ብጉንጅ

ብጉንጅ ብጉር መሰል የቆዳ በሽታ ሲሆን የቆዳ ማበጥ ወይም መደደር ነው።አንድ እና ከዚያ በላይ የሆኑ የፀጉር መውጫ ቀዳዳዎች በባከቴሪያ ምክንያት ኢንፌክሽን በሚፈጠርበት ወቅት የቆዳ ስር በመቆጣት መግል በመያዝ እና በማበጥ ህመም እንዲከሰት የሚያደርግ የህመም ችግር ነው።እብጠቱ በፍጥነት በማደግና መግል በመሙላት የህመም ስሜቱ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

የህመም ምልከቶች
ብጉንጅ በየትኛውም የሰውነት ከፍል ሊወጣ ቢችልም በብዛት ግን የሚወጣው በፊት ቆዳ፣አንገት፣ብብት ስር፣መቀመጫና ታፋ ላይ ነው፡፡

*ህመም ያለውና ቀላ ያለ እብጠት መታየት
*በእብጠቱ ዙርያ የቀላና ያበጠ ቆዳ መታየት
*እብጠቱ መግል እየሞላው ሲመጣ መጠኑ እየጨመረ መምጣት
*ነጭ ወይም ቢጫ ነገር በእብጠቱ ጫፍ ላይ መታየት ከዚያም መፈንዳት እና መግሉ መውጣት ይጀምራል

ምንም እንኳ ማንኛውም ጤነኛ የሆነ ሠው ብጉንጅ ሊይዘው ቢችልም የሚከተሉት ነገሮች ግን ይበልጥ ተጋላጭ ሊያደርጉት ይችላሉ፦

1.ስታፍሎኮካል ባክቴሪያ ኢንፌከሽን ከያዘው ሥውር ጋር የቅርብ ግንኙነት ካለ
2.የስኳር ህመም ተጠቂ መሆን
3.የሰውነት የበሽታ መቀነስ ናቸው።

እንዴት እንከላከለው?

* የህይወት ዘይቤ ለውጥና የቤት ውስጥ ህክምና አድርግ
* የሞቀ ውሃን በትናንሽ ብጉንጆች እላዩ ላይ መያዝ
*በራሱ እንዲፈርጥ መተው
*ንኪኪን መከላከል፦ብጉንጅን ከነኩ በኋላ እጅዎን በደንብ መታጠብ እንዲሁም ብጉንጅ የኒኩሊየር ልብስ ካለዎትና በተደጋጋሚ የሚያሰቸግረዎት ከሆነ ልብሱን በካውያ መተኮስ
* ብጉንጅን እራስዎ አለማፍረጥ፦ይህን ማድረግ ብጉንጅ ሌላ ቦታ ያደርጋል

ይሁንና በሰውነት ላይ ከሚፈጠረው እብጠትና የመቁሰል ምልከት በዘለለ የከፋ ጕዳት እንደማያደርስ ይነገራል።ሆኖም ግን አልፎ አልፎ የሰውነት ትኩሳት፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ አይነት ምልከቶች ሊያሰከትል ይችላል።ያም _ ሆነ ይህ ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚያሰችል ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ በቤት ውስጥ ማዘጋጀት ስለሚቻል የሚከተሉትን መርሆች ይከተሉ፦

*አ.አር.ኤስ ወይም በተለምዶ የእንግሊዝ ጨው
*በሙቅ ወይም ለብ ባለ ውሐ ውስጥ ኢ.አር.ኤስ በመባል የሚታወቀውን በመጨመር በሚገባ ከደባለቅን በኋላ ሰውነታችንን በውሃ መታጠብ በቀላሉ ሊፈውሰን ይችላል

*ዳቦ
ዳቦ ብጉንጅን ለማጥፋት ፍቱን ነው የተባለለት ሲሆን ለብ ያለ ውሐ ወይም ወተት ካዘጋጀን በኋላ ዳቦውን እዛው ውስጥ ጨምረን በማዋህድ ብጉንጁ ባለበት ቦታ ላይ በቀን ሁለት ጊዜ በመቀባት ራሳችንን ማከም እንችላለን

*ነጭ ሽንኩርት

ለብዙ ህመሞች ፈዋሽ መሆኑ የሚነገርለት ነጭ ሽንኩርት ብጉንጅን ለማከምም ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ተረጋግጧል።አዘገጃጀቱም በመጀመርያ ነጭ ሽንኩርቱን በእሳት ላይ ሞቅ እንዲል ማድረግ ይጠበቅብናል በመቀጠልም ብጉንጁ ባለበት ቦታ ላይ በማድረግ ለአስር ደቂቃ ያክል ማቆየት ፣ይህን

በተደጋጋሚ በተከታታይ ቀናት በማድረግ ለውጥ ማግኝት ይቻላል

*እንቁላል

እንቁላል ከቀቀልን በኋላ ነጩን ከፍል በማንሳት በደንብ እንዲረጥብ በማድረግ ብጉንጁ ባለበት ቦታ ላይ ማድረግ፣ከዚያም በንፁህ ጨርቅ : አስረን ማቆየት ሌላኛው ብጉንጅን የማከም ዘዴ ነው

*ወተት

ወተት ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ብጉንጅን ለማከም በጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል።በአንድ ብርጭቆ ወተት ውስጥ ሶስት የሻይ ማንኪያ ጨውና የስንዴ ዱቄት ከጨመርን በኋላ አንድ ላይ በማደባለቅ ከዚያም ለተወሰነ ቀናት በየቀኑ ደጋግመን በቦታው መቅባት ብጉንጅን ለማከም ፍቱን መድሃኒት ነው።

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202