የጉሮሮ ካንሰር
Author: solomon
Date: 2024-10-17
የጉሮሮ ካንሰር
ሶስት አይነት የጎሮሮ ካንሰር ያለ ሲሆን፥ በርካቶች ግን ይህንን ለመረዳት ሲቸገሩ ይስተዋላል።ለዚህ ግራመጋባት አንዱ ነው የሚባለው ደግሞ የጉሮሮ ካንሰር የሚለው በህከምና ቋንቋ ዘርፍ ጥቅም _ ላይ ስለማይውል ሰዎች በቀለላሉ ለመረዳት ይቸገራሉ።በእንግሊዝ ሀገር የሚገኘው የጥናት ማእከል እንዳስታወቀው፥ በህክምናው ጉሮሮ ዘርፍ ለመግለጽ “ፋርይንከስ” የሚል ቃል የሚጠቀሙ ሲሆን፥ ይህንንም “ናዞፋርይንከስ”፣ “ኦሮፋርይንከስ” እና “ሀይፖፋርይንከስ” በማለት ለሶስት ይከፍሉታል።ሶስቱም የጉሮሮ አካላት በካንሰር የመጠቃት እድል እንዳላቸው የተነገረ ሲሆን፥ እያንዳንዱ የጉሮሮ አካል ላይ ለሚከሰት ካንሰር የህመም ምልክቶች እና የሚሰጠው ህክምና የተለያየ ነው፡፡ ከዚህ በታች የሶስቱም የጉሮሮ ካንሰር አይነቶች ምልከቶች፣ መንስዔ እና ህከምና እንመለከታለን፡፡
1 ናዞፋርይጀል ካንሰር
“ናዞፋርይንከስ” በመባል የሚጠራው የላይኛው የጎሮሮ ከፍል ሲሆን፡ የአፍጫችንን የጀርባ ከፍል ከላንቃችን ጋር የሚያገናኝ የጉሮሮ ከፍል ነው።የዚህ ካንሰር ምልክቶችም፦
• በአንገት አካባቢ የእብጠት ምልክት መታየት እና እብጠቱ ለሶስት ሳምንት እና ከዚያ በላይ የቆየ ከሆነ
• የመስማት ችግር፥ በተለይም በአንድ ጎን ጆሮ ላይ
• በጆሮ ውስጥ የሚያቃጭል (የሚጮህ) ድምጽ መስማት
• ከጆሮ ውስጥ ፈሳሽ የሚጣ ከሆነ
የአፍንጫ መዘጋት፥ በተለይም በአንድ በኩል አፍንጫ የሚደፈን ከሆነ
• ከአፍንጫ ደም የሚወጣ ከሆነ
• ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት
• በእይታ ላይ ብዥታ የመፈጠር
• ምግብ በመመገበብ ጊዜ ለመዋጥ መቸገር
• የድምፅ መለወጥ፥ በተለይም ያልተለመደ የመጎርነን ምልከት
“ናዞፋርይጀል” ካንሰር መንስዔ እስካሁን በውል ባይታወቅም : ጨው የበዛበት ስጋ ነክ ምግቦችን መመገብ እና ለአቧራ ተጋላጭ በሆነ አካባቢ የሚሰሩ ሰዎች ለዚህ የጉሮሮ ካንሰር ተጋላጭነታቸው የሰፋ ነው፡፡ ናዞፋርይጀል ካንሰር ተጠቂዎች በብዛት በራዲዮቴራፒ እና ኬሞቴራፒ ህከምና ይደረጋል።
2 ኦሮፋርይንጀል ካንሰር
“ኦሮፋርይንከስ” በጉሮሮ መካከለኛው ስፍራ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህም የላንቃ ለስላሳ ስፍራ፣የምላስ መነሻ ስፍራ እና የጉሮሮ ኋለኛዉ ክፍልን ያካተተ ነው። የዚህ ካንሰር ዋነኛ ምልከቶች የሚባሉት፥
• ምግብ በቀላሉ ለመዋጥ መቸገር
• በአንገት አካባቢ እብጠት መታየት
• በጉሮሮ እና ምላስ ላይ የህመም ስሜት መሰማት
• የጆሮ ህመም
• አፍ እና መንጋጋን በቀላሉ የማንቀሳሰቅ ችግር
• የድምፅ መለወጥ
• መጥፎ የአፍ ጠረን
ከመጠን በላይ መጠጥ አብዝቶ መጠጣት እና ሲጋራማጨስ “ኦሮፋርይንጀል" ካንሰር የመጋለጥ እድልን ያሰፋል።
ኦሮፋርይንጀል ካንሰር ህከምና በቀዶ ጥገና፣ በራዲዮቴራፒ እና ኬሞቴራፒ ይሰጣል።
3 ሀይፖፋርይንጀል ካንሰር
“ሀይፖፋርይንከስ” በመባል የሚጠራው የጉሮሮ ከፍል የላይኛው እና መካከለኛውን የጉሮሮ ከፍልን ከምግብ ቱበ ጋር እና የአየር ቱቦን ድምፅ ሳጥን አማካኝነት የሚያገናኝ የጉሮሮ ከፍል ሲሆን የዚህ የጉሮሮ ከፍል ካንሰር ምልከቶች፡
• ምግብ የመዋጥ ችግር
• ከፍተኛ የሆነ የጉሮሮ ህመም
• ከጉሮሮ አካባቢ ወደ ጆሮ የሚሄድ ህመም
• የድምፅ መጎርነን
እንደ ሌሎች የጉሮሮ ካንሰር ሁሉ “ሀይፖፋርይንጀል" ካንሰር ከመጠን ያለፈ መጠጥ በመጠጣት ሲጋራ ማጨስ እና ባልተመጣጠነ የአመጋገብ ስርዓት ሊከሰት ይችላል፡፡ ህከምናውም በቀዶ ጥገና፣ በራዲዮቴራፒ እና ኬሞቴራፒ የሚሰጥ ነው፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትን የህመም ስሜቶች እና መልከቶች በብዛት የሚያስተዉሉ ከሆነ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የህከምና ባለሙያዎችን ማማከር መልካም ነው፡፡
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736