ኮሌስትሮል ምንድን ነዉ 🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
Author: admin
Date: 2024-05-16
ኮሌስትሮል ምንድን ነዉ
🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
፨ኮሌስትሮል በሰውነት ህዋሳት ውስጥ የሚገኝ የሚጣበቅ ቅባታማ ንጥረ ነገር ነው፡፡ለሰውነታችን የተወሰነ ኮሌስትሮል ሆርሞኖችን ፣ ቫይታሚን ዲ እና ምግብን ለመፈጨት የሚያስፈልግ ንጥረ ነገር ነው ሰውነት የሚያስፈልገውን ኮሌስትሮል በራሱ ይሰራል፡፡በተጨማሪ ከእንቁላል አስኳል ፣ስጋ፣ አይብ ፣ የወይራ ዘይት እና ኦቾሎኒ ማግኘት እንችላለን፡፡
#በደምዎ ውስጥ በጣም ብዙ ኮሌስትሮል ከተጠራቀመ ከሌላ ደም ውስጥ የሚገኝ ነገር ጋር በመደባለቅ ድንጋይ የሚመስል ክምችት ነገር በመፍጠር ከደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ ይጣበቃል፡፡ ይህም ችግር #አትሮስክለሮሲ በመባይ ይታወቃል፡፡በመሆኑም የደም ውስጥ ቧንቧዎችን በማጥበብ ወይም በመዝጋት ለደም ቧንቧ በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
✍️ #የኮሌስትሮል #አይነቶች
➥ #HDL የሚባል ሲሆን ጥሩ ኮሌስትሮል ነው ምክንያቱም ይህ ኮሌስትሮል ከሌላ የሰውነት ክፍል ኮሌስትሮል ተሸክሞ ወደ ጉበት ያስተላልፋል፡፡ ጉበት ደግሞ ኮሌስትሮሉን ከሰውነት ያስወጣል፡፡
➥ LDL መጥፎ ኮሌስትሮል ሲሆን የድንጋይ መሰል ክምችት በደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
#ከፍተኛ #የኮሌስትሮል #ምክንያት #ምንድነው?
➥ #ጤናማ ያልሆነ ያመጋገብ ዘይቤ ብዙ መጥፎ ቅባት መመገብ (saturated fat) እነዚህ ምግቦች ስጋ ፣ የወተት ተዋጾ ቼኮሌት ፣የተጠበሱ እና በማሽን የተዘጋጁ ምግቦች ፡፡
➥ የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግ ብዙ መቀመጥ እና እንቅስቃሴ አለማድረግ
➥ ሲጋራ ማጨስ
➥ በቤተሰብ ይህ አይነት ችግር ካለ
➥ ከመጠን በላይ ውፍረትና አልኮል በመጠጣት ነው።
#የኮሌስትሮል #ችግሮች #ምልክቶች #ምንድናቸው?
➥ በደም ውስጥ ያለው ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን ግልጽ ምልክቶች የሉትም ፣ ግን #angina (#በልብ ሕመም ምክንያት የደረት ህመም) የደም ግፊትና የደም ዝውውር ሕመሞችን ጨምሮ ምልክቶች ላላቸው ሁኔታዎች ተጋላጭነትዎን ከፍ ሊያደርግ ይችላል ስለዚህ ከፍተኛ የኮሌስትሮልን ተከትለው የሚመጡ በሽታዎችን ምልክቶችን ያስተውላሉ።
➥ #ስትሮክ
➥ #የልብ ድካም
➥ # (የደረት ህመም)
➥ #ከፍተኛ የደም ግፊት
➥ #የደም ቧንቧ በሽታ
➥ #ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ)
➥ #ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን እንዲሁ ለሃሞት ጠጠር የመጋለጥ እድልን ከፍተኛ ያደርገዋል።
#መፍትሄዎች
➥ ጤናማ አመጋገብ መከተል
➥ ከመጠን በላይ ውፍረት ካለ ለመቀነስ መሞከር
➥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
➥ በጤና ባለሙያ የሚታዘዙ መድሃኒቶችን መውሰድ
እናመስግናለን
መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736