አስትሮሎጂ ወይም ኮከብ ካንሰር ኮከብ ————ከሰኔ 15 እስከ ሐምሌ 16
Author: admin
Date: 2024-05-08
አስትሮሎጂ ወይም ኮከብ
ካንሰር ኮከብ
————ከሰኔ 15 እስከ ሐምሌ 16————
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
»» ካንሰር ወንድ ቁጥብ ነው፣ ሀሳበ ብትን አይደለም፣ መጀመሪያ እንዳገኘሽ ልቡን አይሰጥሽም፣ እንግዳ ፊትም ያፍራል፣ የቅርብ ጓደኞቹ እንኳን በውል የማያውቋቸው አንድንድ ፀባዮች አሉት፣ ይህን ሰው በደንብ ለማወቅ ረጅም ጊዜና ሰፊ ትግስት ይጠይቃል።
»» ስሜተ ስስና ታማኝ ነው፣ ቅድም ንዴታም ሆኖ አግኝተሽው አሁን የጨዋ ፈገግታውን ተላብሶ ታይዋለሽ፣ የፍቅር ጥመኛ መሆኑ ጥርጥር የለውም፣ ስብእናው የሚቀያየር ሰው አይደለም፣ ስሜቶቹ ግን የሚቀያየሩ ናቸው፣ ፈገግታና ኩርፊያ፣ ሳቅና ሀዘን፣ ደስታና ትካዜ ቶሎ ቶሎ ይፈራረቁበታል፣ በያንዳንዱ ስሜት ውስጥ ሆኖ ታድያ ለራሱ ታማኝ ነው።
»» ጥራት እና ቁጠባ የካንሰር መመሪያዎች ናቸው፣ገንዘብ ለክፉም ለደጉም በሚል ይቆጥባል፣ ሁሉም በአግባቡ ነው እሱ ጋ፣ ካንሰር የማይሰረው የፈጠራ ስራ የለም፣ ስራ መፍጠር ላይ ጎበዝ ነው።
»» እናቱን ከልክ በላይ ነው የሚወዳት፣ በጨዋታው ውስጥ እንኳን ካፋ አጠፉም፣ እሱን ከፈለግሽ እናቱን መውዳድ አለብሽ፣ እናቱን ከዙፋናቸው ላይ አውርዶ አንቺን አዲሷን ፍቅረኛውን ማንገስ ይከብደዋል፣ እናቱ ከወደዱሽ ልብ ሙሉ ሆነሽ የሙሽራ ልብስሽን ምረጪ፣ አንድ ሺህ ድብቅ ፍላጎት ያለውን የካንሰርን ልብ ድል አድርገሻል ማለት ነው።
»» ለፍላጎቶቹ ሁሉ የምትስማሚ ሆነሽ ሲያገኝሽ በሙገሳና በስጦታ ማጥለቅለቅ ብቻ ሳይሆን ጠበቅ አድርጎም ይይዝሻል፣ እዚ ላይ ግን ለመድረስ የጥራት ደረጃ መመዘኛው ቀላል አይደለም፣ ያለ በቂ ምክንያት ትዳር መስርተው ሲቃጠሉ መኖር አይፈልጉም፣ አንዴ ካፈቀሩ መለየት አይሆንላቸውም።
»» ካንሰር ለልጆቹ እንዴት የሚያስደስት አባት መሰለሽ ፣ ሴቶቹም ወንዶቹም ካንሰራዊያን ለልጆቻቸው እናት ናቸው።
»» ምንም ቢሆን ግን የተጨረማመተ ባርኔጣውን፣ የተቀደደ የቴኒስ ጫማውን፣ የሰበሰባቸውን ቴምብሮች ወይም የልጆቹን ሪፖርት ካርዶቹን አይጠቅሙም ብለሽ እንዳትጥይበት፣ ቅሪቶቹ መሆናቸውን ልትዘነጊ አይገባም።
እናመስግናለን
መልካም ጤንነት
🌱🌱ማንኛውም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ🌱🌱🌱
"ለበለጠ መረጃ፦ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ስለሞን አዳሙን ያማክሩ
"አድራሻ፦ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
"ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736