የአይን ሞራ ማለት ምን ማለት 🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀 እንዴት ሊከሰት ይችላል?
Author: admin
Date: 2024-05-30
የአይን ሞራ ማለት ምን ማለት
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
እንዴት ሊከሰት ይችላል?
» የእድሜ መጨመር እና
»ለፀሀይ ብርሃን አብዝቶ መጋለጥ
» በአይን ላይ በሚደርስ ጉዳት
» ስኳር ህመም
»እንዲሁም የተለያዪ የመድሀኒት አይነቶች ናቸው።
አንዳንዴም ህፃናት ከአይንሞራ ጋር ሊወለዱም ይችላሉ።
ምልክቶች ምንድን ናቸው?
»የአይን ብዥታ ፣ መደብዘዝ ወይም በዳመና የተጋረድ የሚመስል እይታ
»የፀሀይ ወይንም የመብራት ብርሀን በሚያዪ ጊዜ በጨረር መብዛት ምክንያት በጨለማ መኪና ለማሽከርከር መቸገር።
» በአንደኛው አይናችን ብዥታ የመኖር ሁኔታ
»የአይን ሞራሙሉ ለሙሉ እይታን እንዳይኖረን የሚያደርገው እጅግ ዝግመታዊ በሆነ ሁኔታ ሲሆን አንዳንዴም ምንም አይነት የእይታን ችግር ላይፈጥርም ይችላል።
እንዴት ማከም ይቻላል?
»የአይን ሞራ ህመምን በህክምና ባለሞያ የታዘዘ መነፅር በማድረግ የእይታ ችግሩን በመጠኑም መቀነስ የሚቻል ቢሆንም ሊያሻሻልም ይችላል።
» ከአይን ሞራ ጋር የሚወለዱ ህፃናትና በአይን ላይ በሚደርስ ጉዳት ምክንያት የሚከሰቱ የካታራክት ችግሮች የቆዳ ጥገና ህክምና ያስፈልጋቸዋል።
እንዴት መከላከል ይቻላል?
» ካታራክትን መከላከል የሚቻልበት መንገድ ባይኖርም ካታራክት እድገቱን ግን በዝግታ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል ይህም
» ሲጋራን ማጤስ በማቆም
» የፀሃይ መከላከያ መነፅር ወይንም ኮፍያ በማድረግ
» ጤናማ አመጋገብ መከተል
»እንዲሁም የስኳር ህመም ካለ መቆጣጠር ተገቢ ነው።
እናመስግናለን
መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736