መተት ምንድን ነው ?
Author: solomon
Date: 2024-07-02
መተት ምንድን ነው ?
ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
-መተት በተለያየ ቦታ የተለያየ ስያሜና አጠራር ሲኖረው
#ድግምት
#ውለሽ
#የሰው እጅ
#ደንቀራ
#ስልበት በመባል ይታወቃል
👉 መተት ፈሪሐ እግዚአብሔር በሌላቸው ክፉ ሰሪዎችና አሰሪዎች የሚከናወን የክፋት (የመናፍስት) ስራ ነው ።
ብዙውን ጊዜ ጥቁር አስማት የሚባሉት
#መቅትል
#መስተሐምም
#መስተአብድ
#መስተባርር
#ህልመ ደብድብ
#መድፍነ ፀር
#ማዕፀወ ምስያጥ (የገብያ መዝጊያ)
#ሀብተ ገልብጥ በመባል ይታወቃል
እንዳለመታደል ሁኖ አንዳንድ ሰዎች ሰርተው ከማደግና ይልቅ ከፈጣሪ ሕግ በመውጣት በሰው ሀብት፣ ንብረት እድልና ግንባር በመቅናት የተለያየ መተት ተጠቅመው የሰውን ልጅ ህይወት ሲያመሰቃቅሉ ይኖራሉ።
#መተት በዋነኛነት በ3 ይከፈላል
1.በስም በማስደገምና በማስመተት
2. በሚበላ በሚጠጣ በማቅመስ
3. በመርጨት (ደንቀራ በመጣል)
#የመተት ተፅኖውና ክፋቱ
-ሀገር አስለቅቆ መስደድ
-ማሳበድ ፣ዘዋሪና ከርታታ ማድረግ
-እራስን አጥፋ አጥፋ ማለት
-ሽባ ማድረግ
-እስርስር አድርጎ ቤት ማዋል
-የአልጋ ቁራኛ ማድረግ
-ሌሊት እየመጣ በህልም ማሰቃየት
-መንፈሱ በህልመ ሌሊት ተመስሎ በመንደፍ ማርከስ
-ጥቁር ሰው ፣በሬ ፣ውሻ ፣እባብ እየመሰለ ሌሊት ማሰቃየት
-ሆድን ቀትቶ መንፋት
-ከሆድ ላይ መገለባበጥ (መጮህ)
-ሰውነትን መቆርጠም (መሰቅሰቅ)
-ማፍዘዝ ማደንገዝ ማንቀጥቀጥ
-ጭንቅላትን (እወቀትን)ባዶ ማድረግ
-ንቃተ ህሊናን እስከ እድል መስለብ
-ንቡዘ ልብ ማድረግ (ማስረሳት)
+ፍርሃት ጭንቀት ድብርት ብስጭት
-ስንፈተ ወሲብ ማምጣት
-ሰውነትን መሸምቀቅ
-እራብ እራብ ማለት
-እህል መከልከል
-ከመጠን ያለፈ ውፍረት
-በጣም መክሳት
-እንቅልፍ መከልከል
-እንቅፍ እንቅልፍ ማለት
-ሱሰኛ መሆን የጫት የመጠጥ የሽሻ
-ገንዘብ መበተን
-ስራ ጀምሮ አለመሳካት
-የውጭ እድል መዘጋጋት
-እንከን ሳይኖረን ከፍቅርኛ ጋር መለያየት
-ባልና ሚስት ማለያዩት
-መካንነት
-አግኝቶ ማጣት
-የገብያ መዘጋጋት.
👉 ታዲያ ይህ ችግር በሀገራችን ብሎም በአለማች የስንቱን ህይወት እንዳበላሸውና የስንቱን ቤት እንደፈታው ስንቶቻችን ነው የምናውቀው ?
ይህ ችግር በቤታችን ካለና ከተከሰተ መፍትሔውን በመጠቀም ችግሩን ማስወገድ አለበለዚያ ግን የችግሩ ሰለባ ሁነን እንቀራለን
እንደየ እምነታችን በርትተን መፀለይ ንስሐ መግባት በፆም በፀሎት በስግደት ክፉ የመናፍስት መተትንና ማስወገድ የተለያዩ መአቅቦችን መያዝና ፀልየን መውጣት ወሳኝ
ነው
መድሀኒቱም
#የአንባጮ ስሩን ቅጠሉን (ተቀፅላውን )
#የሎሚ ተቀፅላ
#የአገም ስሩንና(ተቀፅላውን)
#የግራዋ ቅጠል (ተቀፅላ)
#የአቱች ስሩን ቅጠሉነ
#የታሪገም ስሩን ቅጠሉን
#የጤናዳም ፍሬናቅጠል
#፯ሎሚ_ፍሬ
#የአበዘጣ ቅጠል
#አዘገጃጀት
የተዘረዘሩትን እፅዋቶች በንፅህና አዘጋጅቶ በእለት ውሀ ዘፍዝፎ ጥዋት ጥዋት መፍትሔ ሥራዩን 7 7 ጊዜ እየጸለዩ መጠመቅና ቤትን መርጨት ነው።
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736