———————(ሳጁታሪየስ)———————— ————ከህዳር 14 እስከ ታህሳስ 12—————
Author: admin
Date: 2024-05-09
አስትሮሎጂ የሰው ኮከብ
————————(ሳጁታሪየስ)————————
————ከህዳር 14 እስከ ታህሳስ 12—————
»» በግልፅነቱ የሚበረግጉ እንደ ስኮርፒዮ ያሉ ሰዎች በደግ አይን አያዩትም፣ እነሱም ቢሆኑ ጉዳት አልባነቱን ሲያውቁ ይተውታል። ዘዴ አልባነቱና አስቀድሞ አለማሰቡ ደካማ ጎኖቹ ናቸው።
»» ሳጁታሪየሶችን የተጣሏቸው ሴቶች ይታረቋቸውና መልሰው ጓደኛ ያደርጓቸዋል፣ አንቺም እንዲሁ ካደረግሽ ውድቀትሽ መሆኑን እወቂው፣ ስኮርፒዮን በሀፍረት የሚያሸማቅቅ ፍጡር ቢኖር ሳጁታሪየስ ነው ፣ስኮርፒዮን እኮ ማሸማቀቅ ከባድ ነው፣ ሳጁታሪየስ ግን ታዞለታል ፣ እያሳደደ ቆሌውን ይገፈዋል።
»» የሳጁታሪየስን ግልፅነት ትወጂለታለሽ ፣ የት፣ ከማን ጋር ምን ሲሰራ እንደዋለ ምንም ሳይደብቅሽ ይነግርሻል፣ ወይም የአፍ ወለምታ ሲዘባረቅ ትይዢዋለሽ። አይክፋሽ ታዲያ፣ አለበለዚያ ጋብቻችሁን ወደ ማፍረስ ታመራላቹ ጠንቀቅ በይ።
»» የሚፈልገው ወሲብ ብቻ ሳይሆን ለውጥና የአእምሮ መነቃቃት ጭምር ነው፣ ለዚህ ነው ቆንጅየዋን እንግዳ ተቀባይ ብቻ ሳይሆን ጋዜጣ ሻጯን አሮጊትና የፖሊስ ወታደሯን ጭምር ሲማትር የሚገኘው፣ ስለዚህ ብልህ ሴት መሆን አለብሽ። መሆን የሌለበሽ ደግሞ ቀናተኛ ነው ፣ ተጠራጣሪ አትሁኚበት ፣ ልታስሪው ብትፈልጊ እንኳን ገመዱን ረዘም አድርጊለት፣ የምርመራ ጥያቄ አትጠይቂው፣ እትነዝንዢው፣ እሄዳለሁ እያለሽ አታስፈራሪው፣ ነፃነት ሰጥተሽ ቀስ በቀስ አርሚው።
»» ህይወትን እሱ እንደሚያያት የምታይና ሰዎችን በነሱነታቸው የምትቀበይ ከሆነ ትስማሚዋለሽ ፣ የሚፈልጋት ሴት እንዲ አይነቷን ነው፣ ታዲያ የሚፈልገውን ሁሉ ልትሰጪው አይገባም የሚፈልገውን ግን ሁኚለት፣ ሆደ ሰፊ ሙሉ ለሙሉ ንቁ ሁኚ፤ የበላይ ሆኖ ቤቱን ይምራ፣ ስፖርት ውደጂ፣ ወደ ቤት አምልኮ ሲሄድ አጅቢው፣ መንፈስ ትኩስና ጉጉ ሁኚለት፣ ቤት ውስጥ አትሰሪው፣ አንቺንም ሊያስርሽ እንደማይችል ግልፅ አድርጊለትና ነፃ መሆንሽን ይወቅ።
»» ዘዴ አልባ፣ ስሜት ጎጂና ፊት ለፊት የሚሰነዝር ፍርጥ ያለ ነቀፌታ ከአሁኑ ልመጂው። ጠውላጋና ደካማ እንዲሁም አናቂ ሴት አይወድም፣ ገንዘብ አባካኝም ሊሆንብሽ ይችላል።
»» ሳጁታሪየሶች ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው የትስስር ገመድ ሲያገቡ ይበጠሳል ወይም ይላላል፣ በትዳራችሁ ላይ ጣልቅ እንዲገቡ አይፈቅዱላቸውም፣ ያንቺም ዘመዶች እንዲሁ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
እናመስግናለን
መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736