ዛሬ ደግሞ ስለ አኳሪየስ ኮከብ እንነግራችዋለን
      🍀ከ ሀኪም ሰለሞን አዳሙ🍀
በቅንነት ሼር ያድርጉልን

፨አኳሪየስ ከጥር 12 እስከ የካቲት 13
የአኳሪየስ ዘመን ስለሆነ ቀውለል ያሉና የማዳበሪያ ትውልዶች እየተባለ ሚቀለድባቸው ረዣዥም ልጆች የበዙበት ሆኗል። በነገራችን ላይ ግዙፍ ሰውን ወይም ነገርን እብድ የሚያክል ብለን የምገልፀው ብዙ ጊዜ እንደዚህ በየወፈፌነት  የምናውቃቸው ሰወች #አኳሪየስ ስለሆኑ ነው። ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ እንዲሉም ብዙሃን የስነ - አእምሮ ሀኪሞችም አኳሪየሶች ናቸው።
የ#አኳሪየስ ቁመና ልእልናንጨየተጎናፀፈ ነው ። ገፅታው እንደሳንቲም ላይ ምስል ቁርጥ ያለርዝመት አለው ። ሲናገር ጭንቅላቱን ወደታች ወይም ወደጎን ጣል የማድረግ ልማድ አለው ። ሲራመድ እንደእርኩም አጎንብሶ ሲሆን ለብቻው እያወራም ሊሆን ይችላል ብዙ ጊዜ መንገድ ስቶ ከቀጠሮው ሰአት ያረፍዳል። ከሚጠበቅበት ስፍራም በበር ሲጠቅ  በመስኮት በመስኮት ሲጠበቅ ደግሞ በበር በፊት በር ሲጠበቅ በጎሮ በር ሊገባ ይችላል ።

ወንዶቹ #አኳሪየስ እንደሴት ሰፊ ዳሌ አላቸው ሴቶቹ ደግሞ እንደወንድ ትክሻቸው ሰፊ ይሆናል። አልፎ አልፎ ቁመት አጭር #አኳሪየሶች ይፈጠራሉ ። ቀልደኛ የሆኑ #አኳሪየሶችም ያጋጥማሉ ። አንዳንዶቹ ደግሞ ትሁትና ጭምት ናቸው።