መጠኑ የበዛ ጋዝ (ፈስ) አስቸግሮኛል ምክንያቱ ምን ይሆን? 🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
Author: solomon
Date: 2024-06-18
መጠኑ የበዛ ጋዝ (ፈስ) አስቸግሮኛል ምክንያቱ ምን ይሆን?
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
፨ በአንጀታችን ውስጥ ጋዝ እንዲከማች የሚያደርጉ የተለያዩ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በትንፈሳ የምንምገው አየር፣ የምንመገበው ምግብ እንዲሁም በአንጀታችን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ባክቴሪያዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሊሆን ይችላል።
👉 ለምሳሌ ምግብ አላምጠን ስንውጥ 10 ሚሊ ሊትር የሚሆን አየር አብረን እንውጣለን፣ ማስቲካ ስናኝክ በቋሚነት አየር እያስገባን ነው፤ በጥናቶች በታወቀው መሰረት በ24 ሰዓት ውስጥ 30 ሊትር የሚሆን አየር በአንጀታችን ያልፋል፡፡ ይህ አየር አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን ህይወት እንዲቀጥል የሚረዱ ነገሮችን ለሰውነት በማቀበል የድርሻውን የሚወጣ ነው፤ ከዚህ አየር ውስጥ ጠቃሚ የሆኑት ወደ ደም ይቀላቀላሉ፡፡ሌሎቹ በፈስ መልክ ይወገዳሉ፡፡
👉 ነገር ግን ፈስ ከለመዱት ውጪ ሲሆንና መጠኑ ሲበዛ ማስተካከል ያለብዎ ነገሮች እንዳሉ ጠቋሚ ነውና ሁኔታውን ለማስተካከል ማድርግ ስለሚገባዎት ነገሮች እንንገሮት፡፡
1. ምግብን ቀስ እያሉና እያሰቡ ይመገቡ
📌 በሆዳችን ውስጥ ከሚገኘው ጋዝ አብዛኛውን የሚሆነው በመዋጥ የሚገባ ነው፤ የምንውጠውን ጋዝ(አየር) ሙሉ ለሙሉ ማስቀረት ባንችልም መቀነስ ግን ይቻላል፡፡
📌 በፍጥነት ስንመገብ በዝግታ ስንመገብ ከምናስገባው አየር የበለጠ አየር ወደ ሆዳችን እናስገባለን፡፡ በመሆኑም በዝግታ መመገብዎ ከመጠን ያለፈ ፈስን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
እናመሰግናለን
መልካም ጤንነት
🌴🌴ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌴🌴🌴
»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com
telegram፦https://t.me/