የአሰርኩሽ
Author: solomon
Date: 2024-06-17
የአሰርኩሽ
ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ
#የአሰርኩሽ ስር ከሚበላሽ እቃ፣ ከሚጠፋው እቃ ፣ከቡኃ እቃ፣ከብር ማስቀማጫ ሳጥን።ወዘተ...በቀይ ሀር አስረው ያስቀምጡ አልያም ይሰሩበት።አያስነካም የተበላሸ ቅን ይስተካከላል።
🔸ለዕብድ ውሻ ንክሻ ማዳኛ፦
#ያበደ ውሻ የነከሰህ እንደሆነ የአሰርኩሽ ተበተብኩሽ ስር በተባለው መሰረት በመቆፈር በ ትንሿ ጣት ለክተህ አድቅቀህ ፈጭተህ በማንኛውም ሰዓት በግማሽ ሌትር የላም ወተት ጋር በማቀላቀል ይጠጡ።
🔸ለእባብ ንክሻ፦
#ለማንኛውም እባብ ንክሻ መከላከያ ገና ዕጿ ስትቆርጥ ዕጽ አንግስን ጸልየህ ከጨረስክ በኃላ ዕቀብኒ እም ሕምዘ ከይሲ (ለእከሌ) በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አወገዝኩኪ ብለህ ቁረጥ።በጣትህ ዓጽቅ ከትበህ በአንገትህ እሰር እንዘ ትሐውር ኃበ ሐቅል!
🔸ለድከመተ ወሲብ(ለመንስኤ እስኪት)፦
#የብልቱ ሴሎች በመድኃኒት፣ በስኳር፣ በግፊት፣በመዳከም ብልት አለመነሳት ችግር ለፈጠረበት ሰው የሚሆን።
~የአሰርኩሽ ሥር፤የወንዴ ቃጫ ሥር፣ ሁለቱም ከሰባት ከሰባት ቦታ በወይራ ዛብያ ቆፍረህ ሥሩን በንጽህና ቀጥቅጠህ ሁለቱም አንድ ላይ ቀላቅለህ በ አንድ ማሰሮ ውስጥ ከ ግማሽ ኪሎ ጥሬ ምሥር ጋር በደንብ ቀቅለህ መረቁን ጧት ጧት ለ 3 ቀን ያክል መጠጣት ነው።
የእጽዋቱ መጠን ከሁለቱም 6 የሾርባ ማንኪያ ይጠቀሙ።
🔸ለግርማ ሞገስ፤ለሰው ፍቅር፦
#የአሰርኩሽ ሥር ከዚህ በፊት በላኩላችሁ የደላሹት ገቢር አቆራረጥ መሰረት በመቁረጥ ለሚሹት ሁሉ መፍትሔ ትሆን ዘንድ በፈጣሪ ስም አወግዘህ ነቀህ በጣትህ ዓጽቅ ለክተህ በዓረብ ቆዳ በመከተብ ከኪስ ወይም ከአንገትህ ሥር አንጠልጥል።
ይህንኑ ገቢር ለንግድም ይሆናል። ጠጅ ለሚነግድ ሰው ከመሸታው እቃ ስር በሰምዕ ጠቅልለህ ቅበር።አልሸጥ ብሎ የገረገረው እንዲሸጥ ይሆናል።
#የደላሹት ገቢር ከዚህ ቀደም ስለላኩላችሁ ወደታች ወረድ ብለው ለማየት ሞክሩ።
🔸ላም እና ጥጃዋ አልዋደድ ቢሉ፦
#ላሚቱ ጥጃዋን ብትጠላ የአሰርኩሽ ሥር በአምሳያ ላም ቅቤ ለውሰህ ጥጃዋን እና ላሟን ቀባ እጅጉን ይዋደዳሉ።
🔸የጨብጥ መፍትሔ፦
#የአሠርኩሽ ሥር፤የመቅመቆ ሥር፤የዘረጭ ፍሬ እነዚህ በትንሿ የሻይ ማንኪያ አንድ አንድ ከሶስቱም በመለካት በንፁህ ማር በመለወስ ጧት በባዶ ሆድ ለሶስት ቀን መዋጥ ነው።
መሻርያው፦የገብስ ጠላ ጠጣ ወይም የደሮ ወጥ ብላ ትድናለህ።
🔸ለደም ፍታት(የወር አበባ ለሚበዛባቸው)
#የአሰርኩሽ ሥር ለ 3 ቀናት ያክል በመቀነት አድርጋ ወገቧን አስራ ትሰንብት ድጋሚ አይመለስባትም።
ትድኅን!
🔸ለከብት እርባታ፦
#የአሠርኩሽ ሥር ምሰህ አምጥተህ በትክል ድንጋይ ቀጥቅጠህ በዕለት ውኃ በጥብጠህ የከብቶቹ በረት በማለዳ ለ 3 ቀን እርጭ ከብቶቹንም በአሞሌ ጨው ቀላቅለህ በትንሹ አስልሳቸው።
🔸ለማንኛውም አሰፈሪ ቁስል፦
#የአሰርኩሽ ሥር ቆፍረህ አድርቀህ ደቁሰህ ከቁስሉ ላይ እስኪድን ድረስ መነስነስ ነው።
ፍቱን ነው።
🔸ለዓይነጥላ ለፍርሃት፤በፈተና ጊዜ ለሚጃጁ፦
#የአሠርኩሽ ሥር፤የሐረግ ሬሳ ሥር፤የቀበርቾ ሥር ለየብቻ አድርቀው እኩል በማቀላቀል ማታ ማታ ሊተኙ ሲሉ አንድ አንድ የሾርባ ማንኪያ በመለካት ተሸፋፍነው ለ 7 ቀን ይታጠኑ።
እናመስግናለን
መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736