ይሆናል።የሆድ ድርቀትን ጠቅለል ባለ ሁኔታ ለመግለፅ ያከል የአንጀት ጡንቻዎች እንቅስቃሴ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከሶስት ጊዜ በታች ሲሆን ነው።በማንኛውም ሠው ላይ የሆድ ድርቀት በአጋጣሚዎች የሚከሰት ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ከባድ የሆድ ድርቀት ያጋጥማቸዋል፡፡ይህም የቀን ከቀን ስራቸውን ያስተጓጉላል።
የሆድ ድርቀት መነሻዎች
የሆድ ድርቀት በአብዛኛው ጊዜ የሚከሰተው ዓይነምድራችን በምግብ መፍጨት ስርዓት ውሰጥ ሲያልፍ በጣም በሚዘገይበት ጊዜ ይፈጠራል፡፡ይህም ዓይነምድራችን ጠንካራ እና ደረቅ እንዲሆን ያደርገዋል ስለሆነም የሚከተሉት የሆድ ድርቀት መነሻዎች ናቸው፡፡
*በቂ ውሐ አለመጠጣት
*በምግብ ገበታዎ ውስጥ በቂ ያልሆነ ፋይበር አለመኖር
*መደበኛ የምግብ ሠዓት መስተጓጎል
*በቂ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ
*ከፍተኛ መጠን ያለው የወተት ተዋዕፆ መመገብ
*ጭንቀት
*ሃይፖታይሮዲዝም
*ከመጠን በላይ የዓይነምድር ማለስለሻ መጠቀም
*የአንጅት ወይም ፊንጢጣ መዘጋት
*በአንጀትና ፊንጥጣ አካባቢ ያሉ ነርቮች ለችግር መጋለጥ
*ዓይነምድር ለማስወጣት መቸገር
*የዳሌ ጡንቻዎች በተቀናጀ ሁኔታ መጨማደድና መዝናናት አለመቻል ናቸው።
የሆድ ድርቀት እንዴት ሊታከም ይችላል?
አብዛኛዎቹ ሠዎች ከባድ የሆነ ምርመራ አያስፈልጋቸውም።በጣም ጥቂት የሚባሉት ደግሞ ከባድ Puango ችግር ስለሚያጋጥማቸው
ህክምና ያስፈልጋቸዋል።ከሁለት ሳምንት በላይ የቆየ የሆድ ድርቀት ካጋጠመዎት የህክምና ባለሙያ ማማከር ያስፈልገዎታርት የሆድ ድርቀት በአንጅት ካንሰር ከተከሰተ ቅድሚያ ማወቅና መታከም በጣም አሰፈላጊ ነው ይሁንና የሆድ ድርቀት መነሻ ምክንያትን ለማወቅ የሚደረጉ ምርመራዎች የሚከተሉትኝ ያካትታል፦
*የደም ምርመራ፦የሆርሞኖች አለመመጣጠን የሚፈጠር ከሆነ
*የባርየም ጥናት፦የአንጀት መዘጋት የሚጠረጠር ከሆነ
*ኮሎኖስኮፒ፦የአንጀት መዘጋትን ለማወቅ ይጠቅማል
የሆድ ድርቀት ካጋጠመዎት የሚከተሉትን ይሞክሩ
*ከሁለት እስከ አራት ተጨማሪ ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ
*ሞቅ ያለ ፈሳሽ ይጠቀሙ በተለይ ጥዋት ላይ
*የምግብ ገበታዎ ላይ ፍራፍሬ እና አትከልት ይጠቀሙ
*የጥራጥሬ ውጤቶችን ይመገቡ
*አሰፈላጊ _ ከሆነ በጣም በጥቂቱ የዓይነምድር ማለስለሻዎች ይጠቀሙ።ለምሳሌ ሚልክያስ ኦፍ ማግኒዚያ
*ሃኪምዎን ሳያማክሩ የዓይነምድር ማለስለሽያ ወይም ላካሳቲቭ ከሁለት ሳምንት በላይ አይጠቀሙ ምክንያቱም ከመጠን በላይ ላክሳቲቭ መጠቀም ምልክቶችን ያባብሳቸዋል
የሆድ ድርቀትን እንዴት መከላከል ይቻላል?
የሆድ ድርቀትን ለመከላከል የተለያዩ መንገዶች አሉ።እነሱም፦ የተመጣጠነ ምግብ በተለይ ፋይበር በብዛት ያላቸውን ይመገቡ
የፋይበር ይዘት ከፍተኛ ፍራፍሬዎች፣አትክልቶች፣ጥራጥሬና ያላቸው ምግቦች ዳቦዎችን ይመገቡ እንዲሁም ፋይበርና ውሃ አንጀታችንን ዓይነምድርን በቀላሉ እንዲያሳልፍ ያደርገዋል።
*ከአንድ ሊትር ተኩል እስከ ሁለት ሊትር ተኩል ውሃ እና ሌሎች ፈሳሾችን በቀን መጠጣት ጠቃሚ ነው።ካፌን የያዙ ፈሳሾች ለምሳሌ ቡና እና ለስላሳ መጠጦች የሰውነት ፈሳሽን የማድረቅ ባህሪ ስላላቸው አጠቃቀማችን መቀነስ አለብን።አንዳንድ ሰዎች ወተት ሲጠጡ ስለሚያባብስባቸው ቢቀንሱ ይመረጣል።
*በየግዜው እሰፖርታዊ እንቅስቃሴ ያድርጉ ነገር ግን ከታች የተዘረዘሩት ምልክቶች በሰውነትዎ ውስጥ ከተከሰተ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ተመራጭ ነው፡፡ለምሳሌ፦
*በዓይነምድር ውስጥ ደም ካለ
*የክብደት መቀነስ ከተፈጠረ
*የአንጀት ጡንቻዎቸ ህመም ካለ
*የሆድ ድርቀት ችግርዎ ከሁለት ሳምንት በላይ ከሆነ
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
telegram፦https://t.me/