⚫️ ማድያት

ማድያት ማለት
በተለያዩ ምክንያቶች በፊታችን ላይ ሊከሰት
ይችላል።ከምክንያቶች መካከል ለብርቱ የፀሐይ ብርሀን
መጋለጥ፣የሆርሞን መለዋወጥ፣የፊት ቅባት፣የወሊድ መከላከያ፣የተለያዩ
የፊት መዋቢያዎችን(ኮስሞቲክስ) እና
ከፍተኛ ሙቀት ይገኙበታል በመሆኑም ተፈጥሯዊ መላዎችን
ማወቅና መጠቀም ተገቢ ይሆናል።

ከዚህ በመቀጠል በቤትዎ
ዉስጥ በተፈጥሮ ከሚገኙ ነገሮች እንዴት ማድያትን ማጥፋት
እንደሚችሉ እንመለከታለን፦
1.የሎሚ ጭማቂ
ሎሚ ማድያትን ለማጥፋት ምርጡ መንገድ ነዉ።የሎሚን
ጭማቂ ፊትን ቀብቶ ለሁለት ደቂቃ ማሸት እና ሃያ ደቂቃ
ከቆዩ በኋላ መታጠብ።የሎሚ ጭማቂ እና ማርን በእኩል መጠን
ቀላቅሎ ፊትን መቅባት ከዛም በሞቀ ፎጣ ለ15 ደቂቃ ሸፍኖ
ማቆየትና መታጠብ ሌላኛው አማራጭ ሲሆን የሎሚ ጭማቂን
ከእርድ ጋር በመደባለቅ መቅባት ጥሩ ውጤት ይሰጣል።
2.አጃ
የተፈጨውን የአጃንስ ዱቄት ከማር ጋር መለወስ ከዚያም
በማድያቱ ላይ መቅባት እና ለግማሽ ሠዓት አቆይቶ በሙቅ ውሃ
መታጠብ የሞቱ ሴሎችን ከቆዳችን ላይ ያነሱልናል
3.የፖም ኮምጣጤ
አንድ ማንኪያ የፖም ኮምጣጤ ከአንድ ማንኪያ ውሃ ጋር
በመደባለቅ በየቀኑ መቀባት
4.እርድ
አንድ የሻሂ ማንኪያ የተፈጨ እርድ ከ2-3 የሻይ ማንኪያ ወተት
ጋር በመደባለቅ ማዋህድ እና አንድ የሻይ ማንኪያ የባቄላ ወይም
የሽንብራ ዱቄት ጋር ደባልቆ መቅባት እና ለ20 ደቂቃ አቆይቶ
መታጠብ ሲሆን ማድያቱ እስኪጠፋ ይህን ውህድ መቅባቱ
ጠቃሚ ነው።
5.የሽንኩርት ጭማቂ
ከሁለት እስከ ሶስት የሚሆኑ ሽንኩርት በመፍጨት ወይም
በመቀጥቀጥ የሸንኩርቱን ውሐ በጥጥ መቀባት እና ለ20 ደቂቃ
አቆይቶ ለብ ባለውሃ በየቀኑ መታጠብ ይመከራል።
6.እሬት
አንድ የእሬት ቅጠል በመውሰድ እንደ ጀል ያለውን ፈሳሽ ተቀብቶ
ለሁለት ደቂቃ ማሸት ከአስራ አምስት እስከ ሃያ ደቂቃ አቆይቶ
ለብ ባለውሃ መታጠብ ይመከራል።
7.ፓፓያ
ግማሽ የሻሂ ስኒ የበሰለ ፓፓያ መፍጨት፡ ከሁለት ማንኪያ ማር ጋር ደባልቆ መቀባት እና ለሃያ ደቂቃ አቆይቶ ለብ ባለ ውሐ መታጠብ።

ከጥበብን በማንኪያ መፅሀፍ በሀኪም ሰለሞን አዳሙ 2013 ዓ.ም የተወሰደ፡

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736