ስንፈተ ወሲብ እና መፍትሔው
          ትዳር በታኙ ስንፈተ ወሲብ!!!
          🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀

፨ስንፈተ ወሲብ የሚለውን ቃል፣ ጠበብ ባለው ዐውዱ ሲታይ፣ከዚህም የወንድም ሆነ የሴት ብልት አለመነቃቃትንና ለግንኙነት ዝግጁ ካለመሆን ጋር የቀጥታ ቁርኝት ያለው ነው፡፡ ነገር ግን ስንፈተ ወሲብ ብልት ለግንኙነት ዝግጁ አለመሆን ማለት ብቻ አይደለም፡፡  ሰፋ ያለ ትርጓሜ ያለው ነው፡፡ የስንፈተ ወሲብ ችግር በሁለት መንገድ የሚከሰት ነው፡፡

⚡️የመጀመሪያው ተፈጥሯዊ በሆነ የአፈጣጠር ችግር ማለትም በክሮሞዞን፣ የሴትነትና የወንድነት መገለጫ በሆኑት የኦቫሪና የቴስትሮን አፈጣጠር ችግር ምክንያት የሚፈጠር ሲሆን፣

⚡️ ሁለተኛው ከውልደት በኋላ በዕድገት ሂደት በአካላዊ፣ በአዕምሯዊ፣ በስነ ልቦናዊና በአካባቢያዊ ምክንያቶች የሚፈጠር የስንፈተ ወሲብ ችግር ነው፡፡ በዚህ ወቅት የሚፈጠረው ችግር ለግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅሞ ዝግጁ አለመሆንን፣ ጭራሹኑ ስሜት ማጣትን፣ ፍላጎት አለመኖርን፣ የመጨረሻው እርካታ ላይ አለመድረስን፣ የሌላኘውን ስሜት ሳይጠብቁ ፈጥኖ መርካትን፣ ለግንኙነት ዝግጁ ያለመሆንን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

⚡️ችግሩ ያለበት ሰው ከሚያሳያቸው ምልክቶች ዋና ዋና የሚባሉትን እንሆ!

ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የስንፈተ ወሲብ ችግር ሲከሰትባቸው፣ በጋራ ወይም በተናጠል ከሚያሳዩዋቸው ምልክቶች ዋና ዋና ተብለው የሚታወቁት ቀጥሎ የምገልፃቸው ናቸው፡፡

– የወሲብ ፍላጎት ማጣት (ለሁለቱም)

– የወሲብ መፈፀሚያ አካላት ለወሲብ ዝግጁ አለመሆን (በወንዶች)

– ለግንኙነት ዝግጁ የሚያደርግ ፍሳሽ በበቂ መጠን አለመመንጨት፣ የሚደረገውን የወሲብ ግንኙነት ደረቅና ህመም የበዛበት ያደርገዋል (ለሴቶች)

– የመጨረሻው የእርካታ ደረጃ ላይ አለመድረስ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ የስንፈተ ወሲብ ምልክቶች ናቸው ተብሎ ይወሰዳል፡፡

❌በዘመናዊ ያለ ሐኪም ትእዛዝ የሚወሰድ ቪያግራ ጉዳት

❌ቪያግራ ማንኛውም ሰው የሚወሰደው መድሃኒት አይደለም፡፡

መድሃኒቱ የስኳር፣ የደም ግፊት፣ የልብና የኩላሊት በሽታዎችን ያባብሳል፡፡ እንደዚሁም የደም ስሮችን በማጥበብ ስትሮክንና ደም ማነስን ያመጣለ፡፡ እነዚህ የጤና ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች በምንም ምክንያት ቪያግራን መውሰድ የለባቸውም፡፡

❌ ስለሆነም በምንም መንገድ ቢሆን ቪያግራም ያለ ሐኪም ትዕዛዝ መወሰድ የለበትም፡፡ መድሃኒቱ በሐኪም ትዕዛዝ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ ከተወሰደ ሱስ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

❌ሱስ ከሆነ መድሃኒቱ ካልተወሰደ በስተቀር ወሲባዊ ግንኙነት መፈፀም የማይቻልበት ደረጃ ላይ ያደርሳል፡፡ ሌሎችም መድሃኒቶች ተመሳሳይ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት ስላላቸው በተቻለ አቅም አግባብ ያለው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

»የስንፈተ ወሲብ ችግር ሊታከምና ሊድን የሚችል የጤና ችግር መሆኑን ሁሉም ሰው ቢገነዘብ ጠቃሚ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡

»በተጨማሪም ላልፈው የማልፈልገው ነገር ቢኖር ከላይ የጠቀስኳቸው የስንፈተ ወሲብ ምልክቶች በዘመናዊ ሕክምና ዘንዳ የታመነባቸው ችግሮች ሲሆን!!!

እናመስግናለን
          መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736