ቀይ ሽንኩርት ለጸጉር እድገት ያለውን ጠቀሜታ ያውቃሉ?

🍀ሀኪም ሰለሞን አዳምፈወፈሙ🍀

፨ብዙዎቻችን ቀይ ሽንኩርት ምግብ ለማዘጋጀት ከሚኖረው ፋይዳ ባለፈ ለጸጉር እድገት የሚረዱ ንጥረ ነገሮች መያዙን አንረዳም።

• የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ግን ቀይ ሽንኩርት የጸጉር መበጣጠስን ለመከላከልና የአዲስ ጸጉር እድገትን ለማፋጠን የሚረዳ መሆኑን አረጋግጠዋል።

• ቀይ ሽንኩርትን በምግብ መልክ አልያም በጭንቅላታችን ላይ ዘወትር መጠቀም እንደ ፎረፎር እና ሌሎች የጭንቅላትና ከጸጉር ጋር የተያያዙ በሽታዎችን ለመከላከል አይነተኛ ሚና ይጫወታል።

• ቀይ ሽንኩርት በዘር ወይም ከእንክብካቤ ጉድለት የሚከሰት የጸጉር መበጣጠስን ለመቀነስና ካለጊዜ የሚመጣ የጸጉር ቀለም ለውጥ ወይም ሽበትን ለመከላከል ይረዳል።

• ጥሬ ሽንኩርትን በስሱ ክብ አድርጎ በመክተፍ ጸጉር ላይ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ማድረግ ከዛ በኋላ በቀዝቃዛ ውሃ በሳሙና መታጠብ የፀጉር እድገትን ለማፋጠን ይረዳል።

• ቀይ ሽንኩርትን በጁስ መልክ በማዘጋጀት መጠቀምም የደም ዝውውርን በማቀላጠፍ የጸጉር እድገት እንዲፋጠን ያግዛል።

• በሰልፈር የበለጸገው ሽንኩርት የጸጉር ቅንጣቶች እንዲቀጥኑ በማድረግ በርካታ ጸጉር እንዲኖረንም ከፍተኛ ጥቅም አለው።

እናመስግናለን
          መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736