ወደ ተፈጥሮ እንመለስ
ነጭ ሽንኩርት በታሪክ ውስጥ
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀

፨ነጭ ሽንኩርት በታሪክ ድርሳናት ውስጥ በስፋት የተፃፈለት እና የተተረከለት ቁጥር 1 እፀዋት የትኛው ነው ተብሎ ቢጠየቅ ብዙ ሺ ተመራማሪወች ነጭ ሽንኩርት ነው ይላሉ።

ታሪክ እንደሚያስረዳው በተለይም በሩቅ ምስራቅ ክፍለ አለም የሰውልጅ ከጓሮ አትክልትነትም ሆነ የእርሻ ማሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ካበቀላቸው የደን እፀዋቶች ውስጥ አንዱ ነጭ ሽንኩርት ነው።

ይህ ተክል ተክል የሰው ልጅ ከ አደን ወደ እርሻ ስልጣኔ ሲሸጋገር አሀዱ ብሎ ከተከላቸው እና ፍሬአቸውንም ከተጠቀመባቸው የእርሻ ዘር ውስጥ አንዱ ነው።

በጃፓኖች ዘንድ ነጭ ሽንኩርት እንደ አነቃቂ እፅ ስለሚታይ የጃፓን ብድሀእም እምነት እንደመድሀኒትነት እንጂ ለምግብነት እንዳያገለግል ይከለከል ነበር በዛን ወቅት በጃፓኖች ግንዛቤ ነጭ ሽንኩርትእንደ ጫት ከአነቃቂ እፆች ጎራ እንደተፈረጀ የተፃፈው የታሪክ ሰነድ ያሳያል ። ከጊዜ ወደ ጊዜግን ተቀባይነቱ እየጨመረ መቶ ከብድሀ ቄሶች በስተቀር ሌላው ህብረተሰብ በሁሉም መልኩ መጠቀም እንደሚችል ታመነበት የብድሀ ቄሶች እንዳይበሉት የተከለከሉበት ምክንያት የሩካቤ ስጋ ስሜትን በመቀስቀስ መንፈሳዊ ተግባራቸውን ያሰናክላል በሚል ነበር። ይህ የሚያሳየን ነጭ ሽንኩርት ለአእምሮ ብቃት ለፍቅር ለስሜት መቀስቀሻ እንደሚጠቅም ተገንዝበናል።

ቻይናያን በዚህ ጥልቅ እና ድንቅ ምልክት ላይ የኖሩበት አርማ ነጭ ሽንኩርት ነበር።የቻይናውያን ዩን ያንግ እና የነጭ ሽንኩርት መመሳሰልቻይናዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የተገነዘብት የነጭ ሽንኩርትን ጥቅም ሙቀት አመንጪነቱን እና አእምሮ ብሩህ የማድረግ ጥበብን ነበር በዛን ጊዜ ለድብርት እና ጭንቀት ስሜት ነጭ ሽንኩርት እንደ መድሀኒትነት ይጠቀሙ ረነበረ ሲሆን ቀስበቀስም ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ህመሞች  ለምሳሌ

»ለመተንፈሻ አካላት
»ለሆድ እቃ ህመም
»ለአይን
»ለቆዳ
» ለጥርስ እና ለልዩ ልዮ ኢንፌክሽኖች መጠቀም ጀመሩ ከቻይና ምድር እንደተገኘ በሰፊው የሚነገርለት ነጭ ሽንኩርት ለህክምና የተጠቀሙት የምግብ ፍላጎት እና አምሮትን  ለመጨመር ለምግብገመፈጨት ለሳል ለድካም ስሜት ለስርአተ ፀሎት የሚገብ ከሆነ ግን ይከለከል ነበር
ምክንያቱም የሩካቤ ፍላጎትን ስሜትን ስለሚቀሰቅስ ይህ ደግሞ ፀሎቱን እና ቅዳሴውን ስለሚያስተጓጉል ተብሎ ስለሚታመን ነበር

🍂ስለ ነጭ ሽንኩርት ተነግሮ አያልቅም ነገ ደግሞ ቀጣዩን ክፍል እንፅፍላችዋለን ይጠብቁን፣፣🍂

እናመስግናለን
          መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736