በብብት አከባቢ የሚፈጠር እብጠት 🌵 ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🌵
Author: Hakim Solomon Adamu
Date: 2024-05-24
🍀በብብትዎ ላይ እብጠት እንዲኖር የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶች አሉ። በጣም ከተለመዱት ምክንያቶች አንዱ የንፍፊት እብጠት ነው።
ንፍፊት የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት አካል ናቸው እነሱ እንደ ማጣሪያ ሆነው ፣ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነት ያስወግዳሉ። በብብት ላይ ያለው የንፍፊት እብጠት የኢንፌክሽን ወይም የአካል ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል።
መንስኤዎቹ
በሁለቱም ብብት አከባቢ ይህ ንፍፊት እብጠት ሲኖር የተላላፊ በሽታ ወይም ኢንፌክሽን እንዳለ ያሳያል እብጠቱ በአንድ በኩል ብቻ ሲሆን የጡት ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል።
ከእጅ በታች ያሉ ንፍፊቶች የጡት ካንሰር ከሚሰራጩባቸዉ የተለመዱ ቦታዎች አንዱ ነው ሆኖም ግን ፣ በአንድ በኩል ብቻ የንፍፊት እብጠት ከሚያስከትሉ ምክንያቶች መካከል፡-
🔺 የጡት ኢንፌክሽኖች ፣ ለምሳሌ ማስታይተስ ወይም መግል የያዘ እብጠት
🔺 የክትባት ምላሾች …………………….
ምልክቶቹ
አንዳንድ የብብት እብጠቶች ምንም ምልክቶች የላቸውም ፣ ህመም የሌላቸው እና ምንም ያለመመቸት ስሜት አይፈጥሩም። ሆኖም ፣ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከእብጠት ጋር ተጨማሪ ምልክቶችን ያስተውላ
እነዚህ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ :-
🔺 ትኩሳት
🔺 በብብት አካባቢ ህመም ወይም ምቾት ማጣት
🔺 የተከፈተ ቁስል ወይም መግል መዉጣት
🔺 መቅላት
🔺 በአንገት ፣ በላይኛው ደረት ወይም በሌሎች ቦታዎች ላይ የንፍፊት ማበጥ
🔺 በላይኛው የመተንፈሻ አካላት የኢንፌክሽን ምልክቶች
ህክምናዉ
በአብዛኛዉ ጊዜ የብብት እብጠት ምንም ዓይነት ህክምና ባያስፈልጋቸውም አንዳንዶቹ መንስኤዎች ግን ህክምና ይሻሉ የንፍፊት ማበጥን በቤት ውስጥ ለማከም :-
🔺 ያበጠዉን አካባቢ ሞቅ ባለ ዉሃ ፎጣ እየነከሩ ቦታዉ ላይ ጫን ጫን ማረግ
🔺 ብዙ ፈሳሽ መጠጣት ፣ እንደ ውሃ እና ትኩስ ጭማቂዎች
🔺 እረፍት ማረግ
🔺 የህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ
እናመስግናለን
መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌱🌱🌱
ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736